ቁምሳ
ከወንድሙ መኰንን
ለማጁ ቀጣፊ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሥቃይ መለስ ዜናው መጋቢት ፳፯ ቀን ፪ሺ፫ ፓርላማዬ በሚለው በረት ውስጥ ለኮለኮላቸው ድብኝት አሻንጉሊቶቹ ሲናገር፣ ድርብ ቀመር የታየበት ዕድገት አሳይተናል ብሎ ቀባጠረ። አቤት ውሸት! አቤት ውሸት! ሀቁ መሬት ላይ እንደሚታየው ከሆነ አብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚላስ የሚቀመስ አጥቶ፣ ጦሙን ዉሎ ጦሙን ያድራል። አለው የሚባል፣ ዛሬ ቁርስ ከበላ፣ ምሳን አስቦ የሚውል ዜጋ ነው። እንዲያውም ምሳና ቁርስ አንድ ላይ የመብላት ዘዴ ዘይዷል ። እሱም ምግብ ከተባለ፣ አንድ ሙዝና አንዲት ቁራጭ ዳቦ ናት። ያቺም “ቁምሳ” የሚል ስም ወጥቶላታል። የወያኔ የውሸት ቱልቱላ ሲነፋባቸው ስልችት ያላቸው የኢትዮጵያ አርቲስቶች፣ “ፈረቃ” የሚል ሙዚቃዊ ድራማ አዘጋጅተው በዚያን ሰሞን አዝናኑን። ካላዩት የሚከተለውን ተጭነው
እርስዎም ይዝናኑ። ችጋሩና ቸነፈሩ የተባበሩትን የዓለም መንግሥታት አሳስቦት “ጠኔው ድባቡን አጥልቷልና ቶሎ ለጋሽ አገሮች ካልደረሱላት፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ በረሀብ እንደ ቅጠል መርገፉ ነው፤” ብለው ቅርብ ቀን ያስጠነቀቁትን ልብ ይሏል። የችግሩ ብዛት፣ ዛሬ ማንም ከሚችለው በላይ ሆኖበት፣ ቤተሰብ ብሔራዊ ውርደት ተሸክሞ፣ ትናንሽ ልጃገረዶች፣ ትምህርት ቤት ሳይሆን የሚውሉት፣ ወይ ለአስነዋሪ ተግባር ተሰማርተው በሸቀሉት ገንዘብ በተሰቦቻቸውን ለመመገብ የዚያው የወያኔ ባለሥልጣናት ፍተወት ጥማት ማርኪያነት ሲዳረጉ፣ ሌሎች እንደዝህች ልጅ ቆሻሻ ውስጥ ምግብ ፍለጋ ሲለቅሙ ነው የሚውሉት። የኛዎቹ ሀፍረተቢስ ዘመናይ ገዢዎች ታዲያ ዓይናቸውን በጨው አጥበው “በልማት ያስመዘግብነውን ዕድገት ኑ እዩልን፣ ተመልከቱልን” እያሉ በደረቁ ሊላጩንን ይሞክራል።
የውሸት መንፈስ የተጠናወተው ወያኔ ስላስመዘገበው የልማት ግብ ያለንዳች ሀፍረት ሲደሰኩር ከሰሙት የውጭ አገር ሰዎች መሀል፣ ኢትዮጵያን ሲጎበኙ ከነበሩ የጀርመን የፓርላማ ልዑካን አንዱ ሚስተር ቲሎ ሆፕ (Mr Thilo Hoppe) ይኸ የዱሩዬ መንጋ እንዴት አጭበርባሪ እንደሆነ አጋልጠው፣ የጀርመን መንግሥት ዕርዳታውን ወደፊት ያለገደብ ከመለገሱ በፊት እንደገና የሰብአዊ መብት ረገጣውን መጠን መልሶ ማጤን እንዳለበት አሳስበዋል።