ማጂክ ካርፔት ትምህርት ቤት ያስገነባው ሕንፃ በግብረ ኃይል ፈረሰ

(በብርቱካን ፈንታ)

ማጂክ ካርፔት ትምህርት ቤት ለመዋዕለ ሕፃናት ማስተማሪያነት አስገንብቶ ለሁለት ዓመታት አገልግሎት ሲሰጥበት የቆየው ሕንፃ፣ ሕገወጥ ግንባታ ነው በሚል ባለፈው ማክሰኞ በግብረ ኃይል የፈረሰ ሲሆን፣ ትምህርት ቤቱ በበኩሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፈቅዶ የሰጠኝ ቦታ ነው ብሏል፡፡