– በሥራው ለሚሳተፉ ዳኞች 400 ሺሕ ብር ተመድቧል (በብርቱካን ፈንታ) በፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ በአማራ ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ በኦሮሚያና በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልሎች ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች ለረዥም ጊዜ ውሳኔ ሳያገኙ የቆዩ 15 ሺሕ ውዝፍ ፋይሎች ላይ የመጨረሻ ውሳኔ ለመስጠት የሚያስችል ስምምነት፣  …

በጠቅላይ ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ሳያገኙ የቆዩ 15 ሺሕ የክስ ፋይሎች ፍጻሜ ሊያገኙ ነው Read more »

(በምዕራፍ ብርሃኔ) በመላ አገሪቱ የሚገኙ ትላልቅ ሆቴሎች ለመገልገያነት ከቀረጥ ነፃ ያስገቧቸውን ዕቃዎች ዝርዝር፣ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ለኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን እንዲያሳውቁ ዳይሬክተሩ አቶ መላኩ ፈንታ ትናንት አስታወቁ፡፡

(በታምሩ ጽጌ) የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ሰሞኑን ያደረገው ደመወዝ ጭማሪ በሠራተኞቹ መካከል ከፍተኛ ልዩነት መፍጠሩን አንዳንድ የድርጅቱ ሠራተኞች ለሪፖርተር ገለጹ፡፡

(በመርጋ ዮናስ) የኢትዮጵያ የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማኅበር የሥራ አመራር ቦርድ በኮሜት ትራንስፖርት አክሲዮን ማኅበር በተባረሩት 64 የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ምክንያት፣ በሚቀጥለው ሳምንት ቄራ በሚገኘው የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ክስ ሊመሠረት ነው፡፡

ቃለየሱስ በቀለ ከሁለት ሳምንት በፊት የጅቡቲ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣናት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ጅቡቲ ያደርገው የነበረውን በረራ እንዲያቋርጥ በሰጡት ትዕዛዝ መሠረት፣ በረራውን አቋርጦ የቆየ ቢሆንም ትናንትና መደበኛ በረራውን መቀጠሉን አስታወቀ፡፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ጅቡቲ የበረራ አገልግሎት ይሰጥ የነበረው በፎከር …

አየር መንገድ ተቋርጦ የነበረውን የጅቡቲ በረራ ቀጠለ Read more »

– «ሙስናን ለማጥፋት ምን ዕቅድ ተይዟል?» ተሰብሳቢዎች– «የቀረቡትን ጥያቄዎች በፀጋ እንቀበላቸዋለን»  አቶ ግርማ ብሩ(በውድነህ ዘነበ) ከትናንት በስቲያ ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተጀመረው የአምስት ዓመቱ የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ውይይት ላይ ተሰብሳቢዎች ትኩረት አድርገው የሚያነሱዋቸው ጉዳዮች በከተማው ውስጥ ባሉ ችግሮች ላይ …

በአዲስ አበባ የተካሄደው ውይይት አነጋጋሪ ሆኗል Read more »

(በኃይሌ ሙሉ) በቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ አየለ ጫሚሶ አስተባባሪነት በአሥራ አራት ፓርቲዎች ሊመሠረት ታስቦ የነበረው ግንባር ሳይሳካ ቀረ፡፡ አብዛኛዎቹ ፓርቲዎች ራሳቸውን ከድርድሩ አግልለዋል፡፡

200 ሺሕ ሔክታር መሬት ይፈለጋል (በውድነህ ዘነበ) መንግሥት በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት በ200 ሺሕ ሔክታር መሬት ላይ የሸንኮራ አገዳ ልማትና ሦስት የስኳር ፋብሪካዎችን ለመገንባት አዲስ ዕቅድ አወጣ፡፡

– 400 ሚሊዮን ብር ዕዳ ይቀርበታል (በውድነህ ዘነበ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ ለኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሽን ካለበት ብድር ውስጥ 200 ሚሊዮን ብር ከፈለ፡፡

ብርቱካን ፈንታ በ2002 ዓ.ም. የ12ኛ ክፍል የመልቀቂያ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚያስገባቸው ውጤት ምን ያህል እንደሆነ እንደማይታወቅ ተገለጸ፡፡ የመግቢያ ውጤቱ በዩኒቨርሲቲዎቹ የመቀበል አቅም ይወሰናል፡፡ ተማሪዎቹ የመልቀቂያ ፈተናውን ውጤት ከሐምሌ 23 ቀን 2002 ዓ.ም. ጀምሮ ያወቁ ቢሆንም፣ እንደቀደሙት ጊዜያት ዩኒቨርሲቲ …

የዚህ ዓመት የዩኒቨርሲቲዎች መግቢያ ውጤት አይታወቅም Read more »

– ከሦስት ሚሊዮን ብር የሚበልጥ ወርቅና ንብረት ዘርፈዋል (በታምሩ ጽጌ) የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ ሚያዚያ 18 ቀን 2001 ዓ.ም. በአራዳ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 10 ውስጥ ፒያሳ አካባቢ በሚገኘው ጣና ወርቅ ቤት ላይ ዝርፊያ አካሂደዋል በሚል ጥር 7 ቀን 2002 ዓ.ም. ክስ …

የጣና ወርቅ ቤትን የዘረፉ ተከሳሾች ጥፋተኛ ተባሉ Read more »

‹‹ሁለት መቀመጫ ያለው ቅንጅት የ40 ሰዎች ድጐማ ተሰጥቶታል››  አቶ ለገሰ ቢራቱ‹‹ቅንጅት የገንዘብ ድጐማ የተሰጠው ፓርላማ ባለው ወንበር ልክ ነው›› አቶ አየለ ጫሚሶ‹‹የምርጫ ቦርድ ሕጉን ጥሷል›› አቶ ተመስገን ዘውዴ‹‹ድጐማውን የሰጠነው በመስፈርቱ መሠረት ነው›› አቶ ተስፋዬ መንገሻ (በኃይሌ ሙሉ) ራሳቸውን ከቅንጅት ለአንድነትና …

ምርጫ ቦርድ ለቅንጅት የሰጠው የገንዘብ ድጐማ እያነጋገረ ነው Read more »

– በዓመት 340 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጡ ዕቃዎች ይወረሱ ነበር (በብርሃኑ ፈቃደ) በጂቡቲ ወደብ ውስጥ ስድስት ወርና ከዚያ በላይ የቆዩ ዕቃዎች ከእንግዲህ እንዳይወረሱ የሚያስችል ስምምነት በመደረሱ፣ ወደብ ላይ የቆዩ ዕቃዎች ወደ አገር ውስጥ መግባት ጀመሩ፡፡

– ሊያደርጉት የነበረው ስብሰባ በፖሊስ ኃይል ተበተነ (በታምሩ ጽጌ) በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ሕዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በጉራጌ ዞን በሶዶ ወረዳ ሥር የሚገኙ የ27 ቀበሌዎች ነዋሪዎች በሕገ መንግሥቱ የተፈቀደልንን የመሰብሰብ፣ የመደራጀት፣ ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ፣ የመቃወምና የመደገፍ መብቶቻቸውን በወረዳውና በዞኑ ኃላፊዎች መነፈጋቸውን …

የሶዶ ወረዳ ነዋሪዎች በሕገ መንግሥቱ የተረጋገጠልንን መብት ተነፈግን አሉ Read more »

(በጋዜጣው ሪፖርተር) የኢትዮጵያ ንግድ መርከብ አክሲዮን ማኅበር በበጀት ዓመቱ 415.6 ሚሊዮን ብር ለማትረፍ አቅዶ 641.4 ሚሊዮን ብር ማትረፉንና የዕቅዱን 154 በመቶ ማግኘቱን፣ ካለፈው ተመሳሳይ የበጀት ዓመት ጋር ሲነፃፀር 63 በመቶ የበለጠ ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ፡፡

(በኃያል ዓለማየሁ) የዓለም ማራቶን ክብረወሰን ባለቤት አትሌት ኃይሌ ገብረ ሥላሴ የደቡብ ኮሪያ ስሪት የሆኑትን የሃዩንዳይ ተሽከርካሪዎች መገጣጠሚያ ፋብሪካ እንደሚገነባ ለሪፖርተር ገለጸ፡፡

