የኢትዮጵያ ፌስቲቫል በዋሽንግተን ዲሲ በደማቅ ሁኔታ ተከፈተ

የኢትዮጵያዊነት ውርስና ቅርስ ፌስቲቫሌ በዯማቅ ሁኔታ ተከፈተ
አርብ ጁሊይ 1፡ 2011 ዓ.ም. ዋሽንግተን ዱሲ፡ ተክሇሚካኤሌ አበበ
የኢትዮጵያዊነት ውርስና ቅርስ ማህበረሰብእ በሰሜን አሜሪካ ያዘጋጀው የመጀመሪያው አመታዊ ፌስቲቫሌ፡ ዛሬ አርብ፡
ጁሊይ 1 ቀን በዋሽንግተን ከተማ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን በተገኙበት በዯማቅ ሁኔታ ተከፈተ።
አያላ ኢትዮጵያዊያን በጆርጅታውን ዩኒቨርስቲ፡ አርት ጋሇሪ የተገኙት ከዝግጅቱ መጀመር ቀዯም ብሇው ሲሆን፡ ሇሶስት
ቀናት የሚካሄዯው ይህ ፌስቲቫሌ የተከፈተው፡ መክብብና አምሳሌ የተሰኙ ሁሇት ኢትዮጵያዊያን ሰዓሉያን ባቀረቧቸው
አስዯናቂና ማራኪ የስእሌ ስራዎች፡ እንዱሁም በአርበኞች ፎቶግራፎች ነው።
በመቀጠሌም፡ በጆርጅ ታውን ዩኒቨርስቲ የአርት ፕሮፌሰር የሆኑት ፐሮፍሰር ክሉፎርድ የመክፈቻና ንግግር አድርገዋሌ።
እንዱሁም የኢትዮጵያዊነት ውርስና ቅርስ ማህበረሰብ ሉቀመንበር አቶ ሼክስፒር ፈይሳም የእንኳን ዯህና መጣችሁ ንግግር
አሰምተው፡ ሇረጅም ግዜ ከኢትዮጵያዊያን አይን ተሰውራ የቆየችውና የዚህ ፌስቲቫሌ የክብር እንግዲ፡ የቀድሞዋ የፖሇቲካ
እስረኛ ወ/ት ብርቱካን ሚዯቅሳ በመክፈቻው ዝግጅት ወዯ አዲራሹ መግባቷ፡ በተነገረ ግዜ ከፍተኛና የማያቋርጥ ጭብጨባ
ተሰምቷሌ።
የመጻህፍት ፍርሚያ፡ የግጥም ንባቦች፡ የታሪክ ማስታወሻዎችና የሙዚቃ ቅምሻዎች በታዋቂ ገጣምያን የቀረቡ ሲሆን፡
አርቲስት ማርታ ቀጸሊ፡ አርቲስት መኮንን፡ ኢትዮጵያዊው የአሇምአቀፍ ኦልምፒክ ኮሚቴ የቀድሞ ባሇስሌጣንና የፒያሳ ሌጅ
መጽሀፍ ዯራሲ፡ አቶ ፍቅሩ ኪዲኔም አጭር ንግግር አድርገዋሌ። ዝግጅቱን ሇመከታተሌ የመጣው ሰው ከአዲራሹ ጋር
ባሇመመጣጠኑ የተነሳ፡ ብዙ ሰዎች ከውጭ እንዱቆሙ የተገዯደ ሲሆን፡ ይሄንን የተመሇከተውና በዚህ ዝግጅት የተዯሰተው
የጥበብ ባሇሙያና ጋዜጠኛ አበበ በሇው፡ “ይኼ ዝግጅት በተጠናከረ ሁኔታ ቀጽል፡ እንዯውም አንድ ዋና መንገድ አስዘግተን
የኢትዮጵያ ቀን መከበር አሇበት” ብሎሌ።
በዚህ የመክፈቻ ዝግጅት ሊይ ብዙ ኢትዮጵያዊነትን ያስታወሱ ስሜት ቀስቃሽ ስራዎች ቀርበዋሌ።
የፌስቲቫሌ ዝግጅቱ ነገ ቅዲሜ ጁሊይ 2 የሚቀጥሌ ሲሆን፡ ጠዋቱ ከ9 ሰዓት ጀምሮ የእግር ኳስ ጨዋታዎች ከአትሊንታ፡
ከቨርጂኒያ፡ ከባሌቲሞርና፡ ከዱሲ በተወጣጡ ብድኖች ይካሄዲለ። ከሰዓት በኋሊ የቡና ስነስርአት፡ የሌጆች አምባ ዝግጅት፡
እንዱሁም በዋንኛነት የቅኝት የባህሌ ሙዚቃ ቡድን ባህሊዊ የሙዚቃ ስራዎቹን ያቀርባሌ። የመካከሇኛና አጭር ርቀት የሩጫ
ውድድርም ይካሄዲሌ። ይኸው የእግር ኳስ ጨዋታውና የሩጫ ውድድሩ እሁድም እሇት ቀጥል ውል፡ ታዋቂዎቹ
ድምጻዊያን ብርሀኑ ተዘራ፡ አበባ ዯሳሇኝ፡ እና መስፍን ዘበርጋ በሚገኙበት እሁድ እሁድ ጁሊይ 3 ቀን በሚዯረግ የሙዚቃ
ኮንሰርት ይዘጋሌ። በሁሇቱ ቀናት ዝግጅት ነጻ የመኪና ፓርኪንግ እንዲሇና፡ ሇእግረኞችም ከፎጊ ቦተም ድረስ ወዯ ስቴዱየሙ
የሚያመሊሌስ የትራንስፖርት አገሌግልት እንዯተሰናዲ የዝግጅቱ አስተባባሪዎች ተናግረዋሌ። የዝግጅቱን ሂዯት እየተከታተሌን
እንዘግብሊችኋሇን።
የኢትዮጵያዊነት ውርስና ቅርስ ድርጅት በሰሜን አሜሪካ፡ የኢትዮጵያዊነትን ውርስ ሇማስጠበቅና ኢትዮጵያዊነትን ሇመጠበቅ
የተቋቋመ መንግስታዊ ያሌሆንና ሇትርፍ ያሌተቋቋመ፡ ድርጅት ነው።