የሁለቱ ‹‹ኢህአፓ››ዎች ጉራማይሌ ወግ (በረከት ስምኦን እና ብርሃኑ ነጋ)

ተመስገን ደሳለኝ

ከኢህአፓ ወደ ኢኮፓ፤ ከኢኮፓ ወደ ኢህዴን፤ ከኢህዴን ወደ ብአዴን… እነዚህ ሁሉ የዛሬው እንግዳችን የፖለቲካ ዝውውሮች ናቸው። መቼም ‹‹በዚህ ትውልድ›› ዝውውር ተፈፀመ ወይም ተዘዋወረ ከተባለ ከማንችስተር ዩናይትድ ወደ ሪይል ማድሪድ፤ አሊያም ከአርሰናል ወደ ባርሴሎና ነው። ‹‹በያ ትውልድ›› ደግሞ ከአንዱ ፓርቲ ወደ ሌላው ፓርቲ፤ ከሶሻሊዝም ወደ ካፒታሊዝም፤ ከኢምፔሪያሊዝም ወደ ኮሚኒዝም፤ ከአልባኒያኒዝም ወደ ማሌሊትዝም፤ ከማሌሊትዝም ወደ አብዮታዊ ዲሞክራቲሲዝም… ሲሆን ይሄ አይነቱ ዝውውር ‹‹የብልህ›› ስልት ተደርጎ ከመወሰዱም ባሻገር ለተዘዋዋሪዎቹ ጫማ ከመቀየር የቀለለ ነበር።