(በኃይሌ ሙሉ) በማታለልና በማጭበርበር ወንጀል ክስ ተመስርቶባቸው የነበሩት የጌት አስ ኢንተርናሽናል ኩባንያና የጌቱ ኮሜርሻል ሴንተር ባለቤት አቶ ጌቱ ገለቴ የተመሠረተባቸው ክስ ውድቅ ተደረገ፡፡

(በውድነህ ዘነበ) የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የግልግል ዳኝነት ኢንስቲትዩት፣ በኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣንና በሥራ ተቋራጮች መካከል የሚነሱ አለመግባባቶችን መዳኘት የሚያስችለውን ሥራ ተረከበ፡፡

(በታምሩ ጽጌ) የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ባወጣው መመሪያ መሠረት ትምህርታቸውን በ10+3 ፕሮግራም መጀመራቸውንና ለሦስት ዓመታት ከተማሩ በኋላ ‹‹ሥልጠናችሁ በደረጃ 4 ነው›› የተባሉ የእንጦጦ የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ኮሌጅ የማታ ተማሪዎች፣ ከነሐሴ 7 ቀን 2002 ዓ.ም. ጀምሮ ላልተወሰነ ቀን ትምህርት ማቆማቸውን …

የእንጦጦ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ የማታ ተማሪዎች የትምህርት ማቆም አድማ ማድረጋቸውን ገለጹ Read more »

(በኃይሌ ሙሉ) የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) ምርጫ 2002ትን ተከትሎ በአዲስ አበባ የአባላት ምልመላ እያካሄደ መሆኑን አስታወቀ፡፡ የድርጅቱ ሊቀመንበር አቶ ልደቱ አያሌው ለሥራ ጉብኝት ወደ አሜሪካ ተጉዘዋል፡፡

(በሔኖክ ያሬድ) የቀድሞ ሰው ከ3.4 ሚሊዮን ዓመት በፊት የድንጋይ መሣርያ ይጠቀም እንደነበርና መሣርያዎቹንም ተጠቅሞ የትላልቅ አጥቢ እንስሳት ሥጋና መቅኒ ይመገብ እንደነበር የሚያሳዩ ቅሪቶች መገኘታቸውን ነሐሴ 5 ቀን 2002 ዓ.ም. በብሔራዊ ሙዚየም በ10 ሰዓት ይፋ ሆነ፡፡

(የማነ ናግሽ፥ ሪፖርተር) የኤርትራ ተቃዋሚዎች ጥምረት (ኪዳን) ሰሞኑን በአዲስ አበባ ባካሄደው ጉባዔ፣ የስደት ብሔራዊ ሸንጎ (ፓርላማ) ለማቋቋም መወሰናቸውን አስታወቀ፡፡ ይህንን የሚያመቻች ብሔራዊ ኮሚሽንም ተሰይሟል፡፡ አሥር ተቃዋሚ ኃይሎችን ያካተተውና የኤርትራ ዴሞክራሲያዊ ኪዳን በመባል የሚታወቀው ጥምረት፣ ከኤርትራ ሲቪል ማኅበረሰቦች ጋር በጋራ በመሆን …

የኤርትራ ተቃዋሚዎች የስደት ፓርላማ ለማቋቋም ተስማሙ Read more »

(በኃይሌ ሙሉ) ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ መንግስት በቀጣዩቹ አምስት ዓመታት የያዘው የልማትና የዕድገት ዕቅድ ሙሉ በሙሉ ይፈጸማል ብሎ በእርግጠኛነት መናገር እንደማይቻል ገለጹ፡፡ አቶ መለስ ዛሬ ለአገር ውስጥ ጋዜጠኞች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንዳስታወቁት፣ መንግስት በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት በየአመቱ 15 በመቶ …

ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ በቀጣዩቹ አምስት ዓመታት የልማት ዕቅድ ዕርግጠኛ መሆን እንደማይቻል ገለጹ Read more »

