የኢትዮጵያ ዕፅዋት ጄኔቲክ ሀብት ማዕከል የእሳት ቃጠሎ አደጋ ደረሰበት
– ከ60 ሺሕ በላይ የዕፅዋት ጄኔቲክ ናሙናዎች አሉ
(በታምሩ ጽጌ)
በጀርመን መንግሥት ድጋፍ ከ40 ዓመታት በፊት የተቋቋመው የኢትዮጵያ ዕፅዋት ጄኔቲክ ሀብት ማዕከል (የኢትዮጵያ ብዝኅ ሕይወት ጥበቃ ኢንስቲቲዩት ተብሏል) ጳጉሜ 2 ቀን 2002 ዓ.ም. የእሳት ቃጠሎ አደጋ ደረሰበት፡፡ የደረሰው ቃጠሎ የተጋነነ አለመሆኑን በጅን ባንኩ ውስጥ ያሉት ዘረመሎች ላይ ምንም ዓይነት ጉዳት እንዳልደረሰ ኢንስቲቲዩቱ ገልጿል፡፡