የሰንደቅ ዓላማ ቀን
ባለፈው ሰኞ ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት ሲሆን በመላ አገሪቱ በኢትዮጵያ ሕዝብ መዝሙር በመታጀብ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ የመስቀል ሥነ ሥርዓት ተካሂዷል፡፡ በአዲስ አበባ ስታዲዮም የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አቶ ደግፌ ቡላ የሰንደቅ ዓላማ የመስቀል ሥነ ሥርዓቱን የመሩ ሲሆን፣ ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደ ጊዮርጊስን ጨምሮ የክልል ፕሬዚዳንቶች፣ የፌዴሬሽንና የሕዝብ ተወካዮች አፈ ጉባዔዎች፣ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታ ማዦር ሹም፣ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባና ሌሎች ሹማምንት ለሰንደቅ ዓላማው ክብር ቃለ መሐላ አድርገዋል፡፡ ለሦስተኛ ጊዜ የተዘከረውን የሰንደቅ ዓላማ ቀንን ሥነ ሥርዓት በተመለከተ የተዘጋጀውን ዘገባ በፖለቲካ በገጽ ላይ ይመልከቱ፡፡