(በውድነህ ዘነበ) ከትናንት በስቲያ ጀምሮ በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት በአገሪቱ ተግባራዊ በሚደረገው የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ላይ ሕዝቡን በማወያየት ሥራ የተጠመዱት የመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት፣ የማወያየቱትን ሥራ ከጨረሱ በኋላ የፓርቲ ግምገማ እንደሚጀምሩ አንድ ስማቸው እንዳይገለጽ የሚፈልጉ ከፍተኛ ባለሥልጣን ለሪፖርተር ገለጹ፡፡

(በቃለየሱስ በቀለ) የአሜሪካው ኤክስፖርትና ኢምፖርት (ኤግዚም) ባንክ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከቦይንግ ኩባንያ ለሚገዛቸው 10 ቦይንግ 787 ድሪም ላይነር አውሮፕላኖች፣ ለአምስት ቦይንግ 777 አውሮፕላኖችና ለጄነራል ኤሌክትሪክ ኩባንያ ሰራሽ የአውሮፕላን ሞተሮች መለዋወጫ መግዣ የሚውል የ1.6 ቢሊዮን ዶላር የብድር ዋስትና ሰጠ፡፡

– የይቅርታ አሰጣጥና አፈጻጸም ሥነ ሥርዓት አዋጅ ረቂቅ ቀረበ (በታምሩ ጽጌ) በተለያዩ የወንጀል ድርጊቶች ተፈርዶባቸው በፌዴራልም ሆነ በዘጠኙም ክልሎች ውስጥ በሚገኙ ማረሚያ ቤቶች የሚገኙ ታራሚዎች ይቅርታ ሲደረግላቸው፣ የይቅርታ መስፈርቶቹ መለያየት እንደማይገባቸውና ወጥነት እንዲኖራቸው ተጠየቀ፡፡

– የአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ ተጠርጣሪዎች መታሰራቸውን ገልጻል (በኃይሌ ሙሉ)   የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) አባል ነበሩ የተባሉትን ግለሰብ ምሥራቅ ጎጃም ውስጥ ግንቦት 10 ቀን 2002 ዓ.ም. የገደሉ ግለሰቦች እስካሁን ድረስ ለፍትሕ አለመቅረባቸውን የሟች ቤተሰቦች ገለጹ፡፡ መኢአድ ጉዳዩ በኮሚቴ …

የመኢአድ አባል ገዳዮች ወደ ፍትሕ አልቀረቡም የሚል አቤቱታ ቀረበ Read more »

– ለቦርድ ሰብሳቢውና ለውኃ ሀብት ሚኒስቴር ደብዳቤ ጽፈዋል (በታምሩ ጽጌ)   የኢትዮጵያ ውኃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት በቅርቡ በልዩ ሁኔታ በዋና ሥራ አስፈጻሚው ውሳኔ የተመደቡት ሠራተኞች የምዘና መስፈርት ሕገወጥ መሆኑን አንዳንድ ሠራተኞች ለሪፖርተር ገለጹ፡፡

(በብርቱካን ፈንታ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ፣ በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የቆሻሻ ገንዳዎችንና ቆሻሻ ማንሻ መኪናዎችን አሠራር ኮምፒውተራይዝድ በማድረግ፣ በቅርቡ ወደ ዘመናዊ የአሠራር ዘዴ  እንደሚገባ ገለጸ፡፡

(በታምሩ ጽጌ) በህቡዕ በመሰባሰብ፣ መንግሥትንና ሕገ መንግሥቱን በኃይልና በአመጽ ለመጣል በመስማማት ሲንቀሳቀሱ ተገኝተዋል በሚል በሞት፣ በዕድሜ ልክ፣ በአሥር ዓመት እሥራት ቅጣትና በነፃ የተሰናበቱት የግንቦት 7 ፍርደኞችና ዓቃቤ ሕግ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ያቀረቡት የይግባኝ አቤቱታ ባለፈው ዓርብ ለመጨረሻ ውሳኔ ለጥቅምት 23 …

የግንቦት 7 ተከሳሾች ለመጨረሻ ውሳኔ ተቀጠሩ Read more »

