(በቃለየሱስ በቀለ) በቅርቡ ኡጋንዳ ውስጥ ከፍተኛ መጠን ያለው የተፈጥሮ ድፍድፍ ነዳጅ ያገኘው ቱሎው ኦይል የተሰኘው ታዋቂ የእንግሊዝ ኩባንያ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ በደቡብ ኦሞ አካባቢ በነዳጅ ፍለጋ ሥራ ለመሠማራት መወሰኑን አስታወቀ፡፡

(በታምሩ ጽጌ) የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ አንድነት ንቅናቄ (ኢዴአን)፣ መላው የኦሮሞ ሕብረት ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (መኦሕዴፓ)፣ የኦሮሞ ብሔራዊ ኮንግረስ (ኦብኮ) እና የመላው ኢትዮጵያ ብሔራዊ ንቅናቄ (መኢብን) በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 39 እና በመሬት ባለቤትነት ጉዳይ ሳይስማሙ ከነልዩነቶቻቸው (40 በመቶ) ጥምረት መፍጠራቸውን ጳጉሜ 1 ቀን …

አራት የፖለቲካ ፓርቲዎች በአንቀጽ 39 እና በመሬት ጉዳይ ሳይስማሙ ጥምረት ፈጠሩ Read more »

(በጋዜጣው ሪፖርተር) የኦሮሞ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦሕዴድ) ጠቅላላ ጉባዔ በ6ኛ መደበኛ ጉባዔው አቶ አለማየሁ አቶምሳን የድርጅቱ ሊቀመንበር እንዲሆኑ ከትናንትና በስቲያ መርጦአቸዋል፡፡

(በኃያል ዓለማየሁ) ከኢትዮጵያ ኤርፖርቶች ድርጅት ቅጥር ግቢ ውስጥ ሐምሌ 23 ቀን 2002 ዓ.ም. ተሰርቀው የነበሩት ሁለት የባለሥልጣናት ተሽከርካሪዎች፣ ፖሊስ ባደረገው ክትትል ከትናንት በስቲያ ሰኞ ዕለት መገኘታቸውን የድርጅቱ የሕዝብ ግንኙነት ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ጋሻው አባተ ለሪፖርተር አስታወቁ፡፡

(በውድነህ ዘነበ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በተያዘው የበጀት ዓመት የያዘውን ከፍተኛ የገቢ ዕቅድ ለማሳካት በሚል ወ/ሮ በላይነሽ ተክላይን የከተማው ገቢዎች ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አድርጎ ሾመ፡፡

(በታምሩ ጽጌ) የመንግሥት ማህተሞችን ወደ ሐሰተኛነት በመለወጥና የሕዝብ አገልግሎት ወይም የግል ድርጅቶችን ማህተም ያለአግባብ በመስራትና በመለወጥ ተግባር ላይ በመሰማራት፣ በአገር ደኅንነትና ሰላም፣ በትምህርት ሥርዓቱና በፍትሕ ሥርዓቱ ላይ ከባድ ተፅዕኖ ሊያደርስ ነበር የተባለ ግለሰብ በዘጠኝ ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጣ፡፡

የሰሞኑ ድንገተኛ የምንዛሪ ለውጥ የብርን የመግዛት አቅም በ22 በመቶ አውርዶታል፡፡ የምንዛሪ ለውጡ ገበያው ውስጥ መደነጋገርና ትርምስም ፈጥሯል፡፡ ከውጭ የሚገቡ የፋብሪካ ውጤቶች ዋጋቸው በአንድ ጊዜ የማይቀመስ ሆኗል፡፡ በምንዛሪ ለውጡ ዙሪያ ነጋዴዎች፣ ሸማቾች፣ የኮሚሽን ሠራተኞች፣ የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎችና ባለሙያዎች አስተያየታቸው የተካተተበትን የሳምንቱን …

የምንዛሪ ለውጡ መዘዞች Read more »

– ተቋማቱ ከቴክኒክና ሙያ ወደ ፖሊ ቴክኒክ እንዲሸጋገሩ ተነገራቸው (በምሕረት ሞገስ) የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ማኅበር አዲስ የወጣውና ተቋማቱን የርቀት፣ የሕግና የመምህራን ትምህርት ከመስጠት የሚገድበው አዲስ ሥርዓት አግባብ አይደለም ሲል ለትምህርት ሚኒስቴር ባቀረበው አቤቱታ ላይ፣ ከሚኒስቴሩ ጋር ቢወያዩም ሊስማሙ አልቻሉም፡፡

(በታምሩ ጽጌ) የጋምቤላ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ አንድነት ፓርቲ (ጋሕዴአፓ) ነሐሴ 26 እና 27 ቀን 2002 ዓ.ም. ባደረገው ስብሰባ ላለፉት ሁለት የምርጫ ዘመናት ይመሩ የነበሩት ኃላፊዎች በድጋሚ መመረጣቸው፣ አግባብነት የሌለውና የዴሞክራሲ መንገድን የተከተለ አለመሆኑን አንዳንድ የፓርቲው አባላት ለሪፖርተር ገለጹ፡፡

(በኃይሌ ሙሉ) ከአፍሪካ ወርቅ ቤት በሕገወጥ መንገድ ወደ ውጭ ሊወጣ ሲል እንዲያዝ ለጠቆሙና ወርቁን በመያዝ ሒደት ላይ ለተሳተፉ ግለሰቦች ከሁለት ሚሊዮን ብር በላይ ሽልማት በመንግሥት መሰጠቱ ታወቀ፡፡

– ለ2003 የበጀት ዓመት 12.9 ቢሊዮን ብር በጀት ተይዞለታል (በውድነህ ዘነበ) በመስከረም 2003 ዓ.ም. ይፋ በሚደረገው የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ ቤቶች መዋቅር፣ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን በሁለት መንግሥታዊ ተቋማት ሥር እንደሚደራጅ ታወቀ፡፡

– ከ80 ሚሊዮን ቶን በላይ ክምችት እንዳለ ይገመታል– ቢኤችፒ የተባለ ኩባንያ 10 ሚሊዮን ዶላር ወጪ አድርጓል (በቃለየሱስ በቀለ) በአፋር ክልላዊ መንግሥት በዳሎል አካባቢ መጠነ ሰፊ የሆነ የፖታሽና ሌሎች ማዕድናት ፍለጋ ሥራ በመካሄድ ላይ እንደሆነ ታወቀ፡፡

ትዕግሥት ዘሪሁን | ሪፖርተር በቅርቡ ከሐረር ወደ አዲስ አበባ እንደመጡ የሚናገሩት ወ/ሮ ከድጃ አብዱላህ፣ ባለፈው ዓርብ ከሰዓት በኋላ ምጥ ይዟቸው የወሊድ አገልግሎት ለማግኘት ወደ ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ቢሄዱም፣ ካርድ ከወጣላቸው በኋላ ለአገልግሎቱና ለጓንት የሚከፍሉት ገንዘብ ስላልነበራቸው ተባረው መንገድ ላይ መውለዳቸውን …

‹‹ገንዘብ የለሽም ተብዬ ከሆስፒታል ተባረርኩ›› ያሉ ነፍሰጡር መንገድ ላይ ተገላገሉ Read more »

– በዳሸን ባንክ ፕሬዚዳንት ላይ የተላለፈው የእስር ትእዛዝ ታገደ (በኃይሌ ሙሉ) ከአዲስ አበባ ወደ ወላይታ ሶዶ የተዛወርኩበት በሕጋዊ መንገድ አይደለም በማለት በዳሸን ባንክ ላይ ክስ መስርተው በመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የተወሰነላቸው የቀድሞው የባንኩ የሠራተኛ ማኅበር ሊቀመንበር ከሥራ ተባረሩ፡፡

‹‹አዲሱ የትራንስፖርት ታሪፍ እኛንም ተገልጋዩንም እየጐዳ ነው››  የሕዝብ ማመላለሻ የተሽከርካሪ ባለንብረቶች ‹‹ታሪፉ በዝቷል፣ አንሷል ለማለት የግድ ትግበራውን መገምገም አለብን›› የኦሮሚያ ክልል ትራንስፖርት ቢሮ (በብርቱካን ፈንታ)

