የመኪና አለማማጆች መኪኖቻቸውን በማሠልጠኛ ተቋሞች ሥር አስመዝግቡ መባላቸውን ተቃወሙ
– ለትራንስፖርትና መገናኛ ሚኒስትሩ ቅሬታቸውን በደብዳቤ አስታወቁ
(በታምሩ ጽጌ)
በፌዴራል ትራንስፖርት ባለሥልጣን የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ባለሥልጣን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አቃቂ በሚገኘው የመንጃ ፈቃድ ማውጫና ማለማመጃ ማዕከል ውስጥ የሚገኙትን የአውቶሞቢል ባለንብረቶች፣ ተሽከርካሪዎቻቸውን በማሠልጠኛ ተቋማት ሥር እንዲያስመዘግቡ ያስተላለፈውን መመሪያ ተቃወሙ፡፡