በአገሪቱ የማክሮ ኢኮኖሚ ኮሚቴ አመራር ሰጭነት የተዘጋጀው የኢትዮጵያ የአምስት ዓመት ስትራቴጂክ ፕላን (የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ) የሚሳካ ከሆነ በ2007 ዓ.ም.፡- በአገሪቱ የማክሮ ኢኮኖሚ ኮሚቴ አመራር ሰጭነት የተዘጋጀው የኢትዮጵያ የአምስት ዓመት ስትራቴጂክ ፕላን (የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ) የሚሳካ ከሆነ በ2007 ዓ.ም.፡- • በኢትዮጵያ …

በተስፋ የተሞሉት ቀጣዮቹ አምስት ዓመታት ‹‹ኢትዮጵያ በዓለም ፊት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በተመጽዋችነት ስሟ አይነሳም›› አቶ ሱፊያን አህመድ Read more »

(በኃያል ዓለማየሁ) የኢትዮጵያና የሱዳን መንግሥት ከወር በፊት ባደረጉት ስምምነት መሠረት ሱዳን ብቸኛዋ የኢትዮጵያ የቤንዚን ፍጆታ አቅራቢ ሆነች፡፡ ባለፉት ዓመታት የኢትዮጵያን 80 በመቶ የቤንዚን ፍጆታ ሲያቀርብ የቆየው ባለቤትነቱ የሱዳን መንግሥት የሆነው ሱዳን ፔትሮሊየም ኮርፖሬሽን፣ በስምምነቱ መሠረት ከመስከረም 2003 ዓ.ም. ጀምሮ ሙሉ …

ሱዳን ብቸኛዋ የኢትዮጵያ ቤንዚን አቅራቢ ሆነች Read more »

– ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ እንዲያነጋግሯቸው ጥሪ አቅርበዋል (በጋዜጣው ሪፖርተር) በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት፣ በካፋ ዞን የቦንጋ ከተማ ነዋሪ የሆኑ ከ7000 በላይ ሰዎች፣ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ በአቶ ብርሃኑ አዴሎ የደረሰባቸውን በደልና የመልካም አስተዳደር እጦት የሚያስረዳ አቤቱታ …

ከ7000 በላይ የቦንጋ ነዋሪዎች በአቶ ብርሃኑ አዴሎ ላይ ያላቸውን አቤቱታ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ላኩ Read more »

(በታምሩ ጽጌ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን አባል የሆኑት ዋና ሳጅን ስንታየሁ አረጋ፣ አንድ የፌዴራል ፖሊስ አባል ሐምሌ 28 ቀን 2002 ዓ.ም. ከመኖሪያ ቤታቸው ድረስ ሄዶ ባደረሰባቸው ድብደባ፣ ከባድ ጉዳት እንደደረሰባቸው በተለይ ለሪፖርተር ገለጹ፡፡

(በኃይሌ ሙሉ) ‹‹መለስ ዜናዊና የሕወሓት የትግል ጉዞ›› የተሰኘ በሦስት ተከታይ ሕትመቶች የሚወጣ መጽሐፍ በሸራተን አዲስ ነሐሴ 22 ቀን 2002 ዓ.ም. በከፍተኛ ሥነ ሥርዓት እንደሚመረቅ ታወቀ፡፡

‹‹የመንገዶችን ምልክት ማድረግ የትራንስፖርት ባለሥልጣን ሥራ ነው››  የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን‹‹ምልክት የመትከል ኃላፊነት ያለበት የመንገዶች ባለሥልጣን ነው››   የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ባለሥልጣን (በብርቱካን ፈንታ) በቅርብ ጊዜ በተገነባው ከጎተራ እስከ ሳሪስ የአስፋልት መንገድ ላይ ምንም አይነት ምልክት ባለመቀመጡና በነዋሪዎች ዘንድ እያስከተለ ባለው …

በመንገድ ምልክቶች ላይ ባለሥልጣን መሥርያ ቤቶቹ እየተወዛገቡ ነው Read more »

