ዓቃቤ ሕግ በሽብር ወንጀል ተከሳሾች ላይ ምስክሮቹን አሰምቶ ጨረሰ
የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ፣ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአሸባሪ ድርጅትነት በተፈረጀው ግንቦት 7 ድርጅት ውስጥ ጥምረት በመፍጠር፣ አመራርና አባል በመሆን፣ የሽብር ድርጊቶችን ለመፈጸም በማሴር፣ በማቀድ፣ በማነሳሳትና በማዘጋጀት ወንጀል ተጠርጥረው በተከሰሱና በአገር ውስጥ ሆነው ክሳቸውን በመከታተል ላይ ባሉ ስምንት ተጠርጣሪዎች ላይ የጠራቸውን ምስክሮች በትናንትናው ዕለት አሰምቶ ጨረሰ፡፡