በቅድሚያ እንኳን ለዘመን መለወጫው አዲስ ዓመት አደረሳችሁ! መጪው ዘመን መብላትን አስበን ሳይሆን እህል በልተን የምንጠግብበት፤ መዳንን ተመኝተን ሳይሆን ታክመን የምንድንበት፤ከሰቀቀን ኑሮ ተላቀን እፎይ የምንልበት፤ የጎሪጥ ከመተያየት ይልቅ ተሳስበን የምንወያይበት፤በፍራቻ ሳይሆን በመምረጥ የምንኖርበት ዘመን እንዲሆንልን እመኛለሁ፡፡
ሃገራችን በየወቅቱ ከሚጋረጥባት እጦት ተገላግላ ራሷን የምትችልበት፤የሚሸሽባት ሳትሆን የምንሰባሰብባት፤ የምናፍርባት ሳትሆን የምንኮራባት ኢትዮጵያ እንድትሆን ሁላችንም ለሃገራችን እንደ የአቅማችን እንጣር፡፡ ለዚህ ደግሞ […]

ፍኖት — ቋንቋ ምድን ነው? እንዴትስ ይበየናል? የሚሉትን መሠረታዊ ጥያቄዎች አንስተን መቃኘት አለብን፡፡ ቋንቋ ምንድን ነው? ለሚለው ጥያቄ መልሱ ቋንቋ የሰው ልጆች የመግባቢያ መሣሪያ ነው፡፡ ባንደበት ተቀናብሮ ካንድ ግለሰብ ወደ ሌላው ግለሰብ መልዕክት ይስተላለፍበታል፡፡ የግንኙነቱ ሁኔታም አንድ ዓይነት ልሣን (Linguistic) …

ኢትዮጵያውያንን ስለከፋፈለው የኢሕአዴግ የቋንቋ ፖለቲካ Read more »

የትኛው ጋዳፊ? አራት ኪሎ አካባቢ ቡና እየጠጣሁ ጋዜጣ እያነበብኩ እንዳለሁ አንድ ወጣት በኪራይ የሚነበብ ጋዜጦችን ይዞ ማንበብ ይጀምራል፡፡ ትንሽ እንዳነበበ ጋዜጣ አዟሪውን “አንተ! ጋዳፊ የት ገባ?” ሲል ይጠይቀዋል፡፡ ለጥያቄው ሳይሆን ለመልሱ በመጓጓት ሁላችንም ወደ ጋዜጣ አዟሪው ዐይኖቻችንን አፈጠጥን፡፡ አንዳዶች ደግሞ …

የአደባባይ ምስጢሮች – የትኛው ጋዳፊ? Read more »

ኢትዮጵያ ብሔራዊ አንድነት ፓርቲ ፕሬዘደንት የሆኑት አቶ ዘሪሁን ገ/እግዚአብሔር “እጅና እግራቸው ታስሮ ለሁለት ቀን ተሰቅለው ሲደበደቡ እንደነበር ለፍ/ቤትና ለቤተሰብ መግለጻቸውን” ልጃቸው ወ/ሪት ሊዲያ ዘሪሁን ለዝግጅት ክፍላችን ገለፀች። ወ/ሪት ሊዲያ አያይዛ «በአባቴ ላይ ሰብአዊነት የጐደለውና ኢ-ህገመንግሥታዊ የሆነ የጭካኔ ተግባር መፈፀሙ በአጅጉ …

እነ ውብሸት ታዬ ላይ ዘግናኝ ድብድባ ተካሄደባቸው Read more »

“የደላው ሙቅ ያኝካል” – የኑሮ ውድነቱ እንደቋያ እሳት ከዳር እዳር እየተንቦገቦገ ባለጊዜን ሳይጨምር ሕዝበ አዳምን ክፉኛ እየለበለበ በሚገኝበት በአሁኑ ሰዓት የኢንተርኔቱ ጦርነት አፈ ሙዙን በኦነግ፣ በኦብነግና በግንቦት 7 ላይ አነጣጥሮ የደላቸው በብዕር እየተተጋተጉ ናቸው፡፡ ሰው በወደደው ይቆርባልና እንደጠቅላይ ሚኒስትራችን አባባል …

ታይቶ ያልተወቀ የሰደድ እሳት በአዲስ አበባ Read more »