– ጉዳያቸው በሚዲያ እንዳይዘገብ ተጠየቀ (በኃይሌ ሙሉ) ወይዘሪት ሄለን አንበሴ ግሩም በተባሉ ግለሰብ ላይ የማታለል ወንጀል ፈጽመዋል ተብለው በዓቃቤ ሕግ የተከሰሱት የጌት አስ ኢንተርናሽናል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበርና የጌቱ ኮሜርሻል ሴንተር ባለቤት አቶ ጌቱ ገለቴ፣ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቦሌ …

ጌቱ ገለቴ በተከሰሱበት ወንጀል በ10 ሺሕ ብር ዋስ ተለቀቁ Read more »

– ጉዳዩን ፖሊስ እየመረመረው ነው (በታምሩ ጽጌ) በኢትዮጵያ ቀደምት ከሆኑት የመንግሥት ሆቴሎች መካከል አንዱ የሆነውና እስካሁንም ድረስ መንግሥት በባለቤትነት የሚያስተዳድረው ኢትዮጵያ ሆቴል ውስጥ አልጋ ይዘው ከአንድ ወር በላይ ተቀምጠው የሚገኙ አንድ ፕሮፌሰርና ሌላ ማንነታቸው ያልታወቁ አንድ ግለሰብ ሐምሌ 22 ቀን …

ኢትዮጵያ ሆቴል ያረፉ እንግዳ ባልታወቁ ሰዎች ተዘረፉ Read more »

– ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉት ፓርኮች ከለላ የተደረገላቸው ሁለቱ ብቻ ናቸው (በብርቱካን ፈንታ)   ጋምቤላን ከሱዳን ጋር የሚያዋስነው የጋምቤላ ብሔራዊ ፓርክ ውስጥ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ መጀመሩን፣ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን የትምህርት፣ የሕዝብ ግንኙነትና የመረጃ ዳይሮክቶሬት ዳይሬክተር ወይዘሮ እልፍነሽ ወልደየስ ለሪፖርተር ገለጹ፡፡

(በውድነህ ዘነበ) በቅርቡ ተቋቁሞ አትክልት ተራን በድጋሚ ለመገንባት አክሲዮን መሸጥ የጀመረው ቢስ አትክልትና ፍራፍሬ አግሮ ኢንዱስትሪ፣ የአሁኑ የአትክልት ተራ ሲፈርስ፣ ከቴዎድሮስ አደባባይ ፊት ለፊት የሚገኘው ክፍት ቦታ በተለዋጭነት ለአትክልት ንግድ እንዲፈቀድ ጠየቀ፡፡

– ዘንድሮ 50 ሚሊዮን ዶላር ታቅዶ 21 ሚሊዮን ዶላር ብቻ ነው የተገኘው (በውድነህ ዘነበ) በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ከጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪ የተገኘው ገቢ ከዕቅድ በታች ቢሆንም፣ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በሚቀጥለው የበጀት ዓመት ተጨማሪ ምርት ያስገኛሉ ያላቸውን ሦስት የጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካዎች ታሳቢ …

በመጪው ዓመት ከጨርቃ ጨርቅ ዘርፍ 85 ሚሊዮን ዶላር ይጠበቃል Read more »

(በኃይሌ ሙሉ) ሐምሌ 24 ቀን 2002 ዓ.ም. ኮልፌ በተለምዶ 18 ማዞሪያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የደረሰው የመኪና አደጋ፣ በአሽከርካሪው የአነዳድ ችግር ምክንያት የተከሰተ መሆኑን የአዲስ አበባ ትራፊክ ፖሊስ ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ገለጹ፡፡

(በአሥራት ሥዩም) የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኤጀንሲ በአዲስ አበባና በአካባቢዋ የሚታየውን የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ክምችት፣ ወደ ሌሎች ክልሎች ለማሠራጨት የሚያስችል የኢንቨስትመንት ማበረታቻ በሥራ ላይ ለማዋል መዘጋጀቱን አስታወቀ፡፡

(በውድነህ ዘነበ) ከሚቀጥለው ሰኞ ጀምሮ የመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት በአዲስ አበባና በድሬዳዋ ከተሞች፣ እንዲሁም በዘጠኙም ክልሎች በአገሪቱ ተግባራዊ በሚደረገው የአምስት ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ ላይ ሕዝቡን ለማወያየት ሊንቀሳቀሱ ነው፡፡