በተከራይ አከራዮች ላይ የወጣው መመርያ አፈጻጸም ወጥነት የለውም ተባለ

–    የአንዳንድ ወረዳዎች ኃላፊዎች የተከራይ አከራዮችን እያደራደሩ ነው

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የዲዛይንና ግንባታ አስተዳደር ልማት ቢሮ፣ በንግድ ቤቶችና ወደ ንግድ ቤትነት በተቀየሩ የመኖሪያ ቤቶች ላይ የተፈጠሩ ችግሮችን ለማስወገድ በሚል የወጣውና ከጥቅምት 17 ቀን 2004 ዓ.ም. ተግባራዊ መሆን የጀመረው መመርያ፣ አፈጻጸሙ ወጥነት እንደሌለው ነዋሪዎች እየገለጹ ነው፡፡