ከጌታቸው በጋሻው አርሊንግተን፣ ቨርጂኒያ ውስጥ፣ July 10, 2011 በተደረገው ስብሰባ ላይ ኦነግን አስመልክቶ ባደረግኩት ንግግር ዙሪያ ምስጋናና ማበረታቻ ብቻ ሳይሆኑ ከተራ ስድቦች አንስቶ እስከ መሰረታዊ ብሄራዊና አገራዊ የደህንነት ጥያቄዎች ድረስ ቀርበውልኛል። ይህ ንግግሬ ይህን ያህል ሰዎችን ለማነጋገር በመቻሉና የዘር ድርጅቶች …

ከኦነግና ሌሎች የዘር ድርጅቶች ጋር መነጋገርና መተባበር ለምን ያስፈልጋል? Read more »

ከሲሳይ አጌና “አባባ ታምራት፣አርቲስቶቻችን እና የህዳሴው ግድብ” በሚል ርዕስ ባለፈው ባቀርብኩት ጽሁፍ ላይ ያልተቋጨ እና በይደር የተውነው ነገር መኖሩ ዕውነት ነው፤በዚያ ጽሁፍ ላይ የሰዎቹ ስም ባለመጠቀሱ ቅር ያላቸው፣ልብ ወለድም የመሰላቸው አጋጥመውኛል፤ በኤሌክትሮኒክስ የመልዕክት ሳጥኔ ውስጥ:: እንከሳለን ያሉም ጽፈውልኛል ፤ክሱ ሄግ …

በባንክ ዕዳ ሲፈለግ – የሸፈተው “ታጋይ” Read more »

ይብራለም አማንኤል “አይ አንቺ ቤተ ክርስቲያን፣ ስንቱ ይቀበርብሻል” ነበር ተረቱ:: ታዲያ እንደማስታውሰው ይሄ የተባለው በሀገራችን በኢትዮጵያ በየባላገሩ በከተማውም ጭምር ቤተክርስቲያን የማምለኪያም የመቀበሪያም ቦታ ስለሆነች የማታ ማታ የክፉውም የደጉም፣ የወንበዴውም የሕግ አክባሪውም፣ የስስታሙም የለጋሱም፣ የነፍሰ ገዳዩም የመሀሪውም፣ የጎጠኛውም የኢትዮጵያዊውም ገብአተ መሬቱ …

አይ አንቺ ቤተክርስቲያን! Read more »

በታምሩ ጽጌ | ሪፖርተር በሽብርተኝነት ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር ከዋሉት ዘጠኝ ተጠርጣሪዎች መካከል፣ የአውራምባ ታይምስ ጋዜጣ ምክትል ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬን ጨምሮ ስድስት ተጠርጣሪዎች፣ ከትናንት በስቲያ ፍርድ ቤት ቀርበው ተጨማሪ ጊዜ ቀጠሮ ተጠየቀባቸው፡፡ በፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ …

ወያኔ በሽብርተኝነት የከሰሳቸው 6 ተጠርጣሪዎች ፍርድ ቤት ቀረቡ Read more »

ቀን፦ July 17th ,2011 ሰዓት፦ 1፡30 pm ቦታ፦ Washington Marriott፣ 1221, 22nd Street NW Washington, DC 20037 ዶ/ር አሰፋ ነጋሽ እና ዶ/ር አክሎግ ቢራራ እንዲሁም ታዋቂ ኢትዮጵያውያን ምሁራን የሚገኙበት የኢትዮጵያ ወቅታዊ ችግር ግንዛቤና የጥቂት ምርጦች አስተሳሰብ ካለው ተጨባጭ ሁኔታ አንጻር፣ …

ታላቅ የስብሰባ ጥሪ በዋሽንግጥን ዲሲ Read more »

ክንፉ አሰፋ ጁላይ 1፣ አርብ ምሽት አትላንታ ጆርጂያ አውሮፕላን ማረፊያ እንደደረስኩ እንደቅድሞው ብዙ አበሻ ሲርመሰመስ አላየሁም። የአበሻው ትርምስ በ2005 አትላንታ ላይ ተመሳሳይ ፌስቲቫል በተዘጋጀ ግዜ ከነበረው እጅግ ቀዝቀዝ ብሎ ነበር። ይልቁንም ዝግጅቱ አልቆ አትላንታን ስንስነባበት አውሮፕላን ማረፍያው በአበሻ ተጨናንቆ አሜሪካ …

የአትላንታው ሙቀት Read more »

