በየመን 4 ኢትዮጵያዊያን ሞቱ

ጦርነት ተቀሰቀሰ…!! ስደተኞች UNHCR በር ላይ ተቀመጡ።፡ነገሩ እየተካረረ መግባባት ጠፍቶ ጦርነት በተቀሰቀሰባት የመን 4 ኢትዮጵያዊያን ሰለባ ሆኑ::ሰነዓ ከተማ ውስጥ አሳባ የሚባለው አካባቢ ከሼህ ሳዲቅ ጋር ሲደረግ የነበረው ውጊያ ዛሬ ጋብ ብሎ ቢውልም ክሰነዓ ውጭ ያለው ሁኔታ አልረገብም የሚል አሉ::እነዚህ 4 ኢትዮጵያዊያንም የሞቱት በሰነዓ ከተማ አሳባ በሚባለው አካባቢ በተደረገው ጦርነት ነው።

ያለው ሁኔታ ያሰጋል!!እጅግ አስፈሪነት ያለው ሁኔታ ውስጥ ያሉ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች መፍትሄ ይሰጠን ጥያቄ ይዘው UNHCR በር ላይ ተቀመጡ። ከምንም በላይ ቢሮው ዝምታን ዘላቂ መፍትሄ አድርጎታል::<<..የሞተ የለም ከዚህ ተነሱ..>> በሚል በፖሊስ ለማስነሳት ከማሰብ ያልዘለለ መፍትሄ ሊያቀርብ ያልቻለው UNHCR አማራጭ ሀሳብ ያደረገው የሞቱና የቆሰሉ ሰዎችን ስም እና አድራሻ መጠየቅ ነው::..በስደተኛው ህይወት በማላገጥ ላይ ያለው UNHCR ለሁሉ ነገር መፍትሄ ያደረገው በፖሊስ ከበሩ ላይ ማስነሳት እና ማሳሰር ነው::ከዚህ በፊትም ቢሆን እዛው UNHCR በር ላይ መፍትሄ ካልተሰጠኝ አልነሳም ብለው የተቀመጡት ባልና ሚስቶቸን በፖሊስ አስገድደው ሲያስነሱ ሴቷ በደረሰባት ድብደባ የ5 ወር ጽንስ አስወርዳለች።፡ከነህክምና ማስረጃው ለህዝብ ማቀረቤ ይታወሳል::..ከስህተታቸው ያልተማሩት ለስደተኛ ቆመናል ከሚል ድርጅት የማይጠበቅ ስራ የሚሰሩት ሰራተኞች ግን ዛሬም በተመሳሳይ ስራ ተሳተፉ።

ይህ መፍትሄ ይሰጠን በስደት ያለንበት ሀገር ሰላም አስተማማኝ አይደለም::አልፎ ተርፎም ጦርነት ተጀምሯል::ህይወታችንን ለማዳን ወጥተን ህይወታችንን ልናጣ ነው ምን ይሻለናል የሚል ጥያቄ የቀረበው ለUNHCR ቢሆንም በዓለም ላይ ያሉ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ጉዳያቸው አድርገው ካልተረባረቡበት ነገ..ነገ..ዘግናኝ እልቂት ..አሳዛኝ ታሪክ ሊከሰት ይችላል::ወገን ሁሉ በየመን ያለ ወገንህን አድን የሚል ጥሪ ኮሚቴዎቹ አስተላልፈዋል።

የሞቱት ሰዎችን ሬሳ አንሳ ተብዬ ተጠይቄያለሁ ያለ ጀማል የተባለ የስደተኛ ተወካይ ሬሳው ኩዌት ሆስፒታል እንዳለ ገልጿል::ይህ የሞቱ የተባለው በአይኑ ያያቸውን ብቻ ሲሆን ቁጥሩ ከዚህም ከፍ ሊል እንደሚችል የአይን እማኙ ተናግሯል።