Author: Daniel Kibret www.danielkibret.com
"እናቴን አደራ"
አያልቅበት ስንታየሁ ሱዳን ውስጥ ለ3 ዓመት ያህል የኖረ የብርሀኑ ጌታነህ ወዳጅ ነው። የሚናፍቃቸውን እና ያላባት ብቻቸውን ያሳደጉትን፤ ለስደቱ ምክንያት የሆኑትን እናቱን ለማየት የዛሬ ዓመት ገደማ ወደ ሀገሩ ተመለሰ።
ሱዳን በነበረበት ወቅት ከራሱ ተርፎ እናቱን ለመርዳት የሚልካት ጥቂት ገንዘብ በስተርጅናቸው ሰው ቤት ተቀጥረው የጉልበት ስራ ከመስራት አላዳናቸውም።
ወይዘሮ አለሚቱ በላይነህ ልጃቸው ሱዳን ሳለ የሚልክላቸው ገንዘብ ከቤት ክራይ ክፍያ ውጪ የማይሸፍንላቸው ቢሆንም፤ ችግራቸውን ለልጃቸው ነግረው ከማሳቀቅ፤ በስተርጅናቸው የጉልበት ስራ ውስጥ ገብተው ኑሮዋቸውን በመከራ ተያይዘው ቆዪ።
የእናቱ ነገር የማይሆንለት አያልቅበት፤ በናፍቆቱ ምክንያት ወደ ሀገሩ ሲመለስ ግን ሱዳን እያለ ይልክ የነበረው ገንዘብ ምን ያህል የእናቱን ህይወት ፈቅ ማድረግ እንደተሳነው ተረዳ።
የዚያን ጊዜ ታድያ ከሱዳን አድማስ ማዶ፤ እናቱን ለመጦር ይችልበት ዘንድ ተስፋ የጣለበትን የባህር ላይ ጉዞ ህልም ሰነቀ።
ለልጆቹ ህይወት በእጅጉ ከሚጨነቀው የረዥም ጊዜ ወዳጁ ብርሀኑ ጌታሁን ጋርም ሀሳባቸው ገጠመ። ወደ ሊቢያም በጋራ ሊሻገሩ ተቃጠሩ። ልጆችን ለማሳደግና እናትን ለመጦር።
አያልቅበት በሀምሌ 5፣ 2007 ዓ.ም ወደ ሱዳን ለመመለስ በሚሸኝበት ጊዜ፤ ከዚህ ቀደም በሰላም ደርሶ የተመለሰው ልጃቸው ተመልሶ የሚመጣው መርዶው መሆኑን ፈፅሞውኑ ባይገቱም ካይናቸው ልጃቸው ከሚርቅ በርሀብ ቀድመውት ቢሞቱ መርጠው ነበር።
የብርሀኑ እና አያልቅበት ቀጠሮ ቀን ሲደርስ፤ ብርሀኑ ሚስቱን “ድሬዳዋ ለስራ መሄዴ ነው፤ ስልኬ ግን አይሰራም” ብሎ ሀገሩን ለቆ ወደ ሱዳን አመራ።
በተቀጣጠሩ በስድስት ወራቸው ሱዳን ላይ የተገናኙት እኒህ የልብ ወዳጆች፤ አንዳቸው ስለ ልጅ አንዳቸው ስለ እናት ፍቅር ምስክር ሆነው። ልጆቹን ለናታቸው አደራ ሰጥቶ የተሰደደው፤ ለእናት የሚሰጥ ፍቅር ሀያልነት በአያልቅበት ሲማር፤ ለልጆቹ ሲል የተሰደደው ብርሀኑ ደግሞ በተራው የአባት ፍቅር ምሳሌው ነበር።
ወይዘሮ አለሚቱ፤ አያልቅበት ከሄደ በጝላም ቢሆን የዘወትር ፀሎታቸው የሚወዱት ልጃቸው መንከራተት በቅቶት ከእቅፋቸው ዳግም እንዲገባ ነበር።
የሀገራችን ሰማይ ጠቁሮ፤ ኢትዮጵያም አምርራ በልጆችዎ የግፍ ሞት ስታለቅስ፤ እንደ ብርሀኑ ባለቤት ብርቱካን እና መላው ኢትዮጵያዊ ሁሉ የአያልቅበት እናትም እንባቸውን ይዘረግፉት ነበር። ሊቢያ የማን ሀገር ጎረቤት እንደሆነች እንክዋን የማያውቁት እናት እንዲሁ በደፈናው ልጆቼ ለሚልዋቸው የኢትዮጵያ ሰማዕታት ሁሉ ያነቡ ነበር።
ከሚወደው ወዳጁ ብርሀኑ ጎን በሊቢያ በርሀ አንገቱን ለሰይፍ የሰጠው አያልቅበት ሰማዕትነቱ የተሰማው ዘግይቶ የሁሉም ቤት ሀዘን በመብረድ ላይ ሳለ ነበር።
የእኒህን እናት አይን ለማየት በውነቱ ማን ይደፍር ይሆን? የሀዘናቸውንስ ጥልቀት ምን ይገልፀው ይሆን? በምንስ አይነት መንገድ….?