[በዳዊት ከበደ – አትላንታ] ሁሉንም ትዝብቶች አልጻፍንም። ሆኖም ለፌዴሬሽኑ ይጠቅማሉ የምንላቸውን መሰረታዊ ስህተቶችን ለማየት ሞክረናል። አላማችንም ፌዴሬሽኑ ስህተቶቹን እንዲያርም ለማድረግ ስለሆነ፤ ችግሮቹንና መፍትሄ ያልናቸውን ሃሳቦች አቅርበናል። አስተያየታችን በግለሰቦች ላይ ያነጣጠረ ባለመሆኑ ስህተት ሰርተዋል ያልናቸውን ሰዎች ስም እዚህ ላይ አልጠቀስንም። በቅን …

በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ ስፖርት ፌዴሬሽንና አስር ያህል ትዝብቶች Read more »

ብዙዎች አስቦክተውን፡ ብዙዎችም አስጠንቅቀውን ነበር አንዳንዶቹ፡ “አይ አይሳካላችሁም፡ እንደው ነው የምትደክሙት” ብለው አስፈራርተውን ነበር። ገሚሶቹም፡ “ባዶ ሜዳ ታቅፋችሁ ትቀራላችሁ” ብለው ፈልፍለውብን ነበር። የተቀሩት ግን “በርቱ፡ እኛም እንመጣለን” አሉን። እነሆ ገሚሱን ታቅፈን፡ ገሚሱንም አዝለን ወደፊት ገሰገስን፤ የዛሬ አስር ወር በሀሳብ ደረጃ፡ …

የኢትዮጵያዊነት ፌስቲቫል የግል ዘገባ – በልጅ ተክሌ Read more »

የኢትዮጵያዊነት ውርስና ቅርስ ማህበረሰብ በሰሜን አሜሪካ ያዘጋጀው የመሪያው አመታዊ ፌስቲቫሌ አርብ ጁሊይ 1 ቀን በዋሽንግተን ከተማ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ ተከፈተ። አያሌ ኢትዮጵያዊያን በጆርጅታውን ዩኒቨርስቲ፡ አርት ጋለሪ የተገኙት ከዝግጅቱ ከመጀመሩ ቀደም ብለው ሲሆን፡ ለሶስት ቀናት የሚካሄደው ይህ ፌስቲቫል …

የኢትዮጵያዊነት ውርስና ቅርስ ፌስቲቫል በደማቅ ሁኔታ ተከፈተ Read more »

የኢትዮጵያዊነት ውርስና ቅርስ ፌስቲቫሌ በዯማቅ ሁኔታ ተከፈተ አርብ ጁሊይ 1፡ 2011 ዓ.ም. ዋሽንግተን ዱሲ፡ ተክሇሚካኤሌ አበበ የኢትዮጵያዊነት ውርስና ቅርስ ማህበረሰብእ በሰሜን አሜሪካ ያዘጋጀው የመጀመሪያው አመታዊ ፌስቲቫሌ፡ ዛሬ አርብ፡ ጁሊይ 1 ቀን በዋሽንግተን ከተማ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን በተገኙበት በዯማቅ ሁኔታ ተከፈተ። …

የኢትዮጵያ ፌስቲቫል በዋሽንግተን ዲሲ በደማቅ ሁኔታ ተከፈተ Read more »

ሲሳይ አጌና ከ2003 አዲስ ዓመት መግቢያ ጀምሮ ጥቂት የማይባሉ የኢትዮጵያ የኪነጥበብ ባለሙያዎች ከሕዝብ ፍላጎት በተቃራኒ ቆመው በኢሕአዴግ የቅስቀሳ ስራ ተጠምደው መገኘታቸው ብዙዎችን ግር እያሰኘ ነው፤ ሕወሐት/ኢሕዴግ ዓለም የመዘገበውን የአዲስ አበባውን ጭፍጨፋ ሳይፈጽም፣ሕዝቡን በዚህ መጠን ሳያስርብ በአንጻራዊ ደረጃ ሕዝብ በልቶ በሚያድርበት …

“አባባ ታምራት” – አርቲስቶቻችን እና የህዳሴ ግድብ Read more »

ጦርነት ተቀሰቀሰ…!! ስደተኞች UNHCR በር ላይ ተቀመጡ።፡ነገሩ እየተካረረ መግባባት ጠፍቶ ጦርነት በተቀሰቀሰባት የመን 4 ኢትዮጵያዊያን ሰለባ ሆኑ::ሰነዓ ከተማ ውስጥ አሳባ የሚባለው አካባቢ ከሼህ ሳዲቅ ጋር ሲደረግ የነበረው ውጊያ ዛሬ ጋብ ብሎ ቢውልም ክሰነዓ ውጭ ያለው ሁኔታ አልረገብም የሚል አሉ::እነዚህ 4 …

