በደሴ ከተማ 11 ቤቶች ተቃጠሉ
ሕዝብ እና ፌደራል ፖሊስ ተፋጠዋል
Ethiopia Zare (ማክሰኞ ታህሳስ 17 ቀን 2004 ዓ.ም. December 27, 2011)፦ በደሴ ከተማ ልዩ ስሙ አራዳ ገበያ በመባል የሚታወቀው ቦታ 11 ቤቶች ተቃጥለው ነዋሪዎች በድጋሚ በእሳት የጋዩ ቤቶቻቸውን ለመስራት ሲሞክሩ በስፍራው የደረሱ የፌደራል ፖሊሶች ቤቶቹ እንዳይሰሩ በመከልከላቸው ምክንያት ህዝብና የፌደራል ፖሊስ መፋጠጣቸውን ከስፍራው የደረሰን መረጃ ጠቆመ።