ለቡና አምራች ገበሬዎች ብድር ለመስጠት የሚያስችል የ10 ሚሊዮን ዶላር ዋስትና ተገኘ

(በብርቱካን ፈንታ)

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ አነስተኛ ቡና አምራች ለሆኑ 63 ማኅበራት ብድር ለመስጠት የዓለም ባንክ አካል ከሆነው ዓለም አቀፉ የፋይናንስ ድርጅት /አይኤፍሲ/ የ10 ሚሊዮን ዶላር ዋስትና አገኘ፡፡