በየመን 4 ኢትዮጵያዊያን ሞቱ Read more »

ግንቦት 20 በመጣ ቁጥር ወያኔ/ኢህአዴግ በሕዝብ ፍቅር መጥገቡን በተለያየ መንገድ አስመስሎ በመዋሸት በሃገር ውስጥ ያሉትን ሞኞች፤ በውጭ ያሉትን በርቀታቸው ከለላነት፤ ዓለም አቀፉን ሕብረተሰብ በማያውቀውና በሃገር ውስጥ ያሉትም ኤምባሲዎች እያወቁ በሚሸፍጡት እውነታ በማለባበስ ላይ ከተሰማራ ከረመ፡፡ የዘንድሮው የአባይ መገደብ በሚያስደንቅ ፍጥነት …

ወያኔ ግንቦት 20 (May 28) ሰልፍ ለማዘጋጅት እይተሯሯጠ ይገኛል Read more »

ከትላንት ሌሊት ጀምሮ በአብዛኛው የምዕራብ ኢትዮጵያ ከተሞች፥ በተለየም አሶሳ፥ መተከልና በአዊ ዞን አካባቢ ያሉ ቦታዎች ሁሉ ስልክና መብራት ተቋርጧል። አምቦና ነቀምቴ መብራት አልፎ አልፎ በመስራት ላይ የገኛል፥ ግን የሞባይልና የቤት ስልኮቹ ሁሉ አግልግሎት አቁመዋል። ይቀጥላል (እዚህ ላይ ይጫኑ)

194 ሰዎች የተገኙበት የመክፈቻና፡ የትውውቅ ዝግጅት በተሳካ ሁኔታ ተካሄደ ከትኬት ሽያጭና ከስፖንሰርሺፕ ባንድ ምሽት 27 ሺህ 300 ብር ተሰብስቧል ንፋስ የቀላቀለ ሀይለኛ ዝናብ ሳይጠበቅ መጥቶ የተወሰኑ ትኬት የገዙ ሰዎችን ቢያስቀራቸውም፡ ንፋስና ዝናብ ሳይበግራቸው በወጡና የኢትዮጵያዊነት ፍቅር በሚያቃጥላቸው 194 ከዲሲና አካባቢው …

በዋሽንግተን ዲሲ፡ የኢትዮጵያዊነት መንፈስ አሸንፎ ዋለ Read more »

ዛሬ ሚያዚያ 27/2003 ዓ/ም ከ5,000 በላይ የሆኑ ቤቶች በመቀሌ ከተማ በግሬደርና በዶዘር እየፈረሱ ነው፡፡ ማይ አንበሳና ገፊሕ ገረብ በመባል የሚታወቁ እነዚህ መንደሮች በመቀሌ ከተማ በስተምእራብ የሚገኙ ሲሆን አብዛኞቹ ከኤርትራ ተፈናቅለው የመጡ ዜጎች የሚኖሩባቸው ናቸው፡፡ እነዚህ ዜጎች ሁለቱ መንግስታት በመጣላታቸው ምክንያትና …

በመቀሌ “የአርበኞች ቀን” ቤት በማፍረስ ተከበረ፣ 15 ሺህ ነዋሪዎች ያለመጠለያ ተበተኑ Read more »

ባለፈው ጊዜ በመቀሌ ከተማ መንግስት ቤታቸው አንዲፈርስ በወሰኑ ምክንያት ሰልፍ ወጥተው እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡ በወቅቱ ሰልፈኞቹ ከክልሉ ፕሬዳንት ጋር በጉዳዩ ዙሪያ ለመነጋገር ተወካዮቻቸው እንዲመርጡ ተደርጎ ለጊዜው ሰልፉ እንዲበተን ተደርጎ ነበር፡፡ ከዚያ በኋላ የመንግስት አካላት ከህዝቡ ጋር ለመነጋገር ቀጠሮ ከተያዘ ኋላ …

በመቀሌ “ቤታችንን አናስፈርስም” ያሉ ሰልፎኞች ድብድባና አስራት ተፈጸመ Read more »

