መንግስት ኮሚቴዎቻችንና ቤተሰቦቻቸውን በቃሊቲ ማወከብ መቀጠሉ ታወቀ ። ሬዲዮ ዳንዲ ሀቃ ጥር 11 /2008 የህዝበ ሙስሊሙን የመብትጥያቄ : ይዘው መፍትሄ ለማፈላለግ በመንቀሳቀሳቸው ብቻ በአምባገነኑ ስርአት እጅ ወድቀውና : በመንግስታዊው የካንጋሮ ፍርድ ቤት ጥፋተኛ ተብለው : ከሰባት አመት እስከ ሀያ ሁለት …

መንግስት የህዝበ ሙስሊሙን ኮሚቴዎችንና ቤተሰቦቻቸውን በቃሊቲ ማወከብ መቀጠሉ ታወቀ ። Read more »

ኢሳት (ጥር 11 ፥ 2008) ዳግም በኦሮሚያ የተቀሰቀሰው የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ተቃውሞ ረቡዕ በጥምቀት በዓል አከባበር ወቅትም በተለያዩ ቦታዎች ቀጥሎ መዋሉን ከሃገር ቤት የተገኘ መረጃ አመልክቷል። ከቀናት በፊት በምስራቅ ሃረርጌና በምስራቅ ወለጋ አካባቢዎች ሲካሄድ የሰነበተው ተቃውሞ አልባት አለማግኘቱንና የጸጥታ ሃይሎች በስፍራው እርምጃ መውሰድ መቀጠላቸውም ታውቋል። የፌዴራልና የክልል ባለስልጣናት ትምህርት ያቋረጡ ዩኒቨርስቲዎች ትምህራትቸውን እንዲቀጥሉ ጥረታቸውን …

አፈንዲ ሙተቂ

የስራ ግዴታዬ ሆኖ ከህዳር ወር 2007 (November 2014) ጀምሮ በመካከለኛው ዘመን የኢትዮጵያ ታሪክ ዙሪያ የተጻፉ ሰነዶችን እየመረመርኩ ነው፡፡ በዚህም ድሮ የማላውቃቸውን አስደናቂና አስገራሚ ታሪኮች ለማወቅ ችያለሁ፡፡ ለረጅም ጊዜ እንቆቅልሽ ሆነው ሲያስቸግሩኝ ለነበሩት ጉዳዮችም ምላሽ አግኝቻለሁ፡፡ ለብዙ ዓመታት ስፈልጋቸው የነበሩትን ምርጥ መጻሕፍትንም አግኝቼ ይዘታቸውን በቅርበት ለማወቅ ችያለሁ፡፡

 

ታዲያ በዚህ ምርመራዬ ያስተዋልኳቸው ሌሎች ጉዳዮችም አሉ፡፡ ከነርሱም አንዱ አንዳንድ ጮሌዎች ታሪክን በመጻፍ ስም ፖለቲካን የሚያሸከረክሩበት ጥበብ ነው፡፡ ለዚህ ዋቢ ይሆነኝ ዘንድ የአንድ ሀገር ዜጋ የሆኑ ሁለት ምሁራንን ልጥቀስ፡፡

—-

ሞርዴኻይ አቢር (Mordechai Abir) የሚባል ስም ታውቃላችሁ?…. አዎን! ስለ “ዘመነ መሳፍንት” የተጻፉ ጽሑፎችን ያነበበ ሰው “አቢር” የሚለውን ስም በደንብ ያስታውሳል፡፡ እኝህ ሰው የቀድሞው “ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሤ ዩኒቨርሲቲ” (የአሁኑ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ) የታሪክ ፕሮፌሰር ነበሩ፡፡ ደርግ ስልጣን ከተቆጣጠረ በኋላ ደግሞ ወደ እስራኤል በመጓዝ በኢየሩሳሌም በሚገኘው የሂብሩ ዩኒቨርሲቲ መምህርነት አገልግለዋል፡፡ አቢር “The Era of Princes” በሚል ርዕስ የጻፉት መጽሐፍ በምሁራን ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነት አለው፡፡ እኔም በአንድ ወቅት (የዛሬ አስር ዓመት ገደማ) መጽሐፉን አንብቤው ነበር፡፡

 አቢር በጣም ዝነኛ የሆነ ሌላ መጽሐፍም አላቸው፡፡ ርዕሱ “Ethiopia and the Red Sea” ይሰኛል፡፡ በየትኛውም ወገን ሆኖ ስለኢትዮጵያ ታሪክ የሚጽፍ ሰው ይህንን መጽሐፍ እየደጋገመ ይጠቅሳል፡፡ ታደሰ ታምራት፣ ሪቻርድ ፓንክረስት፣ ነጋሶ ጊዳዳ፣ መርዕድ ወልደ አረጋይ፣ ሙሐመድ ሐሠን፣ ላጵሶ ድሌቦ፣ ኡልሪች ብራውኬምፐር፣ አባስ ሐጂ ገነሞ፣ አሌሳንድሮ ጎሪ እና ሌሎችም ፕሮፌሰሮች የአቢርን መጽሐፍ እንደ ምንጭ ይጠቀሙበታል፡፡ ሰለሰሜን ኢትዮጵያም ሆነ ስለደቡቡ ክፍል በተጻፈ መጽሐፍ ውስጥ “Abir” የሚለውን ስም በግርጌ ማስታወሻ እና በመጽሐፉ ማጣቀሻ ክፍል ውስጥ ማየት የተለመደ ነው፡፡ ነገር ግን “Ethiopia and the Red Sea”ን ለረጅም ጊዜ አይቼው ስለማላውቅ በምሁራን ዘንድ ተመራጭ የሆነበትን ምክንያት ለመረዳት ስቸገር ቆይቻለሁ፡፡ ዘንድሮ ግን ፈጣሪ ብሎልኝ  አግኝቼዋለሁ፡፡  ብዙ ጊዜ እየመላለስኩ ካየሁት በኋላም መጽሐፉ በምሁራን ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነት ያገኘበትን ምክንያት ለመረዳት ችያለሁ!!