ሰሞኑን ማንነታቸው ከማይታወቁ የሞባይል መስመሮች፣ ድረ ገጾች፣ ኤሜልና የሞባይል አጭር የጽሑፍ መልዕክቶች (SMS) አደገኛ የሞባይል ፍሪኩዌንሲ በጤና ላይ አደጋ ያደርሳል ተብሎ የሚናፈሰው ወሬ መሠረተ ቢስ መሆኑን፣ የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሽን አስታወቀ፡፡ ኮርፖሬሽኑ ዛሬ ለሪፖርተር በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፣ በዓለም ኅብረተሰብ ዘንድ ሆን …

ቴሌ በጤና ላይ አደጋ ያደርሳል የተባለው የሞባይል ፍሪኩዌንሲ ሀሰተኛ መረጃ ነው አለ Read more »

የትምህርትና ስልጠና ጥራት ማረጋገጫ ኤጀንሲ ለ2003 ዓ.ም. የትምህርት ዘመን አዲስ ተማሪዎችን ለመቀበል የሚወጣ ማንኛውንም ማስታወቂያ በቴሌቪዥን፣ በሬድዮ ወይንም በጋዜጣ እንዳይተላለፍ ከለከለ፡፡

– ባለአራትና ባለአምስት ኮከብ ሆቴሎች ይገነባሉ – የሄሊኮፕተር ማረፊያ ይኖዋል– ግንባታው በሦስት ዓመት ተኩል ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃል– መንግሥት የ20 በመቶ ድርሻ አለው – ዓለም አቀፉ ኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴሉን ያስተዳድራል – ሆቴሉ  ለፕሬዚዳንቶች ልዩ ማረፊያዎች ይኖሩታል (በኃይሌ ሙሉ) አክሊለ ብርሃን መኮንን ኃይለ …

ኢትዮጵያዊው ባለሀብት ግዮን ሆቴልን በሰባት ቢሊዮን ብር ሊገነቡ ነው Read more »

– የአንድ ዶላር መመንዘሪያ የመነሻ ዋጋ ብር 16.35 ሆነ (በጋዜጣው ሪፖርተር) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከዛሬ ጀምሮ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ16.3514 ብር ግዢ፣ በ16.6784 ሽያጭ እንዲመነዘር መመሪያ አወጣ፡፡ የምንዛሪ ለውጡ የብር የመግዛት አቅምን (ከሌሎች ገንዘቦች አንጻር) ከ22 በመቶ በላይ ያወርዳል፡፡

– ከ300 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ አውጥቷል (በታምሩ ጽጌ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በአገልግሎት ላይ የሚገኘውን ባለ አንድ ብር የወረቀት ገንዘብ ለመተካት ያሠራቸውን ባለ አንድ ብር ሣንቲሞች ለመንግሥትና ለግል ንግድ ባንኮች ነሐሴ 19 እና 21 ቀን 2002 ዓ.ም. ማሠራጨቱን ምንጮች ለሪፖርተር …

ብሔራዊ ባንክ ያሠራቸውን ባለ አንድ ብር ሣንቲሞች ለንግድ ባንኮች አሠራጨ Read more »

– ‹‹መንግሥት ከዚህ በኋላ ምንም ዓይነት የይቅርታ ጥያቄ አይቀበልም›› አቶ ታደለ ይመር (በብርሃኑ ፈቃደ) የኢትዮጵያ አሠሪዎች ፌዴሬሽን 10 ያህል ሆቴሎች ከቀረጥ ነፃ የገቡ ዕቃዎችን ያለ ፈቃድ በመሸጥ፣ ታክስ ባለመክፈልና ለሌላ ተግባር በማዋላቸው በወንጀል እንደሚጠየቁና ክስ እንደሚመሠረትባቸው ቢታወቅም፣ በሆቴሎቹ ስም ፌዴሬሽኑ …

አሠሪዎች ፌዴሬሽን በሆቴሎች ስም መንግሥትን ይቅርታ ጠየቀ Read more »

. ዕቃዎች በማዕከል ተገዝተው ለግል ተቋራጮች ይቀርባሉ. የመንግሥት የኮንስትራክሽን ኩባንያዎች ወደ ዘርፉ ይገባሉ. 80 አዳዲስ የግል ሥራ ተቋራጮች ሥራ ያገኛሉ (በውድነህ ዘነበ) የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን የግንባታ ዋጋ ንረት ለመቆጣጠር ያስችለኛል ያለውን አዲስ የዋጋ ንረት መቆጣጠርያ ዕቅድ አዘጋጀ፡፡

