ኢትዮጵያ በዊኪሊክስ ፋይሎች – ሼህ መሐመድ አል-አሙዲ
(ሊያነቡት የሚገባ!) – ክፍል 3
አቢይ አፈወርቅ
መሐመድ አል-አሙዲ (ሼህ)
የዛሬው ምጥን ፍተሻችን ትኩረት መሀመድ ሁሴን አሊ አል-አሙዲ ናቸው። እኝህ ሰው ባለፉት 20 ዓመታት ምናልባትም እጅግ አወዛጋቢ ሆነው ከቆዩ ሚና ያላቸው ጥቂት ሰዎች መሀል በአይነታነት መጠቀስ የሚችሉ ሰው ናቸው። በኢንቨስትመንቱ መስክ ወደፊት ከምንፈትሸው በትግራይ ህዝብ ስም በጥቂት የወያኔ ሹማምንት ከሚሽከረከረው ከኢፈርት ጋር ገዝፈው መውጣታቸው ይታወቃል። ከገዥዎቻችን ጋር ባላቸው የጠበቀ ትስስርም በተለያዩ ጊዜያት ስለፈጸሟቸው አጠያያቂ ተግባራት በህዝቡ መሀል በስፋት መነጋገሪያ ነበሩ። በፖለቲካው፣ በሰብአዊ መብቱና በኢንቫይሮመንት ዙሪያም እጃቸውን ምን ያህል እንዳስገቡ እነሆ መረጃዎች እየወጡ ናቸው።