ወያኔ/ኢህአዲግ ታላቁ «የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ»ን ለመገንባት በሚል እያካሄደ ያለዉ የቦንድ ሽያጭ የዜጎችን ሙሉ ፍላጎትና ተሳትፎ የያዘ ለማስመሰል በካድሬዎቹ አማካኘነት የተለያዩ ዘዴዎችን እየተጠቀመ መሆኑ ታወቀ። ጉዳዩን አስመልክቶ አስተያየታቸዉን የሰጡን በመንግስት መስርያቤቶች የሚሰሩ ሰራተኞች እንዳስታወቁት በየመስርያቤቱ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ለመነጋገር በሚል ሰራተኞች …

ወያኔ የቦንድ ሽያጩን በካድሬዎቹ አማካኝነት እያጧጧፈዉ ነዉ Read more »

ከመስፍን አማን መቼም የአባይን መገደብ የሚቃወም ሃገሩን የሚወድ ኢትዮጵያዊ ያለ አይመስለኝም። ለሃገራችን መልካም እናስባለን የሚሉ አገር ወዳድ ሀይሎች፡ በጉዳዩ ላይ ያላቸው ተቆርቋሪነት ከወያኔ መሪዎች ቢበልጥ እንጂ የሚያንስ አይደለም። ሁላችንም ቀን ወጥቶ በጋራና በመግባባት ሃገራችን የሃብቷ ተጠቃሚ ሆና ከማየት የበለጠ ሌላ …

አባይና የሰሞኑ ግርግር Read more »

በኢትዮጵያ ውስጥ ለ20 አመታት የዘለቀውን የወያኔ/ኢህአዴግን አገዛዝ በመቃወም “በቃ” በሚል መሪ ቃል በቱኒዚያ፣ በግብጽና በሌሎችም ሀገራት እንደተከሰተው አይነት ህዝባዊ አመጽ አካሂዶ ኢትዮጵያንም ነጻ ለማውጣት እንቅስቃሴ መጀመሩ ይታወቃል፡፡ ይህን እንቅስቃሴ ተከትሎ ስለ ንቅናቄው መራ የሚሰጡ በራሪ ወረቀቶችን በስፋት ከመበተን ባሻገር በመዲናዋ …

የወያኔ ካድሬዎች የ«በቃ!»ን መፈክር ለማጥፋት እየተሯሯጡ ነው Read more »

የኢትየጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን ቀኖና በጣሰ አካሄድ የፓትሪያርክነት ሹመት አግኝተዋል ተብለው ለአመታት ሲወቀሱና ከምዕመኑም ተገቢውን ክብር ሳያገኙ እስካሁን የቆዩት አባ ገብረመድህን (የቀድሞው አቡነ ጳውሎስ) በያዝነው ሳምንት የ30 ሚሊዮን ብር ቦንድ እንደሚገዙ አስታውቀዋል፡፡ አባ ገብረመድህን እገዛለሁ ያሉት ኢህአዴግ ከህዝቡ እየመጣ ያለውን …

አባ ገብረመድህን የሰላሳ ሚሊዮን ብር ቦንድ ሊገዙ ነው Read more »

ከታደሰ ብሩ ወያኔ የኢትዮጵያን ህዝብ “ከስግብግብ” ነጋዴዎች ለመታደግ ሲል “መሠረታዊ” ባላቸው ጥቂት የሸቀጥ ዓይነቶች ላይ የዋጋ ተመን ጣለ። ለውይይታችን እንዲመቸን ስኳርና ዘይት ላይ ብቻ እናትኩር። የሸቀጦች ዋጋ እያሻቀበ፤ ሸማችም እተማረረ መጣ። ኑሮ ከዳገት መውጣት የከበደ ፈተና ሆነ። “ሳይቲስቶቹ” የወያኔ መኳንንት …

ጉልበት ገበያ ውስጥ ከገባ፤ “ዘረፋ” እንጂ “ገበያ” አይባልም Read more »

ገለል በልና ገለል አርጋቸው ወደመጡበት ወዳገራቸው! ብለን እይዘመርን አፕሪል 16 ቀን 2011ን በጉጉት እየጠበቅነው ነው። ቦታው ኢምፔሪያል ኮሌጅ ቀኑ አፕሪል 16 ቀን 2011 (16th April 2011) ሰዓት ከቀኑ 8 ሰዓት እስከ ምሽቱ 1 ሰዓት ተደፍረናል ጎበዝ! ቤታችን ድረስ መጥተዋል። እንግዲህ …

ሎንደንም ተዘጋጅተንላቸዋል Read more »

ከይነጋል በላቸው ከጥቂት ቀናት በፊት አመፀኛው የኮትዲቩዋሩ ሎራን ባግቦ ሃያ በመቶው የሀገሪቱ ከተሞችና ክልሎች በሕጋዊው ተመራጭ ዕጅ ገብተው እርሱና ጥቂት ግብረ አበሮቹ በራሱ በባግቦ መኖሪያ ቤትና በተወሰኑ አካባቢዎች ተወስነው በነበረበት ወቅት በተወካዩ አማካይነት አንድ መልዕክት አስተላልፎ ነበር – አላሳን ዋታራ …

አምባገነኖች ከአንድ ባሕር(ይ) ይቀዳሉ Read more »

ገዢው ፓርቲ ወያኔ የተቃውሞ ይዘት ያላቸው መፅሐፍትን በተለይ ከአንደኛና ከሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ቤተመፅሐፍት ውስጥ ሰብስቦ በማውጣት ላይ መሆኑን ምንጮቻችን ገለፁ፡፡ ይኸው የወያኔ ድርጊት የወጣቶች ማዕከላት ተብለው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተከፈቱ ማዕከላት ቤተመፅሐፍት ውስጥም ተጠናክሮ መቀጠሉ ታውቋል፡፡ እንደምንጮቻችን ገለፃ ገዢው ፓርቲ …

ወያኔ የተቃውሞ ይዘት ያላቸውን መፅሐፍት ከቤተ-መፅሐፍት ማውጣት ጀመረ Read more »

ከትላንት በስቲያ በአንድ ወር ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ በነዳጅ ዋጋ ላይ የተደረገው ጭማሪ በተለይም የምግብ ሸቀጦች ዋጋ ከፍ እንዲል በማድረጉ ነጋዴዎችን ሸማቾች እየተማረሩ ነው፡፡ የዋጋ ማስተካከያው በአንድ ሊትር ቤንዚን ላይ አራት ብር ገደማ የጨመረ መሆኑን ተከትሎ የከተማ ታክሲና …

የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ነጋዴውንና ሸማቹን እያማረረ ነው Read more »

“በቃ” በሚል መሪ ቃል በፌስ ቡክ ድረ ገጽ ላይ ግንቦት 20 2003 ዓ.ም በኢትዮጵያ ህዝባዊ አመጽ ለማካሄድ እንቅስቃሴ መደረግ ከጀመረ ወዲህ በርካታ ተግባራዊ እንቅስቃሴዎች እየተደረገ መሆኑ ተስተውሏል፡፡ ከሚያዝያ 1 2003 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ አበባና አካባቢዋ “የኢትዮጵያ ወጣቶች ንቅናቄ ለዴሞክራሲያዊ ለውጥ” …

የ”በቃ!” በራሪ ወረቀቶች አዲስ አበባን እያጥለቀለቋት ነው Read more »

«ሰውን ካልናቁ አጥሩን አይነቀንቁ» ወያኔ በሰሜን አሜሪካ ጉብኝት ካደረገባቸው ከተማዎች አንዱ ሎስ አንግጀለስ ነው። በሎስ አንጀለስ ከተማ የሚገኙ አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ወያኔ ወደ አሜሪካ ሊመጣ ነው ተብሎ ወሬው ከተሰማበት ጊዜ ጀምረው በመጣበት መንገድ አሳፍሮ ለመመለስ ከፍተኛ ዝግጅት ሲያደርጉ ነበር የሰነበቱት። …

የወያኔ ጉብኝት በሎስ አንጀለስና ውጤቱ Read more »

የዘመን ባንክ የቦርድ ሊቀመንበር የነበሩት አቶ ኤርምያስ አመልጋ ከቦታቸው እንዲነሱ መደረጋቸውን ተከትሎ በምትካቸው ሌላ ሰው ለማስመረጥ የተደረገው ጥረት ሳይሳካ ቀረ፡፡ የብሔራዊ ባንክ ተወካዮች በመሩትና ያለፈው ቅዳሜ በሚሊኒየም አዳራሽ በተደረገው ስብሰባ ወቅት የዘመን ባንክ ጠቅላላ ጉባኤ አባላት ሌላ ሰው ከመምረጣቸው አስቀድሞ …

ዘመን ባንክ አዲስ የቦርድ ሊቀመንበር ሊመርጥ አልቻለም Read more »

ያለፈው እሁድ ተግባራዊ የተደረገው የነዳጅ ጭማሪ ህብረተሰቡን ከመቼውም ጊዜ በበለጠ እያማረረ ነው፡፡ ይህ የሆነውም ከዚህ በፊት በነዳጅ ዋጋ መጨመር ምክንያት ይደረጉ ከነበሩት የትራንስፖርት ዋጋ ጭማሪዎች በሙሉ የአሁኑ የበዛ በመሆኑ ምክንያት እንደሆነ ታውቋል፡፡ በአሁኑ የዋጋ ጭማሪ 1፡15 የነበረው የጉዞ ታሪፍ ወደ …

የትራንስፖርት ዋጋ ጭማሪ ህዝብ እያማረረ ነው Read more »

ከወንድሙ መኰንን ለማጁ ቀጣፊ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሥቃይ መለስ ዜናው መጋቢት ፳፯ ቀን ፪ሺ፫ ፓርላማዬ በሚለው በረት ውስጥ ለኮለኮላቸው ድብኝት አሻንጉሊቶቹ ሲናገር፣ ድርብ ቀመር የታየበት ዕድገት አሳይተናል ብሎ ቀባጠረ። አቤት ውሸት! አቤት ውሸት! ሀቁ መሬት ላይ እንደሚታየው ከሆነ አብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ …

ቁምሳ Read more »

ምርጫ ቦርድ የ2002 ዓ.ም ምርጫን በተመለከተ ያዘጋጀውን የዳሰሳ ረቂቂ ሰነድ ተቃዋሚ ፓርቲዎች እንደማይቀበሉት አስታወቁ፡፡ ተቃዋሚ ፓርቲዎቹ ይህንን ያስታወቁት ባለፈው ቅዳሜ በምርጫ ቦርድ አዳራሽ በሰነዱ ላይ ከምርጫ ቦርድ ጋር ውይይት ባደረጉበት ወቅት ነው፡፡ ምርጫ ቦርድ በጠራው በዚሁ ስብሰባ ላይ የፓርቲዎቹ ተወካዮችን …

የምርጫ ቦርድ ጥናት ለገዢው ፓርቲ የወገነ መሆኑ ተነገረ Read more »

ከአቢይ ኢትዮጵያዊ ሥጋዊ ወመንፈሳዊ:: ሰለሞን ጠንባልኝ አህያ ሆንክልኝ? ከርፋልኝ በቁምህ ያ!ሞት:-እስኪስምህ:: በድብቅ እንዳንተ ስንት አለ የሞተ:: የገ ማ የቀረና ው ስጡ የጎረና:: አሉ የታወቁ በእኛ የተደበቁ:: ላይ ላዩን ሲታዩ ገጣጣ የሚ ያሳዩ:: አቦሬ አፋቸውን ከፍተው የማይዘጉ; እንደው ስላዜሙ ገዳይ የተጠጉ:: …

እንደዚህ ጠንባልኝ፤ ሰለሞን ተካልኝ Read more »

ከታደሰ ብሩ “የሚሌኒየሙን ግድብ ሕዝባዊ የልማት ሐውልት እናድርገው1!!” — የሪፓርተር ጋዜጣ ርዕሰ አንቀጽ ይህ ድንቅ ሃሳብ ነው። ብራቮ ሪፓርተር!!! ግን ለምን እስከነገ እንጠብቃለን? የሚሊኒየሙ ግድብ የልማት ሃውልታችን ነው!!!! ነው!!!! ነው!!!! ነው!!!! የሪፓርተር ጋዜጣ ታላቁ የሚሊኒየም ግድባችን የልማታችን ሃውልት እናድርገው በማለቱ …

ታላቁ የሚሊኒየም ግድብ – ላም አለኝ በሰማይ፤ ወተትዋን እማላይ! Read more »

ለአንድ ሃገር ልማት ከዜጐቿ በላይ የሚጨነቅ የለም፡፡ ሃገር ውስጥም ሆነ ውጭ ያሉ ሁሉ ጥረው ግረው ያገኙትን በሃገራቸው ግንባታና በራሳቸው ህይወት መሻሻል ላይ ቢያውሉት የበለጠ ይመኛሉ፡፡ ቁም ነገሩ ግን ይኸ መልካም ምኞታቸው ብቻ ሳይሆን ለእውቀት ለሃብትና ገንዘባቸው እንዲሁም ለራሳቸው ደህንነት አስተማማኝ …

የመሸበት መንገደኛ አንቀበልም! Read more »

ወያኔ ኢትዮጵያ አገራችንን በጎሳና በሐይማኖት ከፋፍሎን ለ20 ዓመታት በጉልበት እየገዛ ነው። ለመብታቸው የሚታገሉ ኢትዮጵያውያን ወደ እሥር ቤት እየተወረወሩና ለሞትና ለስደትም እየተዳረጉ ይገኛሉ። በየትም ዓለም ያልታየውን የኢኮኖሚ እድገት አሳይተናል፣ “14 በመቶ ኢኮኖሚያችን አድጋጓል” በማለት እየሸፈጠ 2.2 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን በእራብ እያለቁ ናቸው። …

በሳን ዲያጎና አካባቢዋ ለሚገኙ የኢትዮጵያውያን ሁሉ! Read more »

ኢትዮጵያውያን በሁሉም ቦታዎች በከፍተኛ ደረጃ በመንቀሳቀስ ላይ ናቸው። እኛም በምንያፖልስና- ሴንትፖል ከተማዎችና በአካባቢው የምንገኝ አገር-ወዳድ ኢትዮጵያውያን በከፍተኛ አገራዊ ስሜት ተነስተን ይህን ዓይን ያወጣ የወያኔ ዘመቻ ማጋለጥ አለብን። ለምን ብለን አንዴ ሕሊናችንን እንጠይቅ። ለናሙና ያህል ብንጠቅስ፤ አገራችን ን ኢትዮጵያ ዘረኛውና ፀረ-ኢ …

በምኒያፖሊስ-ሴንትፖል ከተማዎች ለምትኖሩ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያኖች በሙሉ Read more »

የወያኔ ከፍተኛ ባለስልጣናት በሎስ አንጀለስ ከተማ ህዝባዊ ስብሰባ ስለሚያድርጉ፣ የህዝባችን ስቃይና መከራ የሚሰማችሁ ኢትዮጵያውያን በነቂስ ወጥታችሁ በተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ተቃውሟችሁን አንድታሰሙ ጥሪ እናቀርባለን። ቀን April 10, 2011 ሰዓት 1 PM ቦታ Los Angeles Convention Center አዘጋጅ ኮሚቴው

በድሃው የኢትዮጵያ ሕዝብ ኑሮ ጠኔ የሚቀልደው የወያኔ አገዛዝ ኢኮኖሚያችን አድጎ ተትረፍርፏል፤ ለጎረቤቶቻችን መትረፍ እንችላለን፤ ከፍተኛ ልማት እያካሄድን ነው እያለ የተለመደውን አፍዝዝ አደንግዝና አሰልች ፕሮፓጋንዳውን በመንዛት ላይ ይገኛል። የቅርብ ጊዜ ትዝታ የሚሆነን፣ ፀረ-ኢትዮጵያው ወያኔ ትላንት በአደባባይ ያደረጋቸውን ፀረ-ኢትዮጵያ ቅስቀሳዎችና ንግግሮች ወደ …

በኮለምበስ ኦሃዮና አካባቢው ለምትገኙ አገር-ወዳድ ኢትዮጵያውያን በሙሉ Read more »

በሰሜን አፍሪካ ተጀምሮ በርካታ አምባገነን መንግስታትን በማስደንበር ላይ ያለው ህዝባዊ አመጽ በኢትዮጵያም ሊከሰት ይችላል በሚል ግምት የኢህአዴግ ባለስልጣናት በርካታ እርምጃዎችን ሲወስዱ ቆይተዋል፡፡ የመጀመሪያውና ውጤት አልባ የሆነው የማስቀየሻ ስልት “በመሰረታዊ የፍጆታ እቃዎች” ላይ የተደረገው የዋጋ ተመን ሲሆን የኤርትራን መንግስት በጦርነት ከስልጣን …

“አቶ መለስ ስለደነፉ የሚቀነስም ሆነ የሚጨመር ነገር የለንም” – አንዱአለም አራጌ Read more »

በሀገራችን ህልውናና በወገኖቻችን ሕይወት ላይ ከወራሪ ጠላት ባልተናነስ መልኩ ከፍተኛ ጉዳት ባደረሰውና አሁንም በማድረስ ላይ ያለው መለስ ዜናዊና ግብረ አበሮቹ ሀገር ቤት የሚያካሂዱትን የመከፋፈል ሴራ እነሆ በሎስ አንጀለስና አካባቢዋ በምንኖር ኢትዮጵያውያን ላይ ለመዝራት አፕሪል 10 ስብሰባ ጠርተዋል። ጥሪያቸውንም በከተማችን ለዚሁ …

በሎስ አንጀለስ ሊካሄድ የታቀደውን የወያኔ ሴራ እናክሽፍ Read more »