አቡጊዳ – የናዝሬት ድህረ ገጽ አቶ እስክንድር ነጋን የአመቱ ሰዉ ብሎ ሰየመ !
አቡጊዳ – የናዝሬት ድህረ ገጽ አቶ እስክንድር ነጋን የአመቱ ሰዉ ብሎ ሰየመ !
ሁሉንም ወገኖች ፣ የኢሕአዴግ ደጋፊዎችን ሆነ የሕወሃት/ኢሕአዴግ ተቃዋሚዎችን የሚያስተናግደዉ ገለልተኛው የናዝሬት ድህረ ገጽ፣ አንጋፋዉ ጋዜጣኛ እስክንድር ነጋን የአመቱ ሰዉ ብሉ ሰይሞታል። ድህረ ገጹ፣ ሃሳብን በነጻነት የመግልጽ መብት ይከበር ዘንድ አቶ እስክንድር በየሳምንቱ ለአንባቢያን ፣ ትምህርት ሰጪ ጽሁፎች ያለ ማቋረጥ ማበርከቱን ያስታወሰ ሲሆን፣ በዛሬይቱ ኢትዮጵያ ግን፣ ሃሳብን በነጻነት የመግልጽ መብት እንደ »ሽብርተኛነት” የሚቆጠርበትና በሞት የሚያስቀጣ መሆኑ ያትታል።
የአቶ እስክንድር የአሁኑ መታሰር የመጀምሪያዉ እንዳልሆነ፣ ክጥቂት አመታት በፊትም ከባላቤቱ ከወ/ሮ ሰርካልም ፋሲል እና ከሌሎች የሰብአዊ መብት ተከራካሪዎችና ጋዜጠኞች ጋር መታሰሩን የጠቀሰዉ የናዝሬት ድህረ ገጽ፣ የአቶ እስክንድር ነጋ ባለቤት ወ/ሮ ስርካለም ፋሲል፣ ልጇን በእሥር ቤት እንደወለደችም አስታወሷል።
እስክንድርና ባለቤቱ ከመጀመሪያዉ እሥራቸው እንደተፈቱ ስደትን መርጠዉ በዉጭ አገር የተመቻቸ ኑሮ መኖር ይችሉ እንደነበር የገለጸዉ የናዝሬት ድህረ ገጽ፣ አቶ እክስንድር ነጋ ከሕዝቡ ጋር በመኖር፣ የያዙትን ታላቅ መሳሪያ እርሱም ብእራቸዉን፣ በመጠቀም፣ ለሰላም፣ ለዲሞክራሲና ለሕግ የበላይነት ላደረጉትና ለሚያደርጉት ጥረት እዉቅና በመስጠት የ2010 ዓ.ም የአመቱ ሰዉ ብሎ ሰይሟቸዋል።
የናዝሬት ድህረ ገጽ ሙሉዉን ይዘት ለማንበት ከዚህ ይጫኑ !
http://nazret.com/blog/index.php/2011/12/26/ethiopia-eskinder-nega-is-nazret-com-s-person-of-the-year