ለጨረታ የቀረበው የላንጋኖ በቀለ ሞላ ሆቴል ገዥ አጣ

(በኃይሌ ሙሉ)

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለጨረታ ያቀረበው የላንጋኖ በቀለ ሞላ ሆቴል ገዥ አጣ፡፡ ባንኩ የሆቴሉን የሚንቀሳቀሱና የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች ሳይጨምር ሕንፃውን ብቻ ለጨረታ ማቅረቡ ገዥ አሳጥቶታል የሚል እምነት እንዳላቸው የሆቴሉ ሥራ አስኪያጅ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