በአዲስ አበባ ከተማ እየታየ ያለው ዝርፊያ ተስፋፍቶ ቀጥሉአል፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አምስት ኪሎ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሁለት ቤተ ሙከራዎች ባልታወቁ ሰዎች ተዘረፉ

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የተደራጁ ሃይሎች የጦር መሳሪያን በመጠቀም ሰፊ የሆነ ዘረፋ አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ እየፈጸሙ መሆኑ ተደጋግሞ የተዘገበ ሲሆን የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን ባወጣው ዘገባው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ኤሌክትሪካል ኢንጂነሪንግ የትምህርት ክፍል ሥር የሚገኘው ሲስኮ ላብራቶሪ በሩ በድሪል ተበስቶና ተከፍቶ መዘረፉ ታውቁአል፡፡ይህ ላብራቶሪ ከተዘረፈ ከሦስት ቀን በኋላ፣ ደግሞ አይአይቲ ደልሂ የተባለው የማስተርስ ተማሪዎች ላብራቶሪም እንዲሁ መዘረፉ ታውቁአል::

በኢትዮጵያ ውስጥ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሚታየው የተደራጀ ዝርፊያ ህብረተሰቡን ስጋት ላይ የጣለ ጉዳይ ሆኗል ያለው ኢሳት በአገሪቱ ውስጥ የሚታየው የኑሮ ውድነት መባባስ እና የደሀው ቁጥር ከቀን ወደ ቀን መበራከት ዝሪፊያውን እንዳባባሰው ለማወቅ መቻሉንም አክክሎ ገልጹአል።

እንደ ኢሳት ምንጮች ዘገባ በአዲስ አበባ ከተማ እየታየ ያለውን የተደራጀ ዝሪፊያው ከጀርባ ሆነው ከሚመሩት መካከል ነባር የህወሀት አባላትም እንደሚገኙበት፣ እነዚሁ አባላት የተለያዩ መጠን ያላቸውን የጦር መሳሪያዎች ላደራጁአቸው ሃይሎች በመስጠት በእጅ አዙር ዝሪፊያ ላይ መሰማራታቸውን ህብረተሰቡ ጠንቅቆ እንደሚያውቅ ታውቁአል።

ቃሊቲ ውስጥ በተደራጀ ዝሪፊያ ታስረው ከሚገኙት መካከል አብዛኞቹ የህወሀት አባላት መሆናቸውን መረጃዎች ያሳያሉ ያለው ኢሳት አባላቱ በእንዲህ አይነት ዝሪፊያ ውስጥ ለምን ለመሰማራት እንደፈለጉ የሚታወቅ ነገር እንደሌለም አክሎ ገልጹአል::

ዘረኛውና አምባገነኑ የወያኔ አገዛዝ በምርጫ ዘጠና ሰባት በአዲስ አበባ ከተማ የማያዳግም ቅጣትን ከቀመሰ ወዲህ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎችን በተለያዩ መንገዶች መበቀል መቀጠሉ በስፋት የተዘገበ ሲሆን በ 1997 ምርጫ ማግስት ዘራፊዎች የአዲስ አበባ ከተማ ህዝብን ሲያስቸግሩ ሂዱና ቅንጅትን ጥሩ ቅንጅት ያድናቺሁ የሚል መልስ እየተሰጣቸው እንደነበረና ከነዚህም ዘራፊዎች አብዛኞቹ ሴረኛው ወያኔ አሰማርቱአቸው የነበሩ መሆኑ መዘገቡ አይዘነጋም::