በአዋሳ በርካታ ታዋቂ ባለሃብቶች ታሰሩ
በአዋሳ ከተማ በተለያዩ የንግድ መስኮች ተሰማርተው የሚገኙ በርካታ ነጋዴዎች በዘረኛውና አምባገነኑ ባለስልጣናት ትእዛዝ ወደ እስር ቤት እየታጎሩ መሆኑን የግንቦት ሰባት ዘጋቢ ከስፍራው በላከልን ዘገባ ገለጸ፣ ፣ ነጋዴዎቹ በገፍ ወደ ማጎሪያ እስር ቤት እየተላኩ ያሉት የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት ) አልከፈላቺሁም በሚል ሽፋን እንደሆነ ተያይዞ የደረሰን ዘገባ አመልክቷል።
እንደ ዘጋቢያችን ሪፖርት እነኝህ የነጋዴው ማህበረሰብ አካል የሆኑት የአዋሳ ከተማ ነዋሪዎች ወደ እስር ቤት እንዲታጎሩ ምክንያት ነው የተባለውን የቫት ክፍያ በወቅቱ ከፍለው ያጠናቀቁ መሆናቸውን ነገር ግን ክፍያውን መክፈላቸውን በመግለጽና በማብራራት ለምን እንታሰራለን ብለው ቢጠይቁም ሰሚ ሊያገኙ ያልቻሉ መሆኑ ታውቋል።
ታሳሪ ነጋዴዎች ከሆኑት ውስጥ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለገ የአንደኛው ነጋዴ ወንድም መሆኑን የገለጸ የግንቦት ሰባት ዘጋቢ ያነጋገርው ግለሰብ እንደገለጸው፣ ወንድሙን የዘረኛው አገዛዝ ባለስልጣናት ወደ እስር ቤት የወሰዱት በቫት ክፍያ አለመከፈል ሳይሆን፣ በከተማው ዉስጥ እየተባባሰ በመጣው ጸረ ወያኔ እንቅስቃሴ አገዛዙን አይደግፉም የሚባሉት ሁሉ ሊነሳ ይችላል ተብሎ ለሚፈራው ህዝባዊ አመጽ ሃይል እንዳይሆኑ በፍርሃት ለማሸማቀቅ ታስቦ እንደሆነ ገልጿል። በመቀጠልም፣ ዘረኛው አገዛዝ ዜጎችን ለማፈን በግፍ ወደ እስር ቤት ማጎሩን ቢቀጥልም፣ ከፍተኛ ብሶት ያለበት ህዝብ ስሜቱን መቆጣጠር ከማይችልበት ደረጃ ላይ እየደረሰና ነጻነቱንም በትግሉ ለመቀዳጀት እየሰራ ነው ብሏል::
ዘረኛው የትግራይ ገዢ ጉጂሌ ባለስልጣናት፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የኦነግ አባል ናቺሁ በማለት በፓርላማ ምክር ቤት ለረጂም ጊዜ ሲሳተፉ የነበሩ የመድረክ አባላትን፣ ህዝባዊ አመጽ ለማነሳሳት ትቀሰቅሳላቺሁ በማለት በርካታ የሆኑ ወጣቶችን ፣ እንዲሁም የተለያዩና ፍጹም ከባለጉዳዩቹ ጋር ተያያዥነት የሌላቸውን ውንጀላዎች በመፈብረክ በርካታ ዜጎችን ወደ እስር ቤት እየወረወሩ እንደሆነ በስፋት ሲዘገብ መቆየቱ አይዘነጋም፣ ፣ ከዚህም በተጨማሪ የዘረኛውና አምባገነኑ አገዛዝ ቁንጮ የአንድነት ፓርቲ አባላትን ህዝባዊ አመጽ እንዲነሳ እየሰሩ ለመሆኑ መረጃዎች አሉን እናም ርምጃ እንወስድባቺሁአለን በማለት በምክር ቤት ተብየ ስብሰባ ላይ መዛቱ አይዘነጋም::