የጤፍ ምርት ኢትዮጵያንና ኔዘርላንድን እንዳያጋጭ ተሰግቷል

ከጤፍ ዱቄት ብስኩት፣ ኬክና ዳቦ እያመረተ ለአውሮፓ ገበያዎች የሚያቀርበው የኔዘርላንድ ኩባንያ፣ ከስሬያለሁ በሚል ኢትዮጵያ ማግኘት ያለባትን ገቢ በመከልከሉ የሁለቱን አገሮች ግንኙነት እንዳያበላሽ ስጋት ፈጥሯል፡፡