የቪዛ ካርድ አገልግሎት ሰጪ ባንኮች ማሽኖቻቸውን ሊያስፈትሹ ነው
(በአሥራት ስዩም)
የቪዛ ካርድ ክፍያ አገልግሎት በመስጠት ላይ ያሉና ለመስጠት ዝግጅታቸውን ያጠናቀቁ ባንኮች፣ ከዓለም አቀፉ የቪዛ ካርድ ኩባንያ በመጡ ባለሙያዎች የክፍያ ሥርዓቱ የደኅንነት ደረጃውን የጠበቀ እንዲሆን ለማስቻል በሳምንቱ መጀመሪያ ላይ ሥልጠና የተሰጣቸው ሲሆን፣ በቀጣይነትም የአውቶማቲክ ገንዘብ መክፈያ (ATM) ማሽኖቻቸውን እንደሚያስፈትሹ ታውቋል፡፡