በሎስ አንጀለስ ሊካሄድ የታቀደውን የወያኔ ሴራ እናክሽፍ
በሀገራችን ህልውናና በወገኖቻችን ሕይወት ላይ ከወራሪ ጠላት ባልተናነስ መልኩ ከፍተኛ ጉዳት ባደረሰውና አሁንም በማድረስ ላይ ያለው መለስ ዜናዊና ግብረ አበሮቹ ሀገር ቤት የሚያካሂዱትን የመከፋፈል ሴራ እነሆ በሎስ አንጀለስና አካባቢዋ በምንኖር ኢትዮጵያውያን ላይ ለመዝራት አፕሪል 10 ስብሰባ ጠርተዋል። ጥሪያቸውንም በከተማችን ለዚሁ ትግባር በመለመሎአቸው ሆድ አደሮችና ደካማ ግለሰቦች አማካኝነት ወረቀት ሲበተን ከርሞአል። መለስ ዜናዊና ግብረአበሮቹ እነማን ናቸው፤
* በጎሳ ላይ የተመሠረተ ፓሊሲ በማስፈን ወገኖቻችን በጥላቻና በመከፋፈል እንዲኖሩ እያደረጉ ያሉ፤
* ሕዝባችን ለዘመናት የተዋደቀለትን የመናገር ፤ የመጻፍና የመሰብሰብ ነፃነት በመሣሪያ ኃይል ያፈኑ፤
* የሀገሪቱን ለም መሬቶች ከደሀ ገበሬው እየነጠቁ ለውጭ መንግሥታትና ቱዣሮች ለ99 ዓመታት በሽያጭ የስጡ፤ በዚህ የውጭ ከበርቴዎች በተያዙ ርሻዎች እስከ 96 የሚደርሱ ኬሚካሎች ይረጫሉ ። አብዛኛዎቹ ኬሚካሎች ለሰው ልጆችና ለእንሰሳት ሂዎት አስጊ በመሆናቸው በምዕራቡ ዓለም የተከልከሉ ናቸው። ይህንም ብዙ የጤና ባለሙያዎች አረጋግጠዎል። ወያኔ በስልጣን ላይ እካለ ድረስ ካዝናዉን መሙላት እንጅ ለወደፊቱ ለሐገሪቱና ለሕዝባችን ደንታ የለውም።
* ሀገራችንን ያለባህር ወደብ ያስቀሩ፤
* ከ 193 በላይ የሚሆኑ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ሰላማዊ ስልፈኞችን በ 1997 ዓም በጥይት አስደብድበው ያስገደሉ
* የሀገሪቱን ሀብትና፤ የንግድና እንዱስትሪዎች እንቅስቃሴ ከ 80 በላይ በሚሆኑ የህወሃት የግልና በመለሰ ሚስት ቁጥጥር ሥር በሚተዳደሩት ድርጅቶቻቸው አማካኝነት አይን ባወጣ መልኩ እየዘረፉ ያሉ፤
* በቅጥፈት ኤኮኖሚውን አሳደግን እያሉ ነገር ግን በዓለም ምግብ ድርጅት ስሌት መሠረት በአሁኑ ወቅት ከ10 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ወገኖቻችን በከፍተኛ የምግብ እጦት ምክንያት በመጋለጣቸው በሞት አፋፍ ላይ እንዲገኙ ያደረጉ፤
* በተሳሳተ የአኤኮኖሚ ስሌታቸው ምክንያት በሀገራችን ከቁጥጥር ውጭ እየሆነ በሄደው የዋጋ ግሽበት ምክንያት በከተማም ሆነ በገጠር ያሉ ወገኖቻችን ለከፍተኛ ረሀብ በመጋለጣቸው በሀገሪቱ አራቱም የክልል ማእዘኖች ሀገሩን እየተወ እንዲኮበልል ያደረጉ፤ አብዛኞቻችንም ለስደት የዳረጉ፤
* የሀገሪቱ የሥራ እንቅስቃሴ ዘርፎች፤ በተለይም የሀገር መከላከያ፤ የፖሊስና የደህንነት ክፍሎቹ በራሳቸው ጎሳ አባላት ብቻ እንዲመሩ በማድረግ ሌሎችን በግፍና በዲክተተር አገዛዛቸው ሥር እንዲወድቅ ያደረጉ፤
* ሕዝባችን ለዘመናት የተዋደቀለትን የመሬት ላራሹ መርህ ገልብጠው ገበሬውን ለመቆጣጠርና መሬትን እንደልባቸው ለመሸጥና ለመለወጥ እንዲያመቻቸው ባለቤትነቱን “የመንግሥት” ብሎም የወያኔ ፓርቲ ያደረጉ፤
