የመለስ ዜናዊ የይስሙላ ችሎት በስዊድናዊያን ጋዜጠኞች ማርቲን ሽብየ እና ጆአን ፐርሰን ላይ የጥፋተኝነት ብይን ከሰጠ በኋላ እያንዳንዳንዳቸውን በአስራ አንድ ዓመታት ጽኑ እስራት መቅጣቱ መላውን ዓለም አስቆጥቷል። ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄም እነዚህን የመለስ ዜናዊ የይስሙላ ችሎት ውሳኔዎችን አጥብቆ ያወግዛል። እርግጥ ነው ለእኛ ለኢትዮጵያዊያን እነዚህን የመሰሉ ፍርደ ገምድል ውሳኔዎች ለሃያ ዓመታት የኖርንበት ነውና አዲስ ነገር […]

መለስ ዜናዊ ከደርጉና ከአጼዎቹ ጋር ራሱን እያወዳደረ እኔ እሻላችኋለው እያለ ሲሰብክ እነሆ ሦስት አስርተ ዓመታትን አስቆጥሯል። ይሄንንም ስብከት ያመኑ ብዙ ሰዎች መኖራቸውም እውነት ነው። መለስ ዜናዊ  ዘመኑ ከደረሰበት የእደገት ደረጃ  እጅግ ወደ ኋላ እርቆ የሚጓዝ ክፍ ዘረኛ በመሆኑ ሁል ግዜ ራሱን የሚያወዳድረው ከሙታን ጋር ነው እንጂ ከህያዋን ጋር አይደለም። በህያዋን መንደር የሚያቆመውን ምንም በጎ ተግባር […]

የወያኔ መከላከያ ሚንስቴር ሰሞኑን ይፋ ባደረገው ዜና በወያኔ የመተካካት ፖሊሲ በመከላኪያ ሠራዊት ውስጥ ካሉት ከፍተኛ ባለማዕረጎች ውስጥ 13 ጀኔራሎችና 303 ሌፍቴናንት ኮሌነልነትና ሙሉ ኮሌነል ማዕረግ ያላቸው አባላት በጡረታ ስም ከሰራዊቱ መገለላቸው ታውቆአል። የግንቦት7 ምንጮች መረጃ እንደሚያመለክተው ግን በጡረታ ከተገለሉት አብዛኞቹ ከቀርብ ጊዜያቶች ወዲህ በመላው አገሪቱ ውስጥ በተከሰተው የኑሮ ውድነትና እየተስፋፋ በመጣው የፖለቲካ አፈና ምክንያት ህዝባዊ […]

የኢትዮጵያ ሳታላይት ቴለቪዥን ኢሳት በትናትና ዜናው እንደዘገበው፤ የዳርፉር አማጺ መሪ የነበሩት ዶ/ር ካሊል ኢብራሂም ግዲያ ላይ የወያኔ እጅ ያለበት መሆኑን የሚያመለክት ፍንጮች መገኘታቸውና የዘረኛው መለስ ዜናዊ አፈቀላጤ የሆነው በረከት ስሞኦን ከግዲያው አንድ ቀን ቀደም ብሎ ካርቱም ውስጥ ከሱዳን ከፍተኛ የደህንነት ሰዎች ጋር ውይይት ማድረግ መታወቁ መረጃውን የበለጠ አጠናክሮታል። እንደኢሳት መረጃ ምንጮች ዘገባ በረከት ስሞኦን ከዚህ […]

የመለስ ዜናዊ አገዛዝ በኦጋዴን ወገኖቻችን ላይ እየፈጸመ ያለውን ግፍና ሰቆቃ ለመታዘብ ወደ ክልሉ ሲገቡ የተያዙትና በወያኔ ፍርድቤት የአስራ አንድ አመት ጽኑ እስራት የተፈረደባቸው ሁለቱ የስዊድን ጋዜጠኞች ጉዳይ ከፍተኛ የሆነ አለም አቀፍ ተቃውሞ በአገዛዙ ላይ ማስነሳቱን የዝግጅት ክፍላችን አረጋገጠ። የወያኔ ፍርድ ቤት ከትናንት በስቲያ ባስተላለፈው ቅጣት የተቆጡና የተቃውሞ ድምጻቸውን እያሰሙ ካሉት አገሮች በተጨማሪ የተለያዩ አለም አቀፍ […]

በህወሃት የሚመራው ዘረኛው የመለስ ዜናዊ አገዛዝ በተለያየ ሹመትና ጥቅማ ጥቅሞች የራሱ ምርኮኛ አድርጎ የሚገለገልባቸውን የሌሎች ብሔረሰብ ተወላጆች በአዳዲስ ታዛዦች ለመተካት ዘወትር በሚጠቀምበት ግምገማ ሰሞኑን በደቡብ ክልል በርካታ ሰዎች ከነበሩበት የሃላፊነት ቦታ መባረራቸውን የኢትዮጵያ ሳታላይት ቴለቪዥን ኢሳት በትናንትና የዜና ዘገባው አስታወቀ። እንደ ኢሳት ዘገባ የደቡብን ክልል እያተራመሰ ያለውና ከ50 በላይ ለሚሆኑ የወያኔ የቀድሞ ሹሞች ከሃላፊነት መነሳት […]

በማንኛውም የትምህርት ተቋማት ውስጥ ያሉ ወጣት ዜጎች በአገራቸው የፖለቲካ ጉዳይ ላይ ወያኔን በሚቃውም መልኩ ምንም አይነት ተሳትፎ እንዳያደርጉ ለማገድ ለሥርዓቱ ታማኝ የሆነ አስተዳደር በየትምህርት ቤቶቹ ከማቋቋም ጀምሮ ለነጻነታቸውና ለመብታቸው የሚቆረቆሩትን አድኖ ከትምህር ገበታቸው በማባረር ተግባር ላይ የተሰማራው የመለስ ዜናዊ ዘረኛ አገዛዝ ሰሞኑን በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ላይ ቅጣት ማስተላለፉን ዘጋቢያችን ከስፍራው ባስተላለፈው ዜና ገለጸ። በጎንደር ዩኒቨርሲቲ […]

ወጣቷ ሴት ጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙ ይህንን የወያኔ ከፍተኛ ወንጀል መርማሪዎች ተንኮል ያጋለጠቺው ባለፈው ሳምንት ሃሙስ የወያኔ ፈደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልዴታ ምድብ 3ኛ ወንጀል ችሎት ፊት ቀርባ የተመሰረተባትን የሽብርተኝነት ክስ እንድታስተባብል በተጠየቀችበት ወቅት እንደሆነ ዘጋቢያችን ከስፍራው ከላከልን ሪፖርት ለማወቅ ተችሎአል። ጋዜጠኛ ርዕዮት ለይስሙላ ፍርድቤቱ በሰጠቺው ማስተባበያ ቃል “እኔ በሙያዬ ጋዜጠኛ ነኝ፣ ይህን የሚያውቀው አርቲስት ደበበ […]

ግንቦት7 የፍትህ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ በሁለቱ የስዊድን ጋዜጠኞች ላይ የተሰጠውን ውሳኔ ያወገዘውና አለም አቀፍ ህብረተሰብ የሚችለውን ሁሉ ጫና አድርጎ ያለምንም ቅድሜ ሁኔታ በአስቸኳይ እንዲፈቱ የጠየቀው ባለፈው ቅዳሜ ታህሳስ 15 ቀን በእንግሊዘኛ ቋንቋ ባወጣው መግለጫ ነው። “ጋዜጠኛ ማርቲን ሽብዬ እና ጆሀን ፐርሰን ጆግኖቻችን ናቸው” በሚል ርዕስ ግንቦት 7 ባወጣው በዚህ መግለጫ፤ በህዝባዊ ወያኔ አርነት ትግራይ ቁጥጥር […]

አገር ዉስጥ የሚታተመዉን ካፒታል ኢትዮጵያ የተሰኘዉን የእንግሊዘኛ ጋዜጣ ጠቅሰን፣ ወደ ሶስት መቶ የሚሆኑ ከፍተኛ የኢትዮጵያ መኮንኖች ስራቸዉን እንዲለቁ መደረጉን መዘገባችን ይታወሳል። ከአዲስ አበባ የደረሰን ዘገባ እንደሚጠቁመዉ ከስራ እንዲሰናበቱ ከተደረጉት መኮንኖች መካከል ጄነራል ሳሞራ የኑስ እና ከርሳቸው ጋር ቅርበት ያላቸዉ ሞኮንኖች እንዳልተነኩ ለማወቅ ችለናል። ለአቶ መለስ ዜናዊ በጣም ታማኝ የነበሩትና በቅርቡ ግን ከጄነራል ሳሞራ የኑስ ጋር […]

በሽብር ስራ ተሰማርታችኋል በሚል መስረት የሌለዉ ክስ የታሰሩ፣ የአቶ አንድዋለም አራጌ፣ የአቶ እስክንድርና ነጋ እና ሌሎች ሰላማዊ ታጋዮችን ጉዳይ የሚያዳምጠዉ ችሎት፣ ዲሴምበር 24 ቀን ፣ አቃቢ ሕግ ያቀረባቸዉን ቪዲዮዎችና ኦዲዮዎች አዳምጧል። ፍርድ ቤቱ በመጀመሪያ ያዳመጠዉ በአንድነት ፓርቲ ጽ/ቤት ዉስጥ በይፋና በግልጽ የተደረገዉን፣ አቶ እስክንድር ነጋ በእንግድነት የተገኙበትን እና በአቶ አንዱዋልም አራጌ የተመራዉን ስብሰባ ነበር። በዚህ […]

አቡጊዳ – የናዝሬት ድህረ ገጽ አቶ እስክንድር ነጋን የአመቱ ሰዉ ብሎ ሰየመ ! ሁሉንም ወገኖች ፣ የኢሕአዴግ ደጋፊዎችን ሆነ የሕወሃት/ኢሕአዴግ ተቃዋሚዎችን የሚያስተናግደዉ ገለልተኛው የናዝሬት ድህረ ገጽ፣ አንጋፋዉ ጋዜጣኛ እስክንድር ነጋን የአመቱ ሰዉ ብሉ ሰይሞታል። ድህረ ገጹ፣ ሃሳብን በነጻነት የመግልጽ መብት ይከበር ዘንድ አቶ እስክንድር በየሳምንቱ ለአንባቢያን ፣ ትምህርት ሰጪ ጽሁፎች ያለ ማቋረጥ ማበርከቱን ያስታወሰ ሲሆን፣ […]

አሁን አደገኛ ሁኔታ ላይ ተደርሷል። ፍትህን ወደ መቃብር ለመክተት በተቀናጀ እና በተደራጀ መልኩ የሚሴረው ሴራ እና የሚሸረበው ተንኮል ስጋና ደም ለብሶ እነ…

ቅዳሜ መታተም የነበረበት የፍትህ ጋዜጣ፣ አንድ ቀን ቆይቶ እሑድ እንደታተመ፣ የኢኤምኤፍ ድህረ ገጽ ገለጸ። በፍትህ ጋዜጣ አዘጋጆችና ዘገባዊዎች ላይ ከመቼዉም በበለጠ ጫናና ወከባ እየደረሰ እንደሆነ ይታወቃል። የጋዘጣዉ አምደኛ የሆነችዉ ርዮት አለሙ መሰረት በሌለዉ የሽብር ክስ ተከሳ በወህኒ የምትገኝ ሲሆን የርሷ ጠበቃ በፍርድ ቤት የሚያቀርባቸዉ፣ የጋዜጣዉ አዘጋጆችን ጨመሮ በርካታ ምስክሮች ማስፈራሪያ እንደሚደርስባቸዉ ኢኤምኤፍ አዲስ አበባ ያሉ […]

ወይዘሮ ሙሉ ሰለሞን፣ የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት
ወይዘሮ ሙሉ ሰለሞን ባሳለፍነው ሳምንት የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት…

ከአንድ ወር በፊት በጐንደር ዩኒቨርሲቲ ተከስቶ በነበረው ወረርሽኝ በሽታ መነሻ፣ ረብሻ በማስነሳት በዩኒቨርሲቲው ንብረት ላይ ውድመት አድርሰዋል በተባሉ …

ዶር በረከተ ሃብተ ስላሴ ከጥቂት ወራት በፊት፣ የቆሰለች አገር ( Wounded Nation) የተባለዉን መጽሃፋቸዉን፣ በርካታ ኢትዮጵያዉያን በተገኙበት ፣ ኒዉዮርክ በሚጘኝ የባርስን ኤንድ ኖብልስ መጽሃፍት ቤት አስመርቀዋል። በዚሁ ወቅትም፣ በኤርትራ ስላለዉ ሁኔታ ሰፊ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን፣ በዚያ ከነበሩ ወገኖችም ለቀረበላቸው ጥያቄዎች ግልጽ ምላሾች ሰጥተዋል። ዶር በረከት ፣ አስመራ የተወለዱ የሕግ ባለሞያ ሲሆኑ፣ በአጼ ኃይለስላሴ ዘመን፣ የሃር […]

የኢትዮጵያን ፓለቲካና ኢኮኖሚ ተቆጣጥረው የድሆችን ደም እየመጡ ያሉት የትግራይ ገዢ ጉጅሌ አባላትና ሎሌዎች እአአ ከ1990 መጀመሪያ እስከ 2007 መጨረሻ በነበሩት 18 ዓመታት ውስጥ 8.3 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ከኢትዮጵያ ማሸሻቸው የተባበሩት መንግሥታት የልማት መርሃግብር (ዩ.ኤን.ዲ.ፒ) በጥናት ማረጋገጡን ይፋ ካደረገ አንድ ዓመት አልሞላውም። ስምንት ቢሊዮን ሶስት መቶ ሚሊዮን (8.3 ቢሊዮን) የአሜሪካ ዶላር ማለት ዜናው በተነገረበት ወቅት 150 […]