– የመተዳደሪያና የሥነ ምግባር ደንብ አርቅቀዋል (በታምሩ ጽጌ) የኦሮሞ ብሔራዊ ኮንግረስ (ኦብኮ)፣ የመላው ኢትዮጵያውያን ብሔራዊ ንቅናቄ (መኢብን)፣ የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ አንድነት ንቅናቄ (ኢዴአን) እና የመላው ኦሮሞ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (መኦህዴፓ) ከነሐሴ 25 ቀን 2002 ዓ.ም. ጀምሮ በጥምረት ለመንቀሳቀስ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን …

ኦብኮ፣ መኢብን፣ ኢዴአንና መኦህዴፓ ጥምረት ለመፍጠር ተስማሙ Read more »

የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ የፈሰሰበት፣ ከግብርናው ዘርፍ ቀጥሎ በርካታ የሰው ኃይል የተሰማራበትና በአገሪቱ ውስጥ ካሉ ሌሎች የኢኮኖሚው ዘርፎች ከፍተኛ ትኩረትን የሳበ ነው፡፡ ዘርፉ በአገሪቱ የመሠረተ ልማት እንቅስቃሴዎች ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያደረገ የሚገኝ ቢሆንም በበርካታ ችግሮች የተተበተበ ነው፡፡ ቀጣዩ ልዩ …

የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ፈተናዎችና ገመናዎች Read more »

–  የመንግሥትም ሆነ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በቅድመና በድኅረ ምረቃ የርቀት ትምህርት አይሰጡም–  የሕግና የመምህራን ትምህርት በግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መሰጠት ይቆማል –  ‹‹ሥርዓቱ ሙሉ ለሙሉ የትምህርቱን ዘርፍ የሚገድብ ነው›› ረዳት ፕሮፌሰር ወንድወሰን ታምራት– ‹‹ግብታዊ ውሳኔ ነው፤ የአቤቱታ ደብዳቤ እናስገባለን›› …

የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ የወጣው መመሪያ ተቃውሞ ገጠመው Read more »

(በውድነህ ዘነበ) ቦታ ወስዳችሁ ግንባታ አላካሄዳችሁም በሚል ካርታቸው እንዲመክን የተደረገባቸው የሪል ስቴት አልሚዎች፣ ቅሬታቸውን ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ ቢሮ ማቅረብ ጀመሩ፡፡

‹‹የ40 ዓመት ዕድሜ እያለን ስማችንን ተነጥቀናል››  (የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያዎች ማኅበር)‹‹የኢትዮጵያ ጠበቆች ማኅበር የሚባል ከእኛ በፊት አልነበረም››  (የኢትዮጵያ ጠበቆች ማኅበር) ‹‹ሙያውና ስያሜው አንድ ዓይነት ያልሆነ ማኅበር ፈቃድ ሊሰጠው አይችልም››  (የኢትዮጵያ የበጎ አድራጎትና ማኅበራት ኤጀንሲ) (በብርቱካን ፈንታ) የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያዎች ማኅበርና የኢትዮጵያ …

ጠበቆች ለተመሳሳይ ዓላማ ሁለት ስያሜ ይዘው እየተወዛገቡ ነው Read more »

(በሔኖክ ያሬድ) ኢትዮጵያ በዓለም አቀፉ የቱሪዝም ገበያ ፉክክር ውስጥ ብቁ ተወዳዳሪ ለመሆን በሚያስችላት የቱሪዝም ፖሊሲዋ አማካይነት አሁን ያለውን የ13.5 በመቶ አማካይ የቱሪስት ፍሰትን ከ20 በመቶ በላይ ለማሳደግ መታቀዱን፣ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ በሥራ ላይ ያለው የባህል ፖሊሲንም እንደሚያሻሽለውም ገለጸ፡፡

(በኃይሌ ሙሉ) በአራዳ ክፍለ ከተማ ገቢዎች ቢሮ ትዕዛዝ ማንኛውም ተንቀሳቃሽና የማይንቀሳቀስ ንብረታቸው እንዲታገድ ለባንክ የተጻፈባቸው ዶ/ር አሸብር ወልደ ጊዮርጊስ፣ ከግብር ጋር በተያያዘ ንብረታቸው እንዲታገድ መደረጉ አግባብ አለመሆኑንና ጥሩ ግብር ከፋይ መሆናቸውን ለሪፖርተር ገለጹ፡፡

– ኢንስቲትዩቱ በአምስት የአፍሪካ አገሮች ቅርንጫፉን ሊከፍት ነው (በብርቱካን ፈንታ) የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ሚኒስትሩን አቶ በረከት ስምዖንን ጨምሮ ሚኒስትሮችና ባለሥልጣናት ከኢንተርናሽናል ሊደርሽፕ ኢንስቲትዩት በትራንስፎርሜሽናል ሊደርሽፕ ኤንድ ቼንጅ በድኅረ ምረቃ በቅርቡ እንደሚመረቁ ተገለጸ፡፡

(በትዕግሥት ዘሪሁን) ምንም ዓይነት ወንጀል ሳይፈፅሙ ‹‹የሲአይኤ ሰላይ ናችሁ፤ ፈላሾች ናችሁ፤›› በሚል ለስምንት ዓመታት ያህል ያለክስና ያለፍርድ በሊቢያ መንግሥት ታስረው የቆዩ ኢትዮጵያውያን፣ በመንግሥት ትብብር ከ10 ዓመት በፊት ወደ አገራቸው ቢመለሱም፣ እስካሁን ድረስ በኤግዚቢትነት የተያዘ ንብረታቸው አለመመለሱን፣ በይፋ ይቅርታ እንዳልተጠየቁና ያለፍርድ …

በሊቢያ ለስምንት ዓመታት በግፍ ታስረን ነበር ያሉ ዜጐች መብታችን ይከበር እያሉ ነው Read more »

– ሕንጻው በቅርቡ ይመረቃል ተብሎ ይጠበቃል (በኃያል ዓለማየሁ) የናኒ ሕንጻ ግንባታ ለረጅም ዓመታት በመዘግየቱ ሕንጻውን በባለቤትነት የሚገነባውን የሚድሮክ ኢትዮጵያ እህት ኩባንያ የሆነውን ሁዳ ሪል እስቴትን ከ360 ሚሊዮን ብር በላይ ሊያስወጣው መቻሉን ለፕሮጀክቱ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ለሪፖርተር ገለጹ፡፡

‹‹ለአፈርና ለዘር ጥበቃ ትኩረት ሊሰጥ ይገባል››ዶ/ር ተወልደ ብርሃን ገብረ እግዚአብሔር. ምግብ አምራቹ ኢንዱስትሪ ደካማና ብቃት የሌለው ተብሎ ተተቸ(በብርሃኑ ፈቃደ) የግብርና ዘርፍ የዓለምን የብዝኅ ሕይወትና የሰብል ዘር አመናምኗል ተባለ፡፡

ከሪፖርተር በመለስ ዜናዊ የሚመራው የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) ከሁለት ዓመት በፊት በሰባተኛ ጉባዔው የነደፋቸው ዕቅዶች ከሞላ ጎደል የተሳኩ መሆናቸውን አሳወቀ፡፡ ድርጅቱ አሁን ያለው የግንባርነት አደረጃጀት የላቀ ውጤት ያስገኘለት መሆኑን ስላመነበት ወደ ሌላ ደረጃ (ውህደት) የመሸጋገር ጥያቄ በስምንተኛ ጉባዔው …

ኢሕአዴግ በግንባርነት ለመቀጠል ወሰነ Read more »

– ከ61 ሜጋ ዋት በላይ የሚያመነጨው ትራንስፎርመር ተቃጥሏል (በውድነህ ዘነበ) የጊቤ አንድ የኃይል ማመንጫ ጣቢያ ካሉት ሦስት ትራንስፎርመሮች መካከል አንዱ በመቃጠሉ፣ ግድቡ የያዘውን የክረምት ውኃ በሙሉ አቅሙ መጠቀም ባለመቻሉ የተለቀቀው ውኃ ጎርፍ ሆኖ በአካባቢው ነዋሪዎች ላይ መፈናቀልን አስከትሏል፡፡

– በአካባቢው ጥናት ለማካሄድ 6.5 ሚሊዮን ዶላር መድቧል (በቃለየሱስ በቀለ) አፍሪካ ኦይል የተሰኘ ተቀማጭነቱ በቫንኮቨር ካናዳ የሆነ የነዳጅ ኩባንያ፣ በደቡብ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በደቡብ ኦሞ ሸለቆ የነዳጅ ፍለጋ ሥራ የሚያካሂድበትን መሬት መረከቡን አስታወቀ፡፡

(በውድነህ ዘነበ) ከብዙ አለመግባባቶች በኋላ ባለፈው ቅዳሜ በተካሄደው የአንበሳ ባንክ ባለአክሲዮኖች ስብሰባ፣ በድጋሚ የቦርድ አባላት ምርጫ የተካሄደ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የተመረጡትን ሰዎች ብቃት ከመረመረ በኋላ በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ ውጤቱን ያሳውቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

(በኃይሌ ሙሉ) በሰሜን ወሎ ዞን መርሳ ከተማ ነሐሴ 17 ቀን 2002 ዓ.ም. ከሌሊቱ ዘጠኝ ሰዓት ገደማ በደረሰ የመሬት መንሸራተት አደጋ 14 ሰዎች ሲሞቱ 25 ሰዎች ቀላልና ከባድ የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል፡፡

ከሪፖርተር ከባህር ዳር ወደ ጐንደር በሚወስደው መንገድ እንፍራንዝ የሚባለው ወንዝ ላይ የተገነባው ድልድይ በደረሰበት የመደርመስ ጉዳት የትራንስፖርት እንቅስቃሴ መስተጓጐሉ ተገለጸ፡፡ በአካባቢው የነበሩ የዓይን እማኞች እንደጠቆሙት፣ በድልድዩ ላይ በአንድ ወገን በተፈጠረ መደርመስ ካሳለፍነው እሑድ ጀምሮ በባህር ዳርና በጐንደር ከተሞች መካከል ግንኙነት …

ድልድይ በመደርመሱ የባህር ዳር ጐንደር የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ተስተጓጐለ Read more »

(በአስራት ሥዩም) ዋነኛ የገቢ እና የወጪ ንግድን የሚያስተናግደውና የጅቡቲ ወደብን  ከአገሪቱ ከተሞች ጋር የሚያገናኘው መንገድ ላይ የሚገኙ ሁለት ድልድዮች በጐርፍ ጉዳት ደረሰባቸው፡፡

ከሪፖርተር ተሰናባቹ የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክር ቤት በሐምሌ ወር መጨረሻ ጉባዔው ባደረገው ግምገማ፣ የክልሉን ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ አቶ ኃይለ አብርሃን ከሥልጣናቸው ካነሳቸው በኋላ እንዲከሰሱ ወሰነ፡፡ በአሁኑ ወቅት በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ከተለያዩ ምንጮች ለማወቅ ተችሏል፡፡ ምክር ቤቱ አደረገ በተባለው …

የትግራይ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ታሰሩ Read more »

(በታምራት ጌታቸውና በኃያል ዓለማየሁ) ከአዲስ አበባ በስተምሥራቅ 200 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው መተሐራ ከተማ የበሰቃ ሐይቅ ውኃ ሙላት ከምንጊዜውም በላይ ሥጋት መፍጠሩን በአካባቢው የተገኙት ሪፖርተሮቻችን ለማየት ችለዋል፡፡

– 211 ሺሕ 200 ብር የገንዘብ ቅጣት ተጥሎባቸዋል (በታምሩ ጽጌ) የኢትየጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዓቃቤ ሕግ በ2001 ዓ.ም. መጨረሻ አካባቢ ክስ የመሠረተባቸው አራጣ አበዳሪው አቶ ገብረ ኪዳን በየነ (ሞሮኮ)፣ በ21 ዓመት ጽኑ እሥራትና የ211 ሺሕ 200 ብር የገንዘብ ቅጣት እንዲቀጡ …

አራጣ አበዳሪው ገብረ ኪዳን በየነ (ሞሮኮ) የ21 ዓመት ጽኑ እሥራት ተፈረደባቸው Read more »