ዛሬም ቢሆን ስሜቴ ክፉኛ ተጎድቶአል። ገርጂ ከጊዮርጊስ ቤ.ክርስቲያን ጀርባ በምትገኘው ሰማዕቱ ልጃቸው በተከራየላቸው ጠባብ ቤት ውስጥ፤ በብቸኝነት ተኮራምተው፤ አንድያ ልጃቸው ተመልሶ እንደማያዪት ከተረዱ ሳምንት ሳይሞላቸው ያለ አስተዛዛኝ ብቻቸውን የተቀመጡት እናት፤ የሚያነጋግራቸው ዘመድ፣ ሲቦርቁ እያዪ የሚፅናኑባቸው ህፃናት የሌሉበት ጠባብ ቤት ያለመጠን ሰፍቶ ፍርሀት ሲያነግስባቸው፤ ቤታቸው የተሰቀለው ልጃቸውን ከነገዳዩ የሚያሳይ ምስል እያባነነ እንቅልፍ ሲከለክላቸው፤ ይህንን ሁሉ እየሰማን እና ይህን ሁሉ እያየን ዝም የምንል መሆናችን ያሳፍራል። (በእርግጥ ለህዝቡ ማን ነገረው? የመንግስት ሚድያዎች በሌሎች ጉዳዮች ተጠምደዋል።
ሀላፊነታቸውን በብርቱ ይወጡ የነበሩ ጋዜጦች እና መጵሄቶች ዛሬ በስራ ላይ የሉም) ዛሬስ እኔም እፍረት በዝቶብኝ አንቆ ሊደፋኝ ደርሶዋል።
አያልቅበት እኮ “የሞተው ሁላችንንም ተክቶ ነው። እሱ እኮ አንገቱን የደፋው የናቱን አንገት ቀና ሊያደርግ ነው።”
በኢትዮጵያ አምላክ እለምናለው አዛውንት እናትና ህፃናት ልጆች አንድ ናቸው። ስደቱም የመጣው ለማሳደግና ለመጦር ነው። እኚህን እናት አጠገባቸው ሄደን እናጽናናቸው። ቀሪ ህይወታቸውንም ወድቀው እንዳይቀሩ እንደግፋቸው።
የሰማዕቱ አያልቅበት ድምጽ ግን ይሰማል። ብቸኛዋን “እናቴን አደራ”።
ለሰማዕቱ አያልቅበት ነፍስ ይማርልን!! እንፀድቅባቸው ዘንድ እናቱንም ትቶልን ከሱ ሰማዕትነት
በረከት እንድንሳተፍ እነሆ “እናቴን አደራ” ይለናል።
ከቻሉ በአካል ተገኝተው እናታችንን ያፅናኑ፤ ካልቻሉ ይህን መልዕክት share በማድረግ የሰማዕታቱ ቤተሰቦች መሆናችንን (እንግለጥ።)
አሁንም በድጋሚ እናገራለው። ከብዙ ቃል መግባት ጥቂት ቃልን መፈፀም ዋጋው የላቀ ነው። እግዚአብሔር ይርዳን!!
ትኩረት የሚሹት ሁለቱ የሰማዕቱ የብርሃኑ ልጆች
![]() |
|
ፎቶ፡- ያሬድ ሹመቴ
|
ጀማል ማነው?
