ቡና ባንክ አነስተኛ ብድሮችን እንደሚሰጥ አስታወቀ

በቅርቡ ወደ ሥራ ከገቡት ባንኮች አንዱ የሆነው ቡና ባንክ ከተለመደው የንግድ ባንኮች አሠራር ወጣ ባለ መንገድ፣ ዝቅተኛ መጠን ያላቸው እስከ 1,000 ብር ወይም ከዚያ በታች ሊደርሱ የሚችሉ ብድሮችን ለመስጠት ማቀዱን የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ እሸቱ ፋንታዬ ገለጹ፡፡