* ኢትዮጵያ በልማት አድጋለች ፤ ኑና አገራችሁን አልሙ እያሉ ሕዝባችን በቀቢጠ ተስፋ ሊደልሉት ይሞክራሉ ነገር ግን እነሱ ልማት የሚሉት የውጭ ከበርቴዎች የሚያመርቱትን የአባባ ተክልና ወደ ውጭ አገር ሂዶ ሚሸጠዉን ምርት ነው። አበባ ለድሐው ህዝባችን ዳቦ አይሆንም። የውጭ ምንዛሬው ተሺጦ የውጭ ከበርቴውን ካዝና ይሞላል የተረፈው ፍርፋሪም ከወያኔ ካዝና ይገባል። ሕዝባችን ግን ከርሐብና ከድህነቱ አይወጣም።
* የቀለበት መንገድ ለከበርቴው (ለወያኔ) መገልገያ እንጅ ለደሐው ሕዝባችን ምንም ጥቅም የለው። ስንቱ ሕዝብ ነው መኪና ያለው? ወያኔ ትልልቅ ፎቅ በመስራትና መንገድ በመገንባት የውጭ ጌቱቹን አይን ለመማረክ የሚያደርገው ቅጥፈት ነው።
ውድ ወገኖቻችን፤ ከላይ ከብዙ በጥቂቱ የተዘረዘረው በደላቸው አልበቃ ብሎ አሁን ደግሞ በውጭ ከምንገኘው የሚቻላቸውን ለመዝረፍ በተቀነባበረ ዘዴ በመጠቀም በሎስ አንጀለስ ከተማችን አፕሪል 10 ቀን በሎስ አንጀለስ ኮንቬንሽን ሴንተር እንድንገኝ በተላላኪዎቻቸው አማካኝነት ጥሪ አቅርበዋል። ሌላው ዓላማቸውም በውጭው ዓለም በአሁኑ ወቅት የሚታየውን የተቃውሞ ኅይል የሚቻል መስሎአቸው እርስ በርሳችን የሀሰት መረጃ በመስጠት ለመከፋፈል ነው። መሠረታዊ የሰው ልጆች መብት በሌለበት፤ ፍትህና የግለሰብ ነፃነት በሌለበት፤ ነፃና ፍትሀዊ የንግድ ግብይይት በሌለበት፤ በሀያ ዓመት አገዛዝ ሕዝቡን ከረሀብ አለንጋ እንዲላቀቅ ያልረዱ፤ የአምስት ዓመት የልማት እቅድ አለን ብሎ መሸለሉ አይናችሁን ጨፍኑ ላሞኛችሁ ማለት ነው።
እነሆ ለሀያ ዓመታት ሙሉ በውጭ ለምትገኙት የቤት መሥሪያ ቦታ እንሰጣለን፤ በኢንቨስትመንት ኑና ተሳተፉ ልዩ ልዩ ቢዝነስ መሥራት እንድትችሉ እንረዳችህዋለን እያሉ የዋሆችን ሲያታልሉና በመጨረሻም አምነው የለፉበትን ገንዘብ ስጥተው አጨብጭበው የቀሩ ስንቶች እንደሆኑ ያደባባይ ምሥጢር ነው። በወያኔ ፕሮፓጋንዳ ተታለው ንብረታቸውንና የለፉበትን ቅርስ ሸጠው ወደ ሀገር የገቡ አብዛኛው በወያኔ ጎስኛ ፤የጉቦና የዝምድና አሰራር ተማሮ የተመለሰው ስንቱ እንደሆነ ከአካባቢያችን ጠይቆ መረዳት ይቻላል።
ስለዚህ በሎስ አንጀለስ ከተማ የምትኖሩ ወገኖች በሙሉ የወያኔና በከተማችን የፈለፈላቸውን ቅጥረኞች ሴራ ተባብረን እናክሽፍ እንላለን። ከፍ ብሎ በተጠቀሰው ቀንና የስብሰባ ቦታ በመገኘት ተላላኪዎቹ በመጡበት የውሸት ካባ ተከናንበው እንዲመለሱ እናድርግ።
በከተማችን የሚገኙ የወያኔ ቅጥረኞችንም አውቀን የዚህ ሁሉ ጥቃት ሰለባ ለሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብም ሆነ በከተማችን ለሚገኙ ወገኖች ማንነታቸውን በማጋለጥ እንተባበር እንላለን። ይህንን ጥሪ በማራባትና ለወገኖቻችን በማዳረስ እንዲተባበሩን በማክበር እንጠይቃለን።
የወያኔ ሴራ ይከሽፋል
በሎስ አንጀለስና አካባቢው የምንገኝ አገር ወዳድ ኢትዮጵያን ስደተኞች ግብረ ኅይል