‹ጀማል› የተባለ ሙስሊም ወንድማችን በሊቢያ ከተሠዉ ክርስቲያኖች ጋር አብሮ ተሠዉቷል እየተባለ ሲነገር ቆይቷል፡፡ በአካባቢው የነበሩ የዓይን እማኞችና ሌሎችም የቅርብ ምንጮች ታሪኩ የተሳሳተ መሆኑን ቢናገሩም ሰሚ ለማግኘት ግን አልተቻለም፡፡ አንዳንዶቹም ታሪኩን የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችና ክርስቲያኖች ፍቅር ማሳያ አድርገው ተሟግተዋል፡፡ እንደ እኔ ግን ይህንን ታላቅ ፍቅር ለማሳየት ‹ጀማል› የተባለ መሥዋዕት መፍጠር አያስፈልገንም፡፡ ፍቅሩ ነበረ፤ አለ፡፡ ተጨማሪ ፈጠራው አያስፈልገውም ነበር፡፡
የተለመዱ የአማርኛ ስሕተቶችና መፍትሔያቸው
እየተስተዋለ
እግዜር ያተረፋት ነፍስ ምስክርነት
በቀደም ዕለት አይሲስ በባሕር ዳርቻ የሠዋቸው ክርስቲያኖች በሰውነታቸው ላይ የመስቀል ምልክት የነበረባቸውን መርጦ ነው፡፡ እነርሱን በተለየ ኮንቴይነር አስቀምጧቸው ነበር፡፡ ይኼንን መረጃ የነገረኝ ሰው ሊገደሉ ተመርጠው ከተለዩት ወገን ነበረ፡፡ ሌሎች በኮንቴይነር ያስቀመጣቸው ክርስቲያኖችም አሉ፡፡ ምናልባት ከዚህ የከፋ ዜና እንሰማ ይሆናል፡፡ አምላክ ይጠብቀን፡፡ አሁንም የአይሲስ አራጆች የመንግሥት ወታደሮችን ልብስ ለብሰው ሌሎች ስደተኞችን እየያዙ ነው፡፡
ኢትዮጵያውያን ክርስቲያን ሰማዕታት – ዳንኤል ክብረት
በተለያዩ የባለ ሥልጣናትና የእምነት መሪዎች መግለጫዎች ላይ በሊቢያ ምድር የተሠዉትን ሰማዕታት በኢትዮጵያዊነታቸው ወይም በስደተኛነታቸው ብቻ አደጋ እንደደረሰባቸው ተድርጎ እየተነገረ ነው፡፡ እነዚህ ክቡራን ኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖች ናቸው፡፡ የተሠዉትም እምነታቸውን አንለውጥም ስላሉ ነው፡፡ አይሲስ የሠዋቸው በኢትዮጵያዊነታቸው አይደለም፡፡ አይሲስኮ ዜግነት የለውም፡፡ ዐረቦች፣ አውሮፓውያን፣ አፍሪካውያን እስያውያን የተቀላቀሉት አሸባሪና አሰቃቂ ድርጅትና አስተሳሰብ ነው፡፡ እንዲያውም ባለፈው ሰሞን ትውልደ ኢትዮጵያውያን ከእንግሊዝ ወደ አይሲስ ለመግባት ያደረጉትን ጥረት በመገናኛ ብዙኃን ሰምተን ነበር፡፡ አይሲስ አገር የለውም፡፡
እነዚህ ወንድሞቻችንማ ማተብ የሚያደርጉበትን አንገት ለእምነታቸው ሲሉ የሰጡ ቅዱሳን ሰማዕታት ናቸው፡፡ እኛ በቃል ብቻ የምንናገረውን ሰማዕትነት በ21ኛው ክፍለ ዘመን በተግባር ያሳዩ የተግባር ክርስቲያኖች ናቸው፡፡ ምናልባት ባለ ሥልጣናቱና ሚዲያዎቹ ይህንን ለመናገር የከበዳቸው ሌሎች አማኞችን እናስከፋለን ብለው አስበው ይሆናል፡፡ እውነት ለመናገር ግን በግድ ሃይማኖታቸውን ወደ እስልምና (ያውም አይሲስ ወዳጣመመው የእስልምና አመለካከት) መቀየር ነበረባቸው ብሎ የሚከራከር ኢትዮጵያዊ ሙስሊም ይኖራል ብዬ አላምንም፡፡ ቢኖርም አመለካከቱን እንዲፈትሽ ማድረግ እንጂ እርሱን ላለማስቀየም እውነቱን መካድ አያስፈልግም፡፡ የአይሲስን ሐሳብ ተቀብለው፣ እምነቱን