የወያኔ ጉብኝት በሎስ አንጀለስና ውጤቱ

«ሰውን ካልናቁ አጥሩን አይነቀንቁ»

ወያኔ በሰሜን አሜሪካ ጉብኝት ካደረገባቸው ከተማዎች አንዱ ሎስ አንግጀለስ ነው። በሎስ አንጀለስ ከተማ የሚገኙ አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ወያኔ ወደ አሜሪካ ሊመጣ ነው ተብሎ ወሬው ከተሰማበት ጊዜ ጀምረው በመጣበት መንገድ አሳፍሮ ለመመለስ ከፍተኛ ዝግጅት ሲያደርጉ ነበር የሰነበቱት።

የወያኔ ተወካዮች አርከበ እቁባይ፣ አንድ ከሱማሌ ክልል፣ አንድ ካማራው ክልል፣ ሲሆኑ የሎስ አንጀለሱ አምባሳደርም ነበር።

የተሳታፊው ብዛት፣ 150-200

ከዚህ ውስጥ አብዛኛው የሚሉትን እንስማ ብሎ የመጣና ኢትዮጵያ ውስጥ ቤት ያለው በንብረቱ ተገዶ የመጣ ሲሆን፤ ቁርጠኛ የወያኔ ደጋፊዎች አብዛኛዎች የትግራይ ተወላጆች ነበሩ ከነዚህም ውስጥ አብዛኛው ከሎሳንጀለስ ውጭ ከሆኑ ከተሞች ተለቅመው የመጡ ናቸው።

ተቃዋሚው 100-150 ይሆናል

የሎእስ አንጀለስ አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ዝግጅትና ውጤቱ

ይህ አገር ወዳድ የሎስ አንጀለስ ኗሪ ሁለት እቅዶችን ይዞ ነበር ዝግጅቱን የጀመረው። አንደኛው እቅድ ወደ አደራሹ ገብቶ የወያኔን ስብሰባ እንዳይቀጥል ማድረግ ሲሆን ምናልባት ውስጥ መግባቱ ባይሳካ የመጨረሻው አማራጭ ውጭ መሰለፍን እንደ ሌላ መንገድ በማሳብ ነበር የዝግጅት ክፍሉ የተንቀሳቀሰው። ሰብሰባው የተደረገበት ቦታ የሎስ አንጀለስ ኮንቨንሺን ሴንተር ነበር። ኮንቨንሺን ሴንተሩ በጣም ሰፊ ስለሆነ ከመንገድ ዳር ቆሞ ቢጮህ ወያኔን ሊያሰደነግጠው የማይቻል መሆኑ ቢታወቅም የግድ መሰለፍ አለብን የሚለውን ቁርጥ ሀሳብ በመያዝ ውጭ ከተቆመ ሊደረገ ሚገባዉን ዝግጅት አጠናቀቀ። በዋናነት ለተመረጠውና ውስጥ ለሚደርገውም ከፍተኛ ዝግጅት አጠናቀቀ።

«ምንም ቢቃጠሩ ደረሰ ቀኑ» እንድሚባለው ቀኑ ኤፕሪል 10 ደረሰ። አገር ወዳዱም በአጭር ታጥቆና ሙሉ የስነልቦና ዝግጅት አድርጎ የመጣውን ለመጋፈጥ ከወጣት እስከ አዛውር ያሉ አገር ወዳድ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች ከስብሰባው ሰዓት ቀደም ብለው ተገናኙ። ከውጭ የሚያስፈልገዉን መሰናዶ ካደርጉ በኋላ ወደ አደራሹ አመሩ።

የወያኔዎች አንዱ እቅዱ ከበሩ ላይ የጥሪ ወረቅት የያዙትን ብቻ በጠቋሚዎቻቸው በተመስገንና በአዳል ገንፎ አማካኝነት ተቃዋሚውን በማግለል ደጋፊያቸውን እየመረጠ ለማስገባት ተዝጋጅተው ነበር፤ ነገር ግን የፖሊስ አዛዡ የህዝብ ስብሰባ በፍላዬር ስለጠራችሁ ማንንም ልትከለክሉ አትችሉም ስለዚህ ማንኛውም ሰው እንዲገባ አድርጉ አላቸው። ተቃዋሚውንም ውስጥ ገብታችሁ እንዳትረብሹ፤ ተናጋሪው ተናግሮ ሲጨርስ የናንተ ድምጽ ይሰተናገዳል፤ ከረበሻችሁ ግን እናሰወጣችኋለን በማለት ተቃዋሚውንም ያለምንም ጥያቄ ውስጥ እንዲገባ ተደረገ።

ሰው እስከሚጋባ ድረስ በፓወር ፖይንት ስለ ልማት ፊልም እያሳዩ ነበር። ፊልሙ አልቆ እንግዶች መደረክ ላይ እንደውጡ ስብሰብውን ለመጀመር እየተዝጋጁ ባሉበት ወቅት ከተቃዋሚው በኩል ቪዲዮ የሚያነሳውን ግለሰብ በጸጥታ አሰከባሪዎች ለማስቆም ሲሞክሩ ቤቱ ተበጠበጠ፤ በክፍሉ ውስጥ ተሰበጣጥሮ የነበረው ተቃዋሚ ገንፍሎ ተነሳ፤ አደራሹ ተናወጠ፤ ድንጋጤና ፍርሐት በወያኔ ሰፈር ሰፈነ። እርግማኑ፤ ጩሆቱ፤ የፊሺካው ፉጩት፤ ቤቱን አደባለቀው። አዳል የተባለው አድርባይ መድረኩ ላይ ሆኖ ቤቱን ጽጥታ ሊያሲዝ ሞከሮ አልተሳካለትም። ከዚያ አርከበ ቆሞ ተማጸነ። ነገር ግን እንደ ንብ የገነፈለው ሳታናው አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ማንም ሊያቆመው አልቻለም። የጽጥታ አሰካባሪዎች በስንት ትግል የቆሙትን ለማስቀመጥ ቢጥሩም ጩኽቱ አልቆመም። ምርጫ የሌለው አርከበ እቁባይ በጫጫታ ውስጥ ስለልማት ያዘጋጀውን ጽሁፍ ማንበብ ጀመረ። ሲሚ ግን አልነበርም። ያለ ድማጭ የተዝጋጀሁበትን ተወጥቻለሁ ለማለት ብቻ ማንም ሳይሰማው አንብቦ ጨረሰ። በዚህ ጊዜ ሁኔታው እየባሰ ስለመጣ በቤት አሽከሩ በተመስገን ተስፋዮሐንስ ጠቆሚነት አንድ ተቃዋሚ በሰኪሪቲ እየተገፉ ወደውጭ እንዲወጣ ተደረግ።

ስለዚህ በርከት ያሉ ተቃዋሚዎች ውስጥ ሲቀሩ አብዛኛው ውጭ ወጥቶ ሰልፉን ቀጠለ። ስልፉ ከመንገዱ ላይ መሆኑ ቀርጦ ከስብሰባው በር ላይ እንዲሆን ከፖሊስ ጋር ስምምነት ተደረገ። ውግዘቱ፤ መፈክር ማውረዱ ፍጨቱ ተጧጧፈ።

ወያኔ ውኃ፤ ሻሂ፤ ቡና ከውጭ አዞ ያስመጣውን ውጭ ወጥቶ መጠጣት አልቻለም። ተቃዋሚ ኢትዮጵያዊያን የተዝጋጀውን ድግስ በቁጥጥሩ ሰር በማዋል በጭሆት የደረቀውን ጉሮሯቸውን እያራሰ መፈክሩን፤ መዝሙሩን ማሰማቱን ቀጠለ። ያደራሹ የመጸዳጃ ክፍል በተቃዋሚዎች ቁጥጥር ስር ስለነበር ወያኔዎች ተቃዋሚውን አልፈው ለመሄድ በፍርሃት ስለተዋጡ በሽንት ተውጥረው ዋሉ። አንዳንድ የሆነ ይሁን ብለው የወጡ በስነስርዓት ፎቶ ተነስተው ከሆዳም እስከ አሽከርነት ያለውን የስድብ ካባ ተከናናበው ተመልስው ወደ አደራሹ ይገቡ ነበር። ይህን ውርደት የፈሩ ግን እዝያው ሲያምጡ ውለዋል።

የስብሰባው ጊዜ ከ1PM እስከ ምሽቱ 8 PM ነበር፤ ነገር ግን መጀመሪያ ሲጀምሩ በብጥብጥ ሰለተጀመረ ይህን እርብሻ ለማቀዝቀዝ ሲባል እስከ 3 ሰዓት ድረስ ሳይጀመር ዘገይቷል። ከዚያም 5 PM ሲሆን የፖሊሱ አዛዡ ገብቶ አቆሙ ስላላቸው አምስት ሰዓት ተኩል (5፡30) ሲሆን አቆሙ።

ተጨማሪ ፖሊስ መጥቶ ረዥም መስመር በመስራት እነ አርከበን በጓሮ በር ሲያስወጣ፤ ሌላውን ታዳሚያቸውን ግን በተቃዋሚው ፊት የስድብ ውርዥብኝ እያሽማቀቃቸው እንዲያልፉ ሆነዋል።

ወያኔዎችና ሆዳሞች ከሄዱ በኋላ ወያኔ ጥሎ የኮበሌውን በካርቱን ሙሉ የታሸገውን ባርኔጣቸውን ተቃዋሚው ተከፋፍሎ፤ ስሜት ቀስቃሽ ንግግ በማድረግ ተመራርቆ በደስታ ተለያየቱ።

ሕዝብን በመናቅ ደረቱን ነፍቶ የመጣው የወያኔ ተወካይ በጓሮ በር በፖሊስ ታጀቦ አምልጧል። አጥራችንን የነቀነቀው ወያኔ እሱ ባመጠው መዝዝ እራሱ ተገርፎ ሂዷል።

ቪዲዮ ለመመልከት እዚህ ላይ ይጫኑ
በሎሳንጀለስ አገር ወዳድ ሰደተኛ ኢትዮጵያዊያን