ሊንከን ዩኒቨርሲቲ ኢትዮጵያ ውስጥ የማታ ትምህርት ጀመረ

– አንድ ተማሪ 7,000 ዶላር መክፈል ይጠበቅበታል

(በመርጋ ዮናስ)

የካሊፎርኒያው ሊንከን ዩኒቨርሲቲ በማስተርስ ኦፍ ቢዝነስ ኤንድ አድሚኒስትሬሽን (ኤምቢኤ) ፕሮግራም ካለፈው ማክሰኞ መስከረም 12 ቀን 2003 ዓ.ም. ጀምሮ ኢትዮጵያ ውስጥ በይፋ ማስተማር ጀመረ፡፡