ያበራ ለማ የዲቪዲ ግጥሞች (ዓለማየሁ ታዬ)
ይድረስ ለሥነኪን ሃዋርያው
ዓለማየሁ ታዬ [email protected]
ከጥቂት ወራት በፊት ይድረስ ለሥነኪን ተጠባቢው ዓለማየሁ ታዬ ካለህበት ብለህ በኢትዮጵያ ዛሬ ድረ ገፅ በኩል ላደረስከኝ ኪናዊ ጦማር ምላሹን ያዘገየሁት ዲቪዲህ በሰሜን አሜሪካ እስኪመረቅ በመጠበቅ ነበር። ቦ ጊዜ ለኩሉ እንዲል ጠቢቡ ሠለሞን የጁላይ አስሩን ምረቃ በማሰብ የኪናዊ ጦማርህን ምላሽ ተደረሰኝ።