በ3 የመንግስት መ/ቤቶች ዉስጥ መመሪያን ያልተከተለ የሂሳብ አያያዝ እንዳለ የፌዴራል ዋናው ኦዲተር መ/ቤት ገለፀ

ደንብና መመሪያን ያልተከተለ የሂሳብ አያያዝ ችግር በዋነኛነት ከታየባቸዉ መ/ቤቶች መካከል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዲፕሎማቲክ ሚሲዮኖች ዘርፍ ፡ የመከላከያ ሚኒስቴርና የኢምግሬሽንና የዜግነት ጉዳዮች ዋና መመሪያ እንደሆኑ የዋናው ኦዲተር ቢሮ አስታወቀ።

 የፌዴራል ዋናዉ ኦዲተር ይህን የገለፀዉ በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ለመንግስት ወጪ አስተዳዳርና ቁጥጥር ቋሚ ኮሚቴ ባቀረበው ሪፖርት ላይ ነው።

በዚህም መሠረት፤ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዲፕሎማቲክ ሚሲዮኖች ዘርፍ 21,736,349.98 ብር ገቢ ሂሳብ፣ 6,630,327.06 ብር ደንብና መመሪያን ያልተከተለ ወጪ ሂሳብ፣ እንዲሁም በመከላከያ ሚኒስቴርና በኢምግሬሽንና የዜግነት ጉዳዮች ዋና መምሪያ በድምሩ 2.8 ሚሊዮን ተከፋይ እና 5.3 ሚሊዮን ተሰብሳቢ ሂሳብ እንደሚታይ ተገልጿል። የመ/ቤቶቹ የሂሳብ አያያዝ ግልፅነት የጎደለዉ በመሆኑ ትክከለኛነቱን ለማረጋገጥ እንደማይቻል በሪፖርቱ ላይ ተጠቅሷል። በሪፖርቱ ላይ የተጠቀሱት ሶስት የመንግስት መስሪያ ቤቶች ለገዢዉ ወያኔ ፓርቲ የፖለቲካ አፈፃፀም እጅግ የቀረቡ መሆናቸዉ አሰፈፃሚነታቸዉ በማንአለብኝነት ለህገ ወጥ የሂሳብ አያያዝና የበጀት አጠቃቀም እንደዳረጋቸው ይታወቃል።