አዎን! ፕሮፌሰር አቢር ከልቡ ምሁር ናቸው፡፡ እውነተኛ ምሁር! መጽሐፋቸውን ያጠናቀሩት በእውነተኛ ምሁራዊ መንገድ ነው፡፡ ብዙዎችን እንቅ አድርጎ ሊያሰምጣቸው የሚታገላቸው ኢ-ምሁራዊ ሸፍጥና ውንብድና በመጽሐፋቸው ውስጥ የለም፡፡ አድሎ፣ መረጃ ማምታታት፣ የተወላገደ እይታ፣ ማስመሰል፣ መሸፈጥ ጂንኒ ጀቡቲ በመጽሐፉ ውስጥ አይታዩም፡፡ በመሆኑም “Ethiopia and the Red Sea” በህይወቴ ከገጠሙኝ አጃዒበኛ መጻሕፍት መካከል አንዱ አድርጌ መዝግቤዋለሁ፡፡ እውቀትን መገብየት ለሚሻ ሰው ግሩም መማሪያ ነው፡፡ ለተመራማሪዎችና ለተማሪዎች እጅግ በጣም አስፈላጊ የሆነ ማጣቀሻ ነው፡፡

ፕሮፌሰር አቢር በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ስድስት መጻሕፍትን ጽፈዋል፡፡ ሁሉም መጻሕፍት በምሁራን ዘንድ ከፍተኛ ከበሬታ አላቸው፡፡ ከነርሱ መካከል ከላይ የጠቀስኳቸው ሁለት መጻሕፍት የዓለማችን ቁጥር አንድ ኢንሳይክሎፒዲያ በሆነው “ኢንሳይክሎፒዲያ ብሪታኒካ” ቀዳሚ የማጣቀሻ ምንጮች በመሆን recommend ተደርገዋል፡፡

                       

ፕሮፌሰር አቢር እስራኤላዊ ናቸው፡፡ ታዲያ በኢትዮጵያ ታሪክ ላይ ምርምር ሲያደርጉ የነበሩት እስራኤላዊ እሳቸው ብቻ አልነበሩም፡፡ ሌሎችም በዘርፉ ብዙ ስራዎችን አቅርበዋል፡፡ ከነርሱም አንዱ ሀጋይ ኤልሪክ ነው፡፡ “ሐጋይ ኤርሊክ” የሚለውን ስም ካወቅኩ አስራ አምስት ዓመታት አልፏል፡፡ ነገር ግን ከመጽሐፎቹ ያነበብኩት Ethiopia and the Middle East የሚል ርዕስ ያለውን ብቻ ነው፡፡ ሀጋይ ከመጽሐፎቹ ይልቅ በሴሚናሮችና ዓለም አቀፍ ኮንፈረንሶች ላይ የሚያቀርባቸውን በርካታ አጫጭር ጽሑፎችን ነው ያነበብኩት፡፡ ከህዳር 2007 ወዲህ ባለው ጊዜ ውስጥ ግን ሶስት ያህል መጽሐፎቹን አይቼለታለሁ፡፡ እናም አጃዒብ አልኩ!!

  ይገርማል!! ፕሮፌሰር ሃጋይ አወዛጋቢ ሰው ሆኖ ብቅ ያለው በቅርብ ዘመናት በሚጽፋቸው ጽሑፎቹ ይመስለኝ ነበር፡፡ ነገር ግን ሰውየው ከመነሻው ጀምሮ የተወላገደ እይታ ያለው መሆኑን ነው ያስተዋልኩት፡፡ ምሁራዊ ውንብድና በመጽሐፎቹ ውስጥ እግሩን አንሰራፍቷል፡፡ ከሀጋይ መጽሐፍ ፖለቲካ እንጂ አንዳች የታሪክ እውቀት አይጨበጥም፡፡ ደግሞም የብዙዎቹ መጻሕፍት ጭብጥ “ኢትዮጵያ ራሷን ካልጠበቀች በሙስሊም አክራሪዎች ልትዋጥ ትችላለች” የሚል ነው፡፡ ባጭሩ “ሃጋይ” የእስራኤሉ ሞሳድ በኛ ላይ የተከለው የማስፈራሪያ ሳይኮሎጂስት እንጂ የታሪክ ምሁር ሆኖ አልተገኘም፡፡

በጣም የሚገርመው ደግሞ ሃጋይ ሌሎች ፀሐፊዎችን የሚፈርጅበት ድፍረቱ ነው፡፡ አንድን ክስተት ከርሱ በተለየ አኳኋን ለጻፉ የታሪክ ምሁራን በቶሎ ስም ያወጣላቸዋል፡፡ ሰውዬው ክርስቲያን ከሆነ “ኮሚኒስታዊ አስተሳሰብ ስላለው ነው” ይለዋል፡፡ ሙስሊም ምሁራንን ደግሞ ሁለት ሰሞችን ይሸልማቸዋል፡፡ ጸሐፊው የመካከለኛው ዘመን ሰው ከሆነ “Fanatic writer” ይለዋል፡፡ ፀሐፊው የዘመናችን ሰው ከሆነ ግን “Radical Islamist writer” ይለዋል፡፡ ከርሱ የሚቃረን ትርክት የጻፉ ሰዎችን እንዲህ ብሎ በሚፈርጅ ሰው የተጻፈ መጽሐፍ የታሪክ ማጣቀሻ የሚሆንበት አግባብ በጭራሽ የለም፡፡

የሀጋይ የላሸቀ ምሁራዊ በዚህ ብቻ የተገታ አይደለም፡፡ የታሪክ መረጃዎችን ለራሱ እንደሚመቸው እየገለባበጠ ይጽፋል፡፡ ለምሳሌ ቅዱስ ቁርኣን የአማርኛ ትርጉም በብዙ ምሁራን ተሳትፎ የተከወነ ሆኖ ሳለ (ዋነኞቹ ተርጓሚዎች ሼኽ ሰይድ ሙሐመድ ሳዲቅ እና ሃጂ ሙሐመድ ሣኒ ሐቢብ ቢሆኑም) እርሱ ግን “ትርጉሙን ያከናወኑት ሃጂ ዩሱፍ ዐብዱራሕማን ነው” ይለናል፡፡ ሀጋይ እንዲህ የሚለው ሃጂ ዩሱፍን ለማድነቅ እንዳልሆነ ልብ በሉ፡፡ ይህንንም ትረካ የፈጠረው እርሱ በአድናቆት አቅሉን የሚስትላቸው ሼኽ ዐብዱላሂ ሙሐመድ (ዐብዱላሂ አል-ሐበሺ) በ1948 ከኢትዮጵያ የተባረሩት ሃጂ ዩሱፍ ዐብዱራሕማን በዶለቱት ሴራ ነው በሚል ለሚዘበዝበው ትረካ እንደማስረጃ ለመጠቀም ፈልጎ ነው፡፡ አንባቢያን “ሃጂ ዩሱፍ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሤን አባብለው ሼኽ ዐብዱላሂ ከሀገር እንዲጠፉ የማድረግ አቅም ነበራቸው እንዴ” ብለው ሲጠይቁ የሃጋይ ኤርሊክ ጽሑፍ “ሰውዬው እንዲያ ማድረግ ይቅርና በቅቤ ምላሳቸው ንጉሡን በማሳመን ቅዱስ ቁርኣን እንዲተረጎም ያደረጉ ሼኽ ነበሩ” የሚል መልስ ይሰጣቸዋል ማለት ነው፡፡ ይህቺ ነች ዘዴ!! ይህቺ ነች ሸፍጥ!!

በሌላ በኩል ሃጋይ ኤርሊክ በቀጥታ ጠብ ጫሪነትን የሚያንጸባርቁ ጽሑፎችንም ይጽፋል፡፡ ለምሳሌ የሃጋይ አንዱ ጽሑፍ “The Grandchildren of Abraha” የሚል ርዕስ አለው፡፡ አብረሃ ነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) በተወለዱበት ዘመን የመንን ሲገዛ የነበረው የአክሱም ንጉሥ እንደራሴ ነው፡፡ ታዲያ ሀጋይ በዚህ ጽሑፍ የአሁኖቹን የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ መሪዎች “የአብረሃ የልጅ ልጆች ናቸው” ይላቸውና “እነዚህ ጀግኖች የተስፋፊውን የአክራሪውን የእስልምና ጂሃዲስቶች ድባቅ መምታት ይችላሉ” የሚል እድምታ ያለው ትረካ ይተረትራል፡፡ አብረሃ የጥንቱ የአክሱም ንጉሣዊ ግዛት ተወላጅ እንደነበረ ማንም አይክድም፡፡ ይሁን እንጂ የዛሬዎቹን የኢትዮጵያ ገዥዎች የአብረሃ ዝርያዎች ማለትም ሆነ የጥንቷ አክሱም ሌጋሲ አስቀጣይ አድርጎ ማቅረብ ስህተት ነው፡፡ የጥንቷ አክሱም በማህበራዊ ስብጥሯ ህብረ-ብሄር እንጂ የአንድ ብሄር ሀገር አልነበረችም፡፡ ግዛቷ ደግሞ ከትግራይ ባሻገር ኤርትራን፣ ሰሜን ምስራቃዊ ሱዳንና አብዛኞቹን የሰሜን ኢትዮጵያ ክልሎች ይጠቅላል፡፡  አብረሃ ከነዚህ ሁሉ ግዛቶች በየትኛው እንደተወለደ በትክክል አይታወቅም፡፡ በሁለተኛ ደረጃ የዘመናችን የኢትዮጵያ መሪዎች የጥንቱ አብረሃ ሌጋሲ ወራሾች ናቸው የሚያስብል የታሪክና የአንትሮፖሎጂ ማስረጃ የለም፡፡

  

 የጽሑፉ አደገኛነት ግን ይህ አይደለም፡፡ የሃጋይ ምሁራዊ ሸፍጥ የሚያስከፋው ጥንት የተፈጸመን ታሪክ አሁን ካለው ጂኦ-ፖለቲካዊ ትርምስ ጋር እየቀላቀለ የጠብ ጫሪነት ስሜትን ለማንገሥ በመጣሩ ነው፡፡ የታሪክ ምሁር ዋነኛ ግብ የሰው ልጆች ትናንት የፈጸሟቸው ስህተቶችን እንዳይደግሙ ማስተማር እና ድሮ የነበራቸውን በጎ የአዕምሮና የማቴሪያል እሴቶችን ጠብቀው ወደ ቀጣዩ ትውልድ እንዲያስተላልፉ ማስቻል ነው፡፡ ሀጋይ ግን ታሪክን ሸርና ብጥብጥን ለማውረስ ሲል ብቻ የሚጠቀምበት ነው የሚመስለው፡፡

—-

ከላይ የጠቀስኳቸው ሁለት ምሁራን (ሞርዴኻይ አቢር እና ሀጋይ ኤርሊክ) ይሁዲዎች ናቸው፡፡ ነገር ግን ሁለቱም የተለያየ ምሁራዊ ልቀትና ርትእ ያላቸው ሆነው ተገኝተዋል፡፡ ምሁራን “የአቢርን መጽሐፍ ማንበብ አለብህ” እያሉ ሲናገሩ የነበሩት “በአቢር መጽሐፍ ውስጥ እውቀት አለልህ” ማለታቸው እንደሆነ ገብቶኛል፡፡  ሀጋይ ኤርሊክ ግን በታሪክ ስም ጽዮናዊ ፖለቲካውን የሚያሰራጭ ሸፍጠኛ ነው እንጂ የምሁር “ኳሊቲ” የለውም፡፡

አንድ ነገር ግን አለ፡፡ ይሁዲ በሙሉ መጥፎ ነው የሚሉ ሰዎች አሉ፡፡ ስህተት ነው፡፡ በጣም ስህተት!! ይህ የአዶልፍ ሒትለርና የመሰሎቹ አስተሳሰብ ነው እንጂ የጤናማ ሰው አስተሳሰብ አይደለም፡፡ አይሁድ በሙሉ መጥፎ እንዳልሆነ ለመረዳት የሚሻ ሰው የፕሮፌሰር አቢርን መጽሐፍ ብቻ ማንበብ ይበቃዋል፡፡ የህዝብን አንድነት የሚያናጉትን እንደ ሀጋይ ኤርሊክ ዓይነቶቹን መሰሪ ጸሐፊዎች ግን ጠንቀቅ በሏቸው፡፡ 

—–

First written on August 13/2015
Re-written on January 19/2016

ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም

Bewketu Seyoum and Yared Tibebu በእውቀቱ ሥዩም እና ያሬድ ጥበቡ

ከሁለት ቀኖች በፊት ስለበእውቀቱ ሥዩም አድናቆታቸውን በፌስቡክ ላይ የገለጹ ሁለት ሰዎች ነበሩ፤ ለበእውቀቱ ያላቸውን አድናቆት እኔም እጋራቸዋለሁ፤ ነገር ግን የእነዚህ ሰዎች አድናቆት በእውቀቱ ራሱንና ማንነቱን እንዲከዳ ይቃጣቸዋል። አንዱን አውቀዋለሁ፤ ከፖሊቲካና ከትጥቅ ትግል ወደስደት ”ነጻነት” የተሸጋገረ ያሬድ ጥበቡ የሚል የሚያኮራ ስም ይዞ የስደት መምህር የሆነ ነው፤ ሁለተኛው ሚስተር ቴዲ ገብርኤል ይባላል። እነዚህ ሁለት ስደተኞች በእውቀቱ ሥዩምን በጣም ስለሚወድዱትና ስለሚያከብሩት በአሜሪካ ስደተኛ ሆኖ እንዲቀርላቸው ይፈልጋሉ፤ በዚህ ብቻ ለኢትዮጵያ ያላቸውን ስሜት መገመት በጣም የሚያሳዝን ነው፤ ወደዝርዝር አልገባም።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ግርማ ሠይፉ ማሩ

“የኢትዮጵያ የታሪክ ፈተናዎች እና የሚጋጩ ሕልሞች” ዶ/ር መረራ ጉዲና Dr. Merera Gudinas new bookዶ/ር መረራ ጉዲና “የኢትዮጵያ የታሪክ ፈተናዎች እና የሚጋጩ ሕልሞች” በሚል አዲስ መጽሐፍ አስነብቦናል። በአንድ ጋዜጣ ላይ የዶክተር መረራ ከዩኒቨርሲቲ መሰናበት ያመጣው አንድ በጎ ጎን መሆኑን አንብቤያሁ። እኔም በዚህ እስማማለሁ። ብዙ የሀገራችን ፖለቲካኞች ጋዜጠኛ መቅረፀ ድምፅ ይዞ በሚጠይቃቸው ጥያቄ መልስ ከመስጠት የዘለለ ብዕርና ወረቀት አገናኝተው የሚያምኑበትን የፖለቲካ መስመር እና በግላቸው ያላቸውን ምልከታ ማካፈል ይቸግራቸዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ተስፋዬ ገብረአብ

የህወሓትን የጓዳ ወግ ማወቅ አስቸጋሪ የነበረበት ዘመን እንደዋዛ አልፎአል። ዛሬ ቀዳዳቸው በዝቶ፤ ቴክኖሎጂውም አግዞ የፈፀሙት ብቻ ሳይሆን ያሰቡትም በቀላሉ ይገኛል። ዘመኑ የመረጃ ዘመን ነው። መረጃ ከሌለ ምንም ነገር የለም። ለችግሮች መፍትሄም አይገኝም። ወያኔ ዛሬ በአስር ሺዎች ኦሮሞዎችን በገፍ የሚያስረው ስለ ቄሮ በቂ መረጃ ስለሌለው መሆኑ ይታወቃል። ተቃዋሚ የፖለቲካ ተንታኞች ወይም የማህበራዊ ድረገፅ ፀሐፊዎች አንዳንድ ጊዜ አስቂኝ ስህተት ይሰራሉ። ማለትም ሳያውቁ ለወያኔ የሚጠቅም መረጃና ምክር ይፅፋሉ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

By Eyob Dadi የቀድሞው የኤሲሚላን እና የጁቬንቱስ አማካይ የነበረው አንድሪያ ፒርሎ በእግርኳስ ቆይታው ያየው ምርጡ ወጣት ተጨዋች ተናግሯል። ፒርሎ የቡድን አጋሩ የነበረው ፓል ፓግባን ምርጡ ወጣት ተጨዋች ሲል ያወድሰዋል። ፓግባ 2012 ላይ በማንቸስተር ዩናይትድ በቂ የመሰለፍ እድል በማጣቱ ወደ ጣሊያኑ … Continue reading

በኦሮሚያ  ባሌ ክፍለሃገር ውስጥ  ጣዕመ ወልደየስ እና ቤተሰቦቹ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ንብረት የሆነው የእርሻ ማሳ በእሳት ቃጠሎ ወድሟል ። ለጥምቀት በኣል የወጡ የኦሮሞ ወጣቶች ለተቃውሞ የሚያነሳሱ ዜማዎችን ኣዜማቹሃል በሚል በመቶዎች የሚቆጠሩ ከኣዲስ ኣበባ ከተለያዩ ኣከባቢዎች ታፈሰው መታሰራቸው ታውቋል።ከዚሁ ጋር በተያያዘ …

በባሌ ክፍለሃገር የሕወሓት ባለሃብቶች ንብረት ወደመ።ለጥምቀት በኣል የወጡ የኦሮሞ ወጣቶች ከኣዲስ ኣበባ ታፈሰው ታሰሩ:: Read more »

ጥር 11፣2008 ዓ. ም ትናንትና ምሽት በጣሊያን ዋንጫ ኢንተርሚላን ናፓሊን ባሸነፈበት ጨዋታ ላይ ሁለቱ አሰልጣኞች ሮቤርቶ ማንቺኒ እና ማውሪዚዮ ሳሪ ሲጨቃጨቁ ታይተዋል። ከጨዋታው በኋላ ሪቤርቶ ማንቺኒ ከ ራይ ቲቪ ጋር ከማውሪዚዮ ሳሪ ጋር በአሰልጣኞች መቆሚያ(touchline) ላይ ስለተለዋወጡት ቃላት ስሜታዊ ሆነው ተናግረዋል። በአሰልጣኞች መቆሚያ ላይ ስለተነጋገራችሁት?ይህን ጥያቄ እሱን(ማውሪዝዮ ሳሪ) መጠየቅ አለባችሁ፣እሱ ዘረኛ ነው ብለው ይጀምራሉ ሮቤርቶ … Continue reading ““ማውሪዚዮ ሳሪ ዘረኛ ነው፣አንተ ጅል ነጭናጫ ብሎ ሰድቦኛል” – ሮቤርቶ ማንቺኒ”

በኢትዮጵያ ምድር የደም ጎርፍ ተራራዉን ተሻግሮ ፈሰሰ። ከጋምቤላ እስከ ኤርትራ በጥይት ከመቁሰል እስከ አድካሚ የበረሃ ጉዞ አስደናቂ የወጣቱ ተጋድሎ። ይህ ሁሉ የሆነዉ ፓለቲከኛ ጋዜጠኛ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ስለሆነ አይደለም። የሰራዉ ወንጀል የለም። የሆነዉ ሁሉ የሆነዉ አማራ ስለሆነ ብቻ ነዉ። 2006 …

ከጋምቤላ እስከ ኤርትራ በጥይት ከመቁሰል እስከ አድካሚ የበረሃ ጉዞ አስደናቂ የወጣቱ ተጋድሎ። Read more »

የብሔራዊ ቡድኑ የፊት መስመር ተሰላፊ ነው ፡፡ የአይረሴው የደቡብ አፍሪካው የአፍሪካ ዋንጫ ቡድን አባል፡፡ በ2014 አለም ዋንጫ ማጣሪያ ላይ ለብሄራዊ ቡድኑ ቁልፍ ነበር በስሙ ሶስት ጎሎች አስቆጥሮ ዋልያውን የአፍሪካ ምርጥ አስር ውስጥ ሲካተት ትልቅ የሆነ ድርሻን ተወጥቷል ፡፡ የዋልያው ድንቅ የፊት መስመር ተጫዋች ጌታነህ ከበደ ከኢትዮ አዲስ ስፖርት አዘጋጅ ህሊና አዳነ ጋር በፕሮፌሽናልነተ እግር ኳስ … Continue reading “” እስካሁን ካሰለጠኑኝ አሰልጣኞች ሁሉ ሰውነት ቢሻው የኔ ምርጥ አሰልጣኝ ነው” ጌታነህ ከበደ”

 የተባበሩት መንግስታት ሶሪያና ኢትዮጵያን በአንድ ምድብ አስቀምጧል : በሁለቱ አገራት ያለው ሁኔታ ለህፃናት አስፈሪ ሆኗል :: የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በኢትዮጵያ የቅርብ ዓመታት ታሪክ ውስጥ እጅግ ከፍተኛው በመሆን የተመዘገበው ድርቅ 400.000 ህፃናትን ለአልሚ ምግብ እጦትና 10 ሚልዩን የሚደርሱ ሰዎችን ለምግብ እርዳታ …

የተባበሩት መንግስታት ሶሪያና ኢትዮጵያን በአንድ ምድብ አስቀምጧል : በሁለቱ አገራት ያለው ሁኔታ ለህፃናት አስፈሪ ሆኗል :: Read more »

የአክራሪዎች መፅሃፍ ተቃጠለ በሚል የተቃጠለ ቁርአንን ያሳየው መንግስት በነኤልያስ ከድር ላይ በመፍረድ በሙስሊሞች ላይ ዘመቻውን አጠናክሯል  ሙስሊሙ አንድነቱን አጠናክሮ ብሄራዊ ጭቆናውን መታገል አለበት ተብሏል። በፍትህ እጦት ፍርድ ቤት ከ 40 ግዜ በላይ የተመላለሱት ጀግኖቹ በኤልያስ ከድር መዝገብ የተከሰሱት ወጣቶች የደህንነቱ …

የአክራሪዎች መፅሃፍ ተቃጠለ በሚል የተቃጠለ ቁርአንን ያሳየው መንግስት በነኤልያስ ከድር ላይ በመፍረድ በሙስሊሞች ላይ ዘመቻውን አጠናክሯል Read more »

#‎Ethiopia‬ ‪#‎Oromoprotests‬ : በኦሮሚያ ክልል ተቃውሞ የቀጠለ ሲሆን ለተወሰደው የግድያና እስር እርምጃ ሕወሓት ኦህዴድን ኦሕዴድ ሕወሓትን እየተወነጃጀሉ ይገኛሉ። በኦሮሚያ ክልል ሃረርጌ መኤሶ`ን ውስጥ በዛሬው አለት የህዝብ ተቃውሞ ቀጥሎ የዋለ ሲሆን የሕወሓት ሃይሎች በወሰዱት አርምጃ ኣራት ሕጻናት በጥይት ቆስለዋል። በሃረርጌ የሃሮማያ …

በኦሮሚያ ክልል ተቃውሞ የቀጠለ ሲሆን ለተወሰደው የግድያና እስር እርምጃ ሕወሓት ኦህዴድን ኦሕዴድ ሕወሓትን እየተወነጃጀሉ ይገኛሉ። Read more »

የሰማያዊ ሥራ አስፈጻሚ በአራት አባላቱ ላይ የተላለፈው የመባረር ውሳኔ ተቀባይነት እንደሌለው አስታወቀ ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎Blueparty‬ @semayawiParty ‪#‎NegereEthiopia‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬ ‹‹ውሳኔው ከፓርቲው መሰረታዊ ሀሳቦችና እምነቶች ተቃርኖ የተላለፈ ስለሆነ ተቀባይነት የለውም›› ኢ/ር ይልቃል ጌትነት (በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር) – የሰማያዊ ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ በአራት አባላቱ …

የሰማያዊ ሥራ አስፈጻሚ በአራት አባላቱ ላይ የተላለፈው የመባረር ውሳኔ ተቀባይነት እንደሌለው አስታወቀ Read more »

–    17 ክሶች ውድቅ በመደረጋቸው ከ86 ሚሊዮን ብር በላይ ዕዳም ይሰረዛል በሪል ስቴት ልማት ፈር ቀዳጅ የሆነው አያት አክሲዮን ማኅበርና የአክሲዮኑ ከፍተኛ ባለድርሻ የሆኑት አቶ አያሌው ተሰማ፣ ተመሥርቶባቸው ከነበረው አራጣ የማበደር ወንጀል ክስ ጥር 6 ቀን 2008 ዓ.ም. በነፃ ተሰናበቱ፡፡ …

በስተርጅና በሕወሓት ነጋዴ ባለስልጣናት ደባ ሲንከራተቱ የነበሩት አቶ አያሌው ተሰማ (አያት አክሲዮን ማኅበር) በነፃ ተሰናበቱ፡፡ Read more »

Tesfahun Alemneh : ትናትም የተገደሉት አማሯች ዛሬ የተገደሉት አማሮች። ወያኔ የጀመረዉን የዘር ፍጅት አጠናክሮ ቀጥሏል። ዛሬም በጎንደር ተጨማሪ ስምንት አማሮች ተገደሉ። ኮሮጆ ሃሙስ አካባቢ የቅማንት ማህበረሰብ የሆኑ አማራዎችን አማራ የገደላቸዉ ለማስመሰል የወያኔ ፌደራል ፓሊስ በአሰቃቂ ሁኔታ ገድሏቸዋል። ከተወሰኑ ቀናት በፊት …

በጎንደር ዘግናኝ ግድያ ተፈፀመ። Read more »

@Zone9ners በዴሞክራሲ ጉዳዮች ላይ ተከታታይ ጽሑፎችን ሊያስነብባችሁ ተዘጋጅቷል። እነሆ የመጀመሪያው፣ “ዴሞክራሲ እና የዘውግ ብሔርተኝነት” በናትናኤል ፈለቀ ተጽፎ ቀርቧል። ናትናኤል በዚህ ጽሑፉ ‘ዴሞክራሲ አልፎ–አልፎ የሚከሰቱ የጎሳ ወይም ዘውግ ግጭቶችን ይፈታል’ ብሎ ይከራከራል። መልካም ንባብ! በኢትዮጵያ አቆጣጠር ከ1983 ዓ.ም በኋላ የሀገሪቱን ስልጣን …

ዴሞክራሲና የዘውግ ብሔርተኝነት – (በናትናኤል ፈለቀ – Zone 9 ) Read more »

News Ethiopia Wetatoch Dimts Jan 18.2016 የኢትዮጵያ ወጣቶች ድምጽ በዛሪው የዜና መዋዕል የተመረጡ ወቅታዊ ዜናዎችን፣የተመረጡ ጣዕመ ዜማዎችንና ወቅታዊ ቃለመጠይቆችን ለእናንተ አድማጮ ቹ ይዞላችሁ ቀርቧል ከዚህም ጋር በምስራቅ ኢትዮጵያ ጀጀጋ የ13ኛው ክፍለጦር ወታደራዊ ክንፍ ጥያቄንና ቁጥራቸው 160 የሚሆኑ መኮንኖች መታሰራቸውን ያብራራል …

የኢትዮጵያ ወጣቶች ድምጽ : በምስራቅ ኢትዮጵያ ጀጀጋ የ13ኛው ክፍለጦር ወታደራዊ ክንፍ ጥያቄንና ቁጥራቸው 160 የሚሆኑ መኮንኖች መታሰራቸውን ያብራራል ያድምጡን። Read more »

Ambo University Awaro Campus dormitory on fire – Jawar Mohammed OMN በኦሮሚያ የተለያዩ ከተሞች የቀጠለው ሕዝባዊ ቁጣ እየተባባሰ በመጣበት ባሁኑ ወቅት በዛሬው ዕለት በአምቦ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች መኝታ ቤት እየተቃጠለ መሆኑ ተሰማ::ከስፍራው የሚወጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት የእሳት አደጋው አንዱን የተማሪዎች ህንፃ እያወደመው …

በኣምቦ ዩንቨርስቲ ኣዋሮ ካምፓስ የወንዶች የመኝታ ክፍል ተቃጠለ Read more »

ሰማያዊ ፓርቲ ራሱን ሊመረምር ይገባዋል ፤ ራስን መፈተሽ ለነገ ስኬት ይረዳል። ‪#‎Ethiopia‬ @semayawiparty ‪#‎MinilikSalsawi‬ ‪#‎Blueparty‬ ‪#‎EthiopiaOppositionparties‬ Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – የኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባናል ስለነጻነት እና መብት እንታገላለን በማለት የተቋቋሙ የፖለቲካ ድርጅቶች ራሳችሁን መርምሩ ….. ራሳችሁን ኣጥሩ …..ወዘተ ሲባሉ ተከባበሩ …

ሰማያዊ ፓርቲ ራሱን ሊመረምር ይገባዋል ፤ ራስን መፈተሽ ለነገ ስኬት ይረዳል። (ምንሊክ ሳልሳዊ) Read more »

ሰማያዊ ፓርቲ ኣባሎቹን ጥላቻን የሚሰብኩ በማለት በመወንጀል ለሕወሓት አገዛዝ ኣሳልፎ ሰጠ። በመጀመሪያ ለማለት የምንፈልገው ሪፖርተር ጋዜጣ የሃሰት መረጃ ካስተላለፈ ሰማያዊ ፓርቲ በሕግ ሊጠይቀው ይገባል፥ በመቀጠል በዘገባው መሰረት የሪፖርተር ጋዜጣ ኣማርኛ አትም ባወጣው ዜና የሰማያዊ ፓርቲ ኣራት ኣባላቱን በመወንጀል ሕወሓት ባቀረበባቸው …

ሰማያዊ ፓርቲ ኣባሎቹን ጥላቻን የሚሰብኩ በማለት በመወንጀል ለሕወሓት አገዛዝ ኣሳልፎ ሰጠ። Read more »

የሪፖርተር ጋዜጣ ዜና እና የዞን ዘጠኙ ጦማሪ በፍቃዱ ዘሃይሉ ስለ ሰማያዊ ፓርቲ እና ስለተባረሩት ኣባሎቹ ………….. ሪፖርተር ጋዜጣ :- ሰማያዊ ፓርቲ ቀደም ብለው በገዛ ፈቃዳቸው ራሳቸውን ከፓርቲው ማግለላቸውን በፌስቡክ ገጻቸው ያስታወቁትን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊውን አቶ ዮናታን ተስፋዬን ጨምሮ፣ አራት አባሎቹን …

የሪፖርተር ጋዜጣ ዜና እና የዞን ዘጠኙ ጦማሪ በፍቃዱ ዘሃይሉ ስለ ሰማያዊ ፓርቲ እና ስለተባረሩት ኣባሎቹ Read more »

አርቲስት ሀዊ ተዘራ በኦሮሚያ ክልል በተነስዋ ተቃውሞ ምክንያት ተይዛ ከታሰረች በኋላ በደረሰባት ከፍተኛ ድብደባ የሆስፒታል አልጋ ቁራኛም ሆና ከህዝብ ጎን እንደሆነች ከተኛችበት አልጋም ላይ ሆና ተቃውሞዋን ማሰማቷን ቀጥላለች።

ጥር 8፣ 2008 ዓ. ም ኤቨርተኖች ከቸልሲ ጋር ያደረጉት የዛሬው የፕሪምየር ሊግ ጨዋታ 3ለ3 በሆነ ውጤት ተጠናቋል። በጨዋታው በመጨረሻዎቹ ጭማሪ ሰዓት ላይ ሁለት ጎሎች የተቆጠሩ ሲሆን፣ የጆን ቴሪ የመጨረሻ ደቂቃ ጎል አጨቃጫቂ ነበረች። ሮቤርቶ ማርቲኔዝ ቴሪ ያስቆጠረው ጎል ከተጨመረው ሰዓት ማለፉ ብቻ ሳይሆን ከጨዋታ ውጭ የነበረ በመሆኑ የዕለቱ ውሳኔን “ሰይጣናዊ” ሲሉ ይገልጹታል። “ለደጋፊዎች ጥሩ ጨዋታ … Continue reading ““የዳኛው ውሳኔ ሰይጣናዊ ነበር”- ሮቤርቶ ማርቲኔዝ”

“ማስተር ፕላኑን ህዝቡ እንደማይቀበለው ተረጋግጧል” – ኦህዴድ – “ማስተር ፕላኑ መሰረዝ ያለበት በፓርቲ ውሳኔ አይደለም” – ተቃዋሚዎች Addis Admass :- ማስተር ፕላኑ ተግባራዊ እንዳይሆን የተሰረዘው ህዝቡ እንደማይቀበለው በውይይት በመረጋገጡ መሆኑን የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ ፅ/ቤት የገለፀ ሲሆን ተቃዋሚዎች በበኩላቸው፤ ማስተር ፕላኑ …

“ማስተር ፕላኑን ህዝቡ እንደማይቀበለው ተረጋግጧል” – ኦህዴድ – “ማስተር ፕላኑ መሰረዝ ያለበት በፓርቲ ውሳኔ አይደለም” – ተቃዋሚዎች Read more »

Addis Admass :- • ከዩኒቨርስቲው ጋር የተፈራረሙት የደብረ ሊባኖስ ገዳም አስተዳዳሪ ከሥራቸው ታግደው ነበር • ሐዋርድ ያዘጋጀው ውል የባለቤትነት መብትን ይነፍጋል • ቤተ ክርስቲያኒቱ የምትቀበለው ውል እንዲዘጋጅ ትዕዛዝ ተሰጥቷል “እውነት እና አገልግሎት” ተቋማዊ ብሂሉና መፈክሩ ነው፡፡ በተለይ፣ ለጥቁሮች በሚሰጠው የከፍተኛ …

ከሐዋርድ ዩኒቨርሲቲ የተመለሰው የብራና መጽሐፍ እያወዛገበ ነው Read more »

የተባበሩት መንግሥታት የምግብና የእርሻ ድርጅት በእንግሊዘኛ ምህፃር «FAO» ፣ኢትዮጵያ የገጠማትን አስከፊ ድርቅ መቋቋም የሚያስችላት የ50 ሚሊዮን ዶላር አስቸኳይ የምግብ እርዳታ መጠየቁን ሮይተርስ ዘገበ። በሀገሪቱ በዝናብ እጥረትና ከመጠን በላይ በጣለ ዝናብ ምክንያት በአንዳንድ አካባቢዎች እስከ 90 በመቶ ያህል ሰብል አልያዘም ። …

በያዝነው 2016 በኢትዮጵያ ምግብ ማገኘት አስቸጋሪ እንደሚሆን በኢትዮጵያ የFAO ተጠሪ አማዱ አላሁሪ ገልፀዋል። Read more »

ቢቢኤን የአላህ ውሳኔ ሁኖ ወደ አኪራ የሄደው ሙባረክ ይመር ህክምና እንዳያገኝ ተደርጎ እንደነበር አብረውት የታሰሩት በሀዘን ገለጹ ሙባረክ ቁሞ መራመድ እንደማይችል እንደደከመ እየተነገራቸው ከፈለገ ተንበርክኮ ይሂድ በማለት የማረሚያ ቤት ፖሊሶች መሳለቃቸውም ታውቋል ከ2005 ጀምሮ በአህመድ ኢንዲሪስ የክስ መዝገብ የተከሰሰው እና …

በሼኽ ኑሩ ግድያ በሃሰት ተወንጅሎ በማዕከላዊ ከፍተኛ ድብደባ እና ስቃይ የደረሰበት ሙባረክ ይመር ቂሊንጦ ውስጥ ሞተ Read more »

በኦሮሚያ ክልል ተቃውሞው አንደቀጠለ ነው። ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎Oromoprotests‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬ Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) ዛሬም በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ወረዳዎች ተማሪዎች አና ነዋሪው በኦሮሞ ሕዝብ ላይ የሚደረገውን ግድያ አና እስር በመቃወም ድምጻቸውን ሲያሰሙ ውለዋል። በዚህም መሰረት በሸዋ ጅባት አውራጃ ሻናን ከተማ በሃረርጌ በደኖ …

በኦሮሚያ ክልል ተቃውሞው አንደቀጠለ ነው። Read more »

ለመጀመሪያ ጊዜ የኢትዮጵያ ፊደል በላፕቶፕና በዲስክቶፕ ተቀርጾ አገልግሎት መስጠት ቻለ

The first Amharic, Geez laptop

Ethiopia Zare (ዓርብ ጥር 6 ቀን 2008 ዓ.ም. January 15, 2016)፡- ጋዜጠኛና ፀሐፊ ገነት አየለ የኢትዮጵያ ፊደላት እንደሌሎቹ የቋንቋ ፊደላት በላፕቶፕና በዴስክቶፕ ለመጀመሪያ ጊዜ ተቀርጸው ለተጠቃሚዎች አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረግ መቻላቸውን ከደረሰን መረጃ ለማወቅ ችለናል። ይኸው የመጀመሪያው በኢትዮጵያ ፊደል የሚጽፍ ኮምፒዩተር በገበያ ላይ መዋሉ ታውቋል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

የሃሰት ዶክመንተሪ ፊልም እየሰሩ ሕዝብን መወንጀል ኣጥብቀን አናወግዛለን። ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎Ethiomuslims‬ ‪#‎EBC‬ ‪#‎EPRDF‬ ‪#‎Justice‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬ Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – ልማት እና ኣሸባሪ እያሉ ማጭበርበር እንደተነቃበት እና በዚህ ዘመን እንደማይሰራ ወያኔ ሊያውቀው ይገባል፤ ህዝብ ነቅቷል። መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ፍትሕ እንጂ የሃሰት …

የሃሰት ዶክመንተሪ ፊልም እየሰሩ ሕዝብን መወንጀል ኣጥብቀን አናወግዛለን። Read more »

በኦሮሚያ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ሐላፊ እንደሚሉት ዕቅዱን ሕዝቡ፤ በእሳቸዉ አገላለጥ «ከጫፍ እስከ ጫፍ» ተቃዉሞታል።በማስተር ፕላኑ ሰበብ በተነሳው ተቃውሞ በሁለት ወራት ጊዜ ዉስጥ ወደ 140 ሰዎች እንደተገደሉ ና በርካቶች እንደቆሰሉ የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ በምህፃሩ ኦፌኮ አስታውቋል

#‎Ethiopia‬ ‪#‎Oromoprotests‬ : ዛሬም በኦሮሚያ ክልል ተቃውሞው እንደቀጠለ ውሏል።የኦሮሚያ ትምሕርት ቤቶች ከተወሰኑት ውጪ የመማር ማስተማር ሂደቶች ቆመዋል። Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) በትላንትናው እለት በተቃውሞ እና በቶክስ ስትናጥ የዋለቸው ኣምቦ ኣራት ነዋሪዎቿን በሞት ያጣች ሲሆን በኣምቦ ዩንቨርስቱ ኣውሮ ካምፓስ አንዲሁም በመናኻሪያ …

ዛሬም በኦሮሚያ ክልል ተቃውሞው እንደቀጠለ ውሏል።የኦሮሚያ ትምሕርት ቤቶች ከተወሰኑት ውጪ የመማር ማስተማር ሂደቶች ቆመዋል። Read more »

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ረቡዕ፡- ዴሞክራሲ በተግባር፣ ሴቶችና ቤተሰብ፣ አሜሪካና ሕዝቧ፣ ኢትዮጵያዊያን ባሜሪካ

  ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው እንደሚታወቀው በተማሪዎች የተጀመረው ተቃውሞ ሌላው የኅብረተሰብ ክፍልም ተቀላቅሎት ሲደረግ የቆየው ሕዝባዊ ተቃውሞ እነሆ ሁለት ወራት እየሆነው ነው፡፡ እያየነው እንዳለነው እስከአሁን ተቃውሞው ያመጣው ውጤት ወይም ለውጥ የለም፡፡ ወደፊትም ሕዝቡ በዓመፁ የመቀጠል ብርታት የሚኖረው ከሆነ “በእኔ ግምት ይኖረዋል ብየ ስላልገመትኩ ነው ምክንያቶች አሉኝ” እንዲያው ከሆነ ግን ወያኔ ሁሉንም ለቃቅሞ እስኪፈጅ ድረስ ሳይሰለች […]

Finote Democracy Voice of Ethiopian Unity Satellite Radio News ጥር 3 ቀን 2008 ዓ.ም. (January 12, 2016) # በአዲስ አበባ የነዳጅ እጥረት ተከሰተ # አመጹ በተለያዩ ቦታዎች ቀጥሏል # ወያኔ ቅዋሜ በሚያሰሙ መኮንኖች ላይ ቅጣት ለማድረግ ያሰበ መሆኑ ተሰማ # …

በአዲስ አበባ የነዳጅ እጥረት ተከሰተ:: ወያኔ ቅዋሜ በሚያሰሙ መኮንኖች ላይ ቅጣት ለማድረግ ያሰበ መሆኑ ተሰማ Read more »

የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን ተከትሎ በኦሮሚያ የተነሳው ተቃውሞ እንደቀጠለ ነው ። ‪#‎RDH‬ ጥር 4/2008 በምዕራብ ሃረርጌ መሰላ ወረዳ አባድር ከተማ ከሳምንት በፊት በተደረገ የተቃውሞ ሰልፍ ከተሳተፈ በኃላ በመንግስት ሃይሎች ተይዞ ከተወሰደ በኃላ የት እንደወሰዱት ያልታወቀ የነበረው በሪ ሰኢድ አሊ የተባለ …

የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን ተከትሎ በኦሮሚያ የተነሳው ተቃውሞ እንደቀጠለ ነው ። RDH‬ Read more »

ሱዳን፣ ግብፅ እና ኢትዮጲያ ለብዙ ግዜ እየተንከባለለ ከመጣ ድርድር በኋላ በጎርጎሮሳዊው አቆጣጠር ታህሳስ 29 2015 ካርቱም ሱዳን ሊይ Declaration of Prinicples ወይም የመሰረታዊ መ መርሆዎች ሰነድ ተብሎ የምጠራዉን ሰነድ መፈራረማቸዉ ተዘግቧል ።

በኦሮሚያ ክልል ተቃውሞ የቀጠለ ሲሆን ኣምቦ ተቃውሞው ሲፈነዳ በመላው ኦሮሚያ የትምህርት ማቆም ኣድማ ተደርጓል።Qabsoon itti fufa!! ‪#‎Oromoprotests‬ ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎Miniliksalsawi‬ ‪#‎EPRDF‬ Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ኣከባቢዎች ተቃውሞው የቀጠለ ሲሆን በኣምቦ በማእከላዊ ሲሰቃይ ለሞት የተዳረገውን የኣብደታ ኦላንሳን ኣስከሬን …

Qabsoon itti fufa!! ‪በመላው ኦሮሚያ የትምህርት ማቆም ኣድማ ተደርጓል። Read more »

[ክቡር ሚኒስትሩ የአለቃቸው ልጅ ልታገባ መሆኑን ሰምተው፣ በራሳቸው ተነሳሽነት ሠርጉን የሚያስፈጽም ኮሚቴ ሊያዋቅሩ ተዘጋጅተዋል፡፡ አማካሪያቸውም በአፋጣኝ ወደ ቢሯቸው እንዲመጣ አደረጉት] –    ምነው በአፋጣኝ ፈለጉኝ ክቡር ሚኒስትር? –    አንገብጋቢ ጉዳይ መጥቶ ነው፡፡ –    የምን አንገብጋቢ ጉዳይ? –    ትልቅ አዲስ አገራዊ ፕሮጀክት …

ክቡር ሚኒስትሩ የአለቃቸው ልጅ ልታገባ መሆኑን ሰምተው፣ በራሳቸው ተነሳሽነት ሠርጉን የሚያስፈጽም ኮሚቴ ሊያዋቅሩ ተዘጋጅተዋል፡፡ Read more »

ሕወሓትን ማመን ቀብሮ ነው። ….. የገበሬው የመኖር ሕልውና ሊረጋገጥ ይገባል። ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎Oromoprotests‬ ‪#‎AddisAbabaMasterPlan‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬ ‪#‎EPRDF‬ ‪#‎OPDO‬ Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – እኛ ነገር የሚገባን መች ነው? የኦሮሞ ሕዝብ በፈጠረው ጫና ኣጣብቂኝ ውስጥ የገባው የሕወሓት ኣገዛዝ የማስተር ፕላኑን አቅድ ሰረዝኩት ኣለ። …

ሕወሓትን ማመን ቀብሮ ነው። ….. የገበሬው የመኖር ሕልውና ሊረጋገጥ ይገባል። ‪(ምንሊክ ሳልሳዊ) Read more »

አንዳንድ ፣ አሸባሪ ፣ ልማት እና ወዘተ፣ የቃላት ትርጉም ( ሄኖክ የሺጥላ ) አንድ ወዳጄ <አንዳንድ> የሚለው ቃል ትርጉም ምን ማለት እንደሆነ ልታስረዳኝ ትችላለህ ወይ ብሎ የቃላት እውቀቴን ተፈታተነው ። በመጀመሪያ በፈረንጅኛው a small amount or number of people or …

አንዳንድ ፣ አሸባሪ ፣ ልማት እና ወዘተ፣ የቃላት ትርጉም ( ሄኖክ የሺጥላ ) Read more »

ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር ተያይዞ በኦሮሚያ ክልል ከስምንት ሳምንታት በፊት የጀመረው የተቃውሞ እንቅስቃሴ በተለያዩ ከተሞች እንደቀጠለ መሆኑን ምንጮች ተናግረዋል።