አራምደው፣ ከእርሱ ጋር ተቀላቅለው ለተወሰነም ጊዜ ቢሆን እድሜ ለማራዘም ቢፈልጉ መንገዱ ነበረ፡፡ ወላዋዮች፣ ለእምነት ግድ የለሾ፣ እምነታቸው እንደ ሸሚዝ ለመቀያየር የሚፈልጉ አቋም የለሾች ቢሆኑ ኖሮ ሞት ሩቅ ነበረ፡፡ እነ ኢያሱ፣ እነ ባልቻ፣ እነ ተስፋየና እነ ዳንኤል ግን እንደዚያ አልነበሩም፡፡ በእምነታቸው ጸኑ፤ በክርስቲያንነታቸው ታረዱ፣ ሰማዕትነትንም ተቀበሉ፡፡ይኼንን እውነታ መካድ ሰማዕታቱን ሁለት ጊዜ መግደል ነው፡፡ ከሞታቸው በላይ የሞቱበትን ክቡርና ቅዱስ ዓላማ መካድ አብልጦ ይገድላቸዋል፡፡ደግሞም ስደተኛነታቸው ለአደጋው ምክንያት ሆነ እንጂ የተሠዉት በስደተኛነታቸው አይደለም፡፡ ስደተኞችም ሆነው እምነታቸውን ለመለወጥ ቢፈልጉ ኖሮ ይችሉ ነበር፡፡ የተሠዉት በክርስትናቸው ነው፡፡ ክርስቲያን ኢትዮጵያውያን ናቸው፡፡ አንገታቸውን የሰጡት ለክርስቶስ ነው፡፡ እንደ አግናጥዮስ ምጥው ለአንበሳ አነጋገር ‹እንደ ንጹሕ መገበሪያ ስንዴ ሆነው› ለአምላካቸው ነው በመሥዋዕትነት የቀረቡት፡፡ እነርሱ አንገት የሰጡለትን ክርስትና እኛ ለመናገር ለምን ፈራነው?
የጎንደር ከተማ መንፈሳውያን ወጣቶች የአሸባሪው የአይሲስን ኢሰብአዊ ድርጊት አወገዙ
በጎንደር ከተማ የሚገኙ የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች፣ የመንፈሳውያን ወጣቶች ማኅበራትና የማኅበረ ቅዱሳን የጎንደር ማዕከል አባላት በላኩት መግለጫ በአሸባሪውና አረመኔው አይሲስ በኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖች ላይ የተፈጸመውን ጭካኔ አውግዘዋል፡፡ በመግለጫው ላይ እንደተገለጠው ‹‹‹‹ISIS›› የሽብር ቡድን 30 ኢትዮጵያውያንን ክርስቲያን በመሆናቸውና ሃይማኖታችንን አንቀይርም በማለታቸው ርህራሄ በጎደለው ሁኔታ አንገታቸውን በሰይፍ በመቅላትና በጥይት በመደብደብ የፈጸመው ዘግናኝ ተግባር ኢትዮጵያዊነትን የሚፈታተን፣ ታላቅ ኀዘንን በክርስቲያኖች ላይ ፈጥሯል፡፡›› ብሏል፡፡ በማያያዝም እንደ ቤተ ክርስቲያን ልጅነታቸው ሊደረጉ ይገባል ያሏቸውን አራት ሐሳቦች ለሀገረ ስብከቱ አቅርበዋል፡፡ የመግለጫውን ሙሉ ቃል ቀጥሎ መመልከት ይቻላል፡፡ ይህንን በመጫን መግለጫውን ያንብቡ
የሰባት ቀናት ጸሎተ ምሕላ ታወጀ
ቂርቆስ በኀዘን ማቅ
ወደ ባሕላችንና እምነታችን ስንመለስ
ሰማዕታተ ሊቢያና የ”ሲኖዶሱ” መግለጫ
ቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ ሰጠ
የምናዝነው ስንት ሰው ሲሞት ነው? – ዳንሄል ክብረት
በየመን፣ በደቡብ አፍሪካና በሊቢያ ስለሚሞቱት ዜጎቻችን የሚሰጡት መንግሥታዊ መግለጫዎች ሁለት ነገር የጎደላቸው ናቸው፡፡ የመጀመሪያው ሰብአዊ ስሜት፡፡ ማንኛውም ሰብአዊ ፍጡር ስለሌላው ሰብአዊ ፍጡር መከራና ስቃይ ሲሰማ መጀመሪያ አንዳች የኀዘን ስሜት ይሰማዋል፡፡ ከዕውቀት ይልቅ ስሜት ለሰዎች ቅርብ ነውና፡፡ ባለሥልጣን ቢሆን፣ ፖሊስ ቢሆን፣ ዳኛ ቢሆን፣ ጠቅላይ ሚኒስቴር ቢሆን ሰው ነውና ስሜት አለው ተብሎ ይታሰባል፡፡ ያዝናል፣ ይከፋዋል፣ ልቡ ይረበሻል፣ ሆዱ ይባባል፣ ኅሊናው ይደማበታል ተብሎ ይታመናል፡፡ ስለዚህም የመጀመሪያው ሥራው ማዘን ቀጥሎም ኀዘኑን በወጉ መግለጥ ነው፡፡
ሰሞኑን የማያቸው መግለጫዎቻችን ግን የኀዘን ወግ በሀገራችን የሌለ የሚያስመስሉ ናቸው፡፡ መሪዎቻችን ወደ አደባባይ ወጥተው ለሞቱት ወገኖቻችን እንደ ኢትዮጵያዊነት ኀዘናቸው የሚገልጡት፣ ጥቁር ልብስ ለብሰው የምናያቸው፣ ነጠላ የሚያዘቀዝቁት ስንት ሰው ሲሞትብን ነው? የሚያስብሉ ናቸው፡፡ ኀዘንኮ ፖለቲካ አይደለም፣ ፓርቲ አይደለም፣ ርእዮተ ዓለም አይደለም፣ ሊብራልም አብዮታዊ ዲሞክራሲም አይደለም፡፡ ኀዘን ሰብአዊነት ነው፡፡ የሚመራቸው ዜጎቹ፣ የሚያሠማራቸው በጎቹ ሲታረዱና ሲሞቱ ኀዘኑን በይፋ የማይገልጥ መሪና እረኛ መቼ ነው ኀዘኑን የሚገልጠው?
ዜጎቹ በሕገ ወጥ መንገድም ይሂዱ በሕጋዊ፣ ድንበር ጥሰውም ይሂዱ በአውሮፕላን ተሳፍረው፤ መጀመሪያ ሰዎች፣ ቀጥሎም የዚህች ሀገር ዜጎች ናቸውና ኀዘን ይገባቸዋል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ አንድ ሰው አገኘዋለሁ ብሎ ከሚያስበው ክብር አንዱ በሞቱ ጊዜ የክብር ልቅሶና ኀዘን ነው፡፡ ኢትዮጵያውያን ከአካባቢያቸው ላለመራቅ፣ ከራቁም ለመመለስ ከሚሰጧቸው ምክንያቶች አንዱ ‹በክብር ዐርፎ በክብር መቀበርን፣ የክብር የኀዘን ሥነ ሥርዓትን ማግኘትን› ነው፡፡
ካገሬ እንዳወጣህ አገሬ መልሰኝ
በሹም የታዘዘ አፈር አታልብሰኝ፤
እንኳን የሚቀብረው የሚያዝንለት አጣ
ምን ወግ ማረግ ያያል ካገሩ የወጣ፤
የሚሉት ለዚህ ነበረ፡፡
የመንግሥት አካላት ለምን ይኼንን ለመዘንጋት እንደፈለጉ አልገባኝም፡፡ የደቡብ አፍሪካው ቃጠሎና ግድያ ሲመጣ የሀገራችን ፕሬዚዳንትና ጠቅላይ ሚኒስትር ብቅ ብለው ‹‹በወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ባለው ነገር ከልብ እናዝናለን፣ ከደቡብ አፍሪካ መንግሥት ጋር ተነጋግረን አስፈላጊውን እናደርጋለን፤ ተመሳሳይ ችግር ለወደፊቱ እንዳይከሰትም አንሠራለን› ዓይነት ሰውነት ያለበት መግለጫ ጠብቄ ነበር፡፡ የለም፡፡ ሲሆን በሀገራችን የልቅሶ ሥነ ሥርዓት መሠረት፡፡ አሁን ደግሞ ዓለም ያወቀው አሸባሪ ‹አይ ሲስ› ኢትዮጵያውያኑን በክርስትና እምነታቸው ብቻ ሲሠዋቸው የተሰጠው መግለጫ ስሜት የሌለበት፣ ማዘን መደሰታቸውን የማይገልጥ፣ እንኳን ሰው እንስሳ የሞተብን የማያስመስል ሆነ፡፡ ከማጣራቱም ከምኑም በፊትኮ ስሜቱ ይቀድማል፡፡፡ አዝናችኋል ወይ? ስትሰሙና ስታዩ ምን ተሰማችሁ? የአሜሪካ መንግሥት እንደዚያ ዓይነት መግለጫ ሲያወጣ ከኢትዮጵያ መንግሥት ያንን ነው ወይ መስማት ያለብን? ለመሆኑ መሪዎቻችን ኀዘናቸውን የሚገልጡት ምን ስንሆን ነው? ለምንድን ነው ሁሉም ነገር ፖለቲካ የሚሆነው?
