ሃሰተኛ – ብርቱ ወንጀለኛ!!!
ከግንቦት 7 የተሰጠ መግለጫ ታህሳስ 8 2004 ሰለ ሃሰት – በተለይም በሃሰት ስለመመስክር – አባቶቻችንና እናቶቻችን ያቆዩልን በርካታ ሥነ-ቃሎች አሉን። አንዱ በአርዕስትነት የተጠቀምንበት “ሃሰተኛ፤ ብርቱ ወንጀለኛ!” የሚለው ነው። ለራሳቸው፣ ለአገራቸውና ለወገናቸው ነፃነት ሲሉ የተቃውሞ ድምጽ ባሰሙ ወገኖቻችን ላይ የመለስ ዜናዊ ዘረኛ አገዛዝ በህግ ሽፋን የሚያደርሰው በደል በዝቶ ሕዝብ መሸከም ከሚችለው በላይ ሆኗል። ወገኖቻችን በዘረኞች መደብደባቸው፣ […]