የኢሕአዴግ ስምንተኛ ድርጅታዊ ጉባዔ ዛሬ ይጀመራል
– ከ1600 በላይ የጉባዔው ታዳሚዎች አዳማ ከተዋል
(በውድነህ ዘነበና አስራት ሥዩም)
ከአዲስ አበባ በስተምስራቅ 100 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኘው አዳማ ዛሬ የሚጀመረውን የኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) ስምንተኛ ድርጅታዊ ጉባዔ ለመታደም የመጡ ከ1600 በላይ ተሰብሳቢዎችን ታስተናግዳለች፡፡