ሁለተኛው የሚጎድለው ነገር ደግሞ ፍጥነት ነው፡፡ አትሌቶቻችን በኦሎምፒክ ሲያሸንፉ የባለሥልጣናቱ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልእክት ሯጮቹ ቆርጠውት ካለፉት ሪቫን ቀጥሎ የሚመጣ ዜና ነበር፡፡ አትሌቶቹ ደክሟቸው ከመሬት ሳይነሡ የባለሥልጣናቱ መልእክት ለሚዲያ ይደርስ ነበር፡፡ በዚህ የሁላችንም ኀዘን በሆነው ጉዳይ ግን ለምን መዘግየት እንደተመረጠ ግልጽ አይደለም፡፡ ማጣረቱ፣ መረጃ መሰብሰቡ፣ ተጨማሪ የዲፕሎማሲ ሂደቶችን መሄዱ ጊዜ ይወስዳል፡፡ ማዘን ግን ጊዜ አይወስድም፡፡ ቪዲዮው ተለቅቋል፡፡ ሲሞቱ እያየን ነው፡፡ መልካቸው የኛው ነው፡፡ አይሲስ የገደላቸው ‹ኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖች› ብሎ ነው፡፡ የዓለም ሚዲያዎች ያንኑ እያስተጋቡ ነው፡፡ ይኄ ለኀዘን ያንሳል? አፈፍ ብሎ ተነሥቶ ‹በሆነው ነገር እናዝናለን፤ ልባችን ተነክቷል፤ ለቤተሰቦቻቸው መጽናናትን እንመኛለን፤ ዝርዝሩን በየጊዜው እንነግራችኋለን› ለማለት ስንት ሰዓት ይወስዳል? የደቡብ አፍሪካው ችግር ደረሰ እንደተባለ ሙጋቤን ለውግዘት የቀደማቸው የለም፡፡ የኛዎቹስ የት ሄዱ?
መንፈሳዊ መሪዎችስ የት ናቸው? አንዳንዶቹ ውጭ ሀገር መሆናቸው እየተሰማ ነው፡፡ ሲሆን ይህንን ሲሰሙ አቋርጦ መምጣት፤ ካልሆነም ባሉበት ሆኖ አባታዊ ኀዘንን መግለጥና በእምነቱ የሚገባውን ማድረግ ይገባ ነበር፡፡ ሲኖዶሱስ ምን እየሠራ ነው? አልሰማም ይሆን? ዛሬ ጠዋት ቢያንስ በአዲስ አበባ አብያተ ክርስቲያናት ጸሎት መደረግ አልነበረበትም? ባፈው ካይሮ ሄዳችሁ ከግብጽ ቤተ ክርስቲያን ምንድን ነው ያያችሁት? በጎቹ እረኛ የላቸውም ማለት ነው? አባቶች የሚያዝኑት ምን ሲገጥማቸው ነው? እረኛው የሚያለቅሰው ስንት በጎች ሲታረዱ ነው?
ቤተ ክርስቲያኒቱ ነገሩን በዝምታ የምታልፈው ከሆነ እኛ እንደ ጥንታዊቷ ቤተ ክርስቲያን ትውፊታዊ ቀኖና እነዚህን በክርስትናቸው ምክንያት የተሠው ክርስቲያኖች ‹ሰማዕታተ ሊቢያ› ልንላቸው ይገባል፡፡ የሰማዕትነታቸውንም በዓል ማክበር አለብን፡፡ በስንክሳሩ ማስገባት ባንችል ታሪካቸው በኅዳጉ ማስፈር አለብን፡፡ ማንም ይሁኑ ማን፣ በሚገባ የተማሩም ይሁኑ ያልተማሩ፣ ከመካከላቸው የማያምኑም እንኳን ቢኖሩ የተገደሉበት ምክንያት ክርስትና ነውና ሰማዕታት ናቸው፡፡ ያውም ‹ኢትዮጵያውያን ሰማዕታት›፡፡ በስንክሳሩ እንደምናነበው በዲዮቅልጥያኖስ ዘመን የክርስቲያኖች መንደርና ቤተ ክርስቲያን እየተወረረ ክርስቲያኖቹ ሲሠው ገና ያልተጠመቁት፣ ነገሩ ያልገባቸው፣ ክርስትናን ለመቀበል ያልወሰኑት ሁሉ አብረው ተሠውተዋል፡፡ ቤተ ክርስቲያን ግን የተሠውበት ምክንያት ክርስትና በመሆኑ ሁሉንም ሰማዕታት ብላቸዋለች፡፡ የእነዚህም ክብር እንዲሁ ነው፡፡
እነርሱ በሰማይ ዋጋ አላቸው፡፡ አክሊለ ሰማዕታትንም ተቀብለዋል፡፡ እኛ ግን ሰማዕታቱን ባለማክበራችን ክብር ይጎድልብናል፡፡ ‹በረከታቸው ይደርብን› እንጂ ‹ነፍስ ይማር› አንልም፡፡
ኢትዮጵያውያኑ ሰማዕታት
ዛሬ የዓለም መገናኛ ብዙኃን የ30 ኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖችን በኢስላሚክ ስቴት በሰማዕትነት መገደል ሲዘግቡ ነበር፡፡ ሰው በእምነቱ ብቻ ሰማዕትነት የሚከፍልበት ዘመነ ሰማዕታት አንደገና ታድሶ እየተነሣ ነው፡፡ ትናንት ግብጻውያን ምእመናን የከፈሉትን ሰማዕትነት ዛሬ ኢትዮጵያውያኑ ከፍለውታል፡፡ ክርስቲያን መሆን ወንጀል ሆኖ፡፡ ሰማዕታቱስ ወደሚወዱት ጌታ ሄደዋል፡፡ ይህ ጊዜ ግን የኢትዮጵያ መንግሥትና የኢትዮጵያ የእምነት ተቋማት የሚፈተኑበት ጊዜ ነው፡፡ የግብጽ መንግሥትና የግብጽ ቤተ ክርስቲያን ለግብጽ ሰማዕታት ያደረጉትን በቅርብ ዓይተናል፡፡ የኛዎቹ በሚዛን የሚመዘኑበት ወይ ቀልለው ወይም ከብደው የሚገኙበት ጊዜ ላይ ነን፡፡ እግዚአብሔር ከሰማዕታቱ በረከት ይክፈለን፡፡
የሳይንቲስቱ ልጅ ጥያቄ
ግብረ ሕማማት
ጥንታውያን የብራና መጻሕፍት እንደ ሰነዶች ምዝገባና ማረጋገጫ ጽ/ቤት
የአድዋ ዘማቾች
![]() |
|
የጉዞው መሥራቾች
|
![]() |
|
ተጓዦቹ ከመልስ በኋላ
|
![]() |
|
ጽዮን – እንደ እቴጌ ጣይቱ
|
![]() |
|
የጉዞው አስተባባሪ ያሬድ ሹመቴ
|
የአማርኛ ቋንቋ ከየት ወዴት፤ ተግዳሮቶቹና መፍትሔዎቹ
ሸዋ ረገድ ገድሌ
የደብረ ሊባኖሱ እልቂት
አዳቦል
እየደመሰሱ መቅዳት
ፍቅር እስከ መቃብርን የጻፉት ‹‹ሐዲስ›› ናቸው ወይስ ‹‹ዓለማየሁ››?
ጠላ፣ ጥብስና ግድብ
ዝቋላ ሀገሩ የት ነው?
ሦስተኛው የበጎ ሰው ሽልማት ተጀመረ
እስኪ እንያችሁ
ያልተባለ ይመስል ነበር በዚህች ሀገር፡፡ ‹ፍቅር እዚህ ቦታ ፈገግ ብሎ ነበር› አለ ኤፍሬም ሥዩም፡፡ መቼም ፈገግ ካለባቸው አጋጣሚዎች መካከል አንዱ በቀደም ጋዜጠኞቻችን ‹ፍቅር የመጣውኮ ከውጭ ሀገር ነው› ሊሉን ሲደርሱ ሰምቶ መሆን አለበት፡፡
የአማርኛ ሞክሼ ሆሄያት
የተፈተነው ማነው?
እስኪ ይኼንን በአንድ ትምህርት ቤት ለሦስተኛ ክፍል ተማሪ የቀረበ ፈተና ተመልከቱት፡፡ አሁን የሚወድቀው ማነው? ተማሪው ወይስ ራሱ ትምህርቱ? እስኪ የስሕተቱን ብዛት እዩት? ወይ በአፍ መፍቻ ቋንቋችን ተምረን ጽንሰ ሐሳቡን አልተረዳነው፣ ወይ በእንግሊዝኛ ቋንቋ ተምረን ቋንቋውን በሚገባ አላወቅነው፤ ከሁለት ያጣን ሆንኮ፡፡ ለመሆኑ ፈተናው እንዲህ ከሆነ ትምህርቱማ ምን ሊሆን ነው? እንዲህ እያስተማርንና እየፈተንንስ ምን ዓይነት ትውልድ ይሆን የምናወጣው? ‹አለሽ መስሎሻል ተበልተሽ አልቀሻል› አለ ያገሬ ሰው፡፡
ጎንደሬው የጃማይካ ሰው
ታሪክ ሠሪ ታሪክ አሻጋሪ ሲያገኝ
አበው ሲመርቁ ‹‹ወይ መልካም ልጅ፣ ወይ መልካም ደቀ መዝሙር ይስጥህ›› ይላሉ፡፡ የሚረከብህ ማለታቸው ነው፡፡ ብዙ ታሪክ ሠሪዎች ታሪካቸውን የሚያስተላልፍላቸው አጥተው ሳናውቃቸው ቀርተናል፡፡ ዛሬ ታሪካቸውን ከፍ አድርገን የምንናገርላቸው ታላላቆቻችን ታሪካቸውን የሚጽፍ፣ የሚጠብቅና ለትውልድ የሚያስተላልፍ ያገኙትን ነው፡፡ ስማቸውን ሰምተን ታሪካቸው ያጣን፣ ሥራቸው ደርሶን ታሪካቸው የጠፋብን አያሌ ጀግኖች አሉን፡፡ አንዳንድ አባቶች እንዲያውም ሰው ሲያጡ ታሪካቸውንና ቅርሳቸውን ለወንዞችና ለተራሮች በአደራነት ሰጥተው ነበር፡፡ ይሄው በየዘመኑ እየተቆፈረ የሚወጣው ቅርስ መሬት አደራ የተቀበለችውን እያስረከበች ነው፡፡
ወንድሟ
ከአኩስምና ከቻይና ግንብ በፊት
![]() |
|
ማክሰኞ ለም ሆቴል አካባቢ ለመንገድ የተቆፈረ ገደል ውስጥ የገባው መኪና(ፎቶ ፡- ጽላት ጌታቸው)
|
ቁስል ተራ
ጎርፍና ግፍ
እሳት በዳጋ እስጢፋኖስ
ቀጣይ ዜና – እሳት በዳጋ እስጢፋኖስ
እሳት በዳጋ እስጢፋኖስ ገዳም
በጣና ሐይቅ ውስጥ በሚገኘው የዳጋ እስጢፋኖስ እሳት መነሣቱን የገዳሙ ምንጮች ተናግረዋል፡፤ እሳቱ የተነሣው ከደኑ አካባቢ ሲሆን ወደ ገዳሙ ገና አልደረሰም፡፡ የክልሉ ፖሊስ ወደ ቦታው በፍጥነት መድረሱ ተሰምቷል፡፡ አባቶች እሳቱን ቆርጦ ለመከላከል እየሞከሩ ነው፡፡ በሰው ኃይል ለመከላከል የማይቻል ከሆነ አስፈላጊውን ሁሉ እንደሚያደርግ ክልሉ ገልጦላቸዋል፡፡
ተዋሕዶ በተዐቅቦ
ስለ ገና በዓል እና ጾም አንዳንድ ጥያቄዎች
እንደ ሰው ወይስ እንደ እንስሳ
በልዩ ቅናሽ የመጻሕፍት ሽያጭ ወር









































