ዘረኛውና አምባገነኑ የወያኔ አገዛዝ እጂግ በሙስና የተጨማለቀ መሆኑ በግልጽ እየታየ ርዳታ ለጋሽ ሃገራት ጆሮ ዳባ ልበስ ማለታቸው አሳፋሪ ነው ተባለ
የብሪቲሽ ብሮድ ካስቲንግ ኮርፖሬሽን ቢቢሲ እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር ባለፈው አርብ ግንቦት 21 ቀን ታዋቂ ጋዜጠኞችና ጉዳዩ የሚመለከታቸው ከፍተኛ የእንግሊዝ መንግስት ባለስልጣናት በተገኙበት የጠረቤዛ ዙሪያ ውይይት ያደረገ ሲሆን በውይይቱ ወቅት የመለስ ዜናዊ አገዛዝ ዉስጡና ዉጩ በሙስና የተጨማለቀ አገዛዝ መሆኑ እየታወቀ ብሪታኒያም ሆነች ሌሎች ምዕራባዊያን አገሮች በዚህ ዘረኛና ሙሰኟ አገዛዝ ላይ ለሚቀርቡ አሉታዊ ሪፖርቶች ምንም ጆሮ አለመስጠታቸውና ተገቢ እርምጃ አለመውሰዳቸው እጅግ አሳፋሪ እንደሆነ አንድ የዉይይቱ ተሳታፊ ገለጹ።
በዚህ የእንግሊዝ መንግስት ለታዳጊ አገሮች በሚያደርገው የልማት እርዳታዎች ዙሪያ ባተኮረው ውይይት ኢትዮጵያን በሚመለከት የተናገሩት የዉይይቱ ተሳታፊ እንዲህ ነበር ያሉት።
“እስከዛሬ ድረስ በየትኛውም መድረክ በድፍረት የማይነሳን ሃሳብ ለማንሳት እፈልጋለሁ። ከርዳታ ጋር በተያያዘ የእንግሊዝ መንግስት የሚያደርገውን ሰብዓዊ እርዳታ እኔም የምደግፈው ነውና ችግር የለብኝም ፣ ነገር ግን ከመንግስትም በላይ የእንግሊዝ ሌበር ፓርቲን እጅግ መውቀስ እፈልጋለሁ። የእንግሊዝ መንግስት ለተለያዩ አገሮች የሚሰጣቸውን የልማት እርዳታ የታክስ ከፋዩ የእንግሊዝ ህዝብ ገንዘብ ለታዳጊ አገሮች ስለመሰጠቱ እንጂ እርዳታ ተቀባይ አገሮች የሚሰጣቸዉን ገንዘብ በምን መልኩ እንደሚጠቀሙበት ምንም አይነት እውነተኛ ክትትል አያደርግም።፣ በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች ስለምዘዋወር በዚህ የልማት ርዳታ ዙሪያ የተወሰነ ግንዛቤ ያለኝ ሰው ነኝ። ስለሆነም ከመንግስታችን በልማት ርዳታ ስም ወደ እርዳታ ተቀባይ አገሮች የሚጎርፈው ገንዘብ አጠቃቀም ምን እንደሚመስል የራሴን ግንዛቤ ወስጃለሁ። ይህ የእርዳታ ገንዘብ በሙስና በተጨማለቁ የፖለቲካ መሪዎች አማካኝነት ተመልሶ ወደ ስዊዝ ባንክ እየመጣ ለመሆኑ ምንም የሚያጠራጥር አይደለም። ለዚህም አንድ ዋነኛ ምሳሌ ልስጣችሁ፣ “የኢትዮጵያ የስብዓዊ መብቶች ጠባቂ” በመባል የሚታወቀው ተቋም፣ የኢትዮጵያ መንግስት የልማት ርዳታን በምን መልኩ እየመዘበረው እንደሆነ በጥናት በተደገፈ መረጃ በግልፅ አጋልጧል። በኢትዮጵያ ያለው አገዛዝ ማኦይስት የሆነ ሶሻሊስት አገዛዝ ነው። የኢትዮጵያ መንስግስት ብሪታኒያ ለታዳጊ አገሮች በየአመቱ ከምትሰጠዉ እርዳታ ከፍተኛዉን ድርሻ የሚወስድ መንግስት ነዉ፤ ብሪታኒያም ሆነች ሌሎች ለጋሽ አገሮች ገንዘቡን በቀጥታ ለአገዛዙ ይሰጣሉ፣ አገዛዙ ደግሞ ፍጹም በሙስና የተጨማለቀ አገዛዝ ነው፣ ፣ ይህ መሆኑ እየታወቀ እንግሊዝም ሆነች ሌሎች አገሮች ተፈጸመ የተባለውን ምዝበራ ለማጣራት ትንሽም ቢሆን ሙከራ አለማድረጋቸው ወይንም ፍላጎት አለማሳየታቸው፣ በጣም አሳፋሪና አሳዛኝ ድርጊት ነው፣ ፣ ሂዩማን ራይትስ ዋች በግልጽ እንዳስቀመጠው እንዲህ አይነቱ አካሄድ እጅግ አደገኛ እንደሆነ በአንክሮ ገልጿል። ሂዩማን ሪይትስ ዋች ባቀረበው ሪፖርት ዙሪያ የኢትዮጵያው አገዛዝ ከፍተኛ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ከበርካታ ወራት በፊት ጀምሮ በማድረግ ላይ ይገኛል። ሀሳቤን ለማጠቃለል የእንግሊዝ መንግስትም ሆነ ሌሎች ምዕራባዊያን አገሮች እንዲህ ላለው ወንጀል ተጠያቂ ሊሆኑ ይገባል በማለት ሃሳባቸውን አጠቃልለዋል።
አስተያየት ሰጪው ሃሳባቸውን ሲያጠቃልሉ የዉይይቱ ተሳታፊዎች በከፍተኛ ጭብጨባ ሀሳቡ ተቀባይነት ያለው መሆኑን የገለጸ ሲሆን፣ የእንግሊዝ መንግስት ባለስልጣናት እራሳቸውን ለመከላከል ሙከራ ሲያደርጉ ተስተዉለዋል።
ዘረኛውና አምባገነኑ የወያኔ አገዛዝ የልማት ርዳታን ለፖለቲካዊ ፍጆታ እያዋለ ነው በማለት ሂዩማን ራይትስ ዋች በጥናት ላይ የተመሰረተ ሪፖርት ከበርካታ ወራት በፊት ማቅረቡ አይዘነጋም።