ንግድ መርከብ ለሚገዛቸው ዘጠኝ መርከቦች ከቻይና ባንክ ጋር የ234.7 ሚሊዮን ዶላር ብድር ተፈራረመ

– ከእስራኤል ኩባንያ ጋር በመተባበር የማሪን አካዳሚ ይከፍታል

(በኃያል ዓለማየሁ)

በአገሪቱ ብቸኛው የባሕር ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ መርከብ፣ በቻይና ኩባንያ ለሚያሠራቸው ዘጠኝ መርከቦች ከቻይና ኤግዚም ባንክ (China Exim Bank) ጋር የ234.7 ሚሊዮን ዶላር የብድር ስምምነት ተፈራረመ፡፡