ህዝብ ሲያስመርር የነበረው የሐረሪ ክልል የመሬት አስተዳደር ሹም ተገደለ
የዘረኛውና አምባገነኑ ወያኔ የጭቆናና አፈና አገዛዝ ያንገሸገሻቸው ኢትዮጵያዊያን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በዘረኛው አገዛዝ ባለስልጣናት ላይ ጠንከር ያለ ርምጃን መውሰድ መጀመራቸው የሚታወቅ ሲሆን ሰሞኑን የሐረሪ ክልል የመሬት አስተዳደርና የካሳ ክፍያ ኃላፊ የነበረው ሐሺም ኢድሪስ በጥይት ተደብድቦ መገደሉን የግንቦት ሰባት ዘጋቢ ከስፍራው ባስተላለፈልን ሪፖርት ለማወቅ ተችለአል።
እንደ ዘጋቢያችን ሪፖርት ለወያኔ ዘረኛ አገዛዝ ሆድ አደር በመሆን በህዝብ ላይ ከፍተኛ በደል ሲፈጽም የቆየው ሃሺም ኢድሪስ የተዘፈቀበት የሙስናና አድሏዊ አሰራር እጂግ ያበሳጫቸው ግለሰቦች በርካታ መሆናቸውን ከነኝህ ውስጥ አንዱ ብስጪታቸው ከሚገባው በላይ በማለፉ ርምጃውን መውሰዳቸውን ገልጿል፣ ፣ የወያኔው ሆድ አደር ሃሺም ህይወቱ ከማለፉ በፊት ቀደም ብሎ በሃረር ከተማ ፈረስ መጋላ ተብሎ ከሚጠራው የከተማው እምብርት ላይ በጥይት ተመቶ ቆስሎ እንደነበርም ተያይዞ የደረሰን ዜና አሳይቷል።
የዘረኛውና አምባገነኑ የወያኔ አገዛዝ በኢትዮጵያዊያን ላይ የሚፈጽመው ግፍና በደል ልኩን አልፎ መፍሰስ ከጀመረ መቆየቱ የሚታወቅ ሲሆን፣ ይህም አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ የሃገሪቱ ክልሎች የሚገኙ ዜጎች፣ የአገዛዙ ታማኝና ሆድ አደር ባለስልጣናት እየፈጸሙ ላለው ልክ ያጣ በደል ተገቢውን ቅጣት እየሰጡ መሆኑን ያረጋግጣል።
ሱለይማን አህመድ የተባሉ የሃረር ከተማ ነዋሪ በአገዛዙ ሆድ አደር ባለስልጣን ላይ የተወሰደውን የግድያ ርምጃ አስመልክቶ ለዘጋቢያችን በሰጡት አስተያየት በተለይም በሃረሪ ክልል ዘረኛውና አምባገነኑ የወያኔ አገዛዝ ከፍተኛ ውጥረትና ፍርሃት ስላለበት ህብረተሰቡን በጣም በሚያሳዝን ሁኔታ አፍኖ እንደሚገኝ፣ በሰበብ አስባቡም ወደ እስር ቤት እየወሰደ እንደሚያጉር ገልጸዋል፣ ፣ በመቀጠልም ይህ አፈናና ጭቆና ለአገዛዙ ባለስልጣናት መፍትሄ መስሎ ይታያቸው እንጂ፣ ህዝብ ብሶትና ምሬት ሲበዛበት እንዲህ አይነት ርምጃ መውሰዱ አዲስ ነገር አይደለም፣ በዚህ የሚያቆምም አይደለም ብለዋል፣ ፣ በመጨረሻም ወያኔ በምንም መልኩ ይሁን ለህዝብ ጆሮ ሰጥቶና ችግራችንን ተገንዝቦ መፍትሄ ያመጣል የሚል ተስፋ ፍጹም የሌለን በመሆኑ፣ አገዛዙ እስኪወገድ ድረስ በየግላችን የምንችለውን አይነት የተናጠል ርምጃ መውሰዳችን ይቀጥላል በማለት አስተያየታቸውን አጠቃለዋል።