ግንባታው አምስት ዓመታት የፈጀው ፔኒሲዮን ‹‹ሕገወጥ›› በሚል እንዲፈርስ ተደረገ

– ባለሀብቱ ከሦስት ሚሊዮን ብር በላይ አውጥቼበታለሁ ይላሉ

(በምዕራፍ ብርሃኔ)

በወረዳ 12 ኮተቤ መምህራን ኮሌጅ አካባቢ በአምስት ዓመታት ውስጥ ተገንብቶ ያለቀ 26 መኝታ ክፍሎች ያሉት ባለሁለት ፎቅ ፔኒሲዮን ‹‹ሕገወጥ ግንባታ ነው›› በሚል መስከረም 3 ቀን 2003 ዓ.ም. በወረዳው ደንብ አስከባሪዎች ፈረሰ፡፡