“የዳኛው ውሳኔ ሰይጣናዊ ነበር”- ሮቤርቶ ማርቲኔዝ (ኢትዮአዲስ ስፖርት)

image

image
By Eyob Dadi

ጥር 8፣ 2008 ዓ. ም

ኤቨርተኖች ከቸልሲ ጋር ያደረጉት የዛሬው የፕሪምየር ሊግ ጨዋታ 3ለ3 በሆነ ውጤት ተጠናቋል።

በጨዋታው በመጨረሻዎቹ ጭማሪ ሰዓት ላይ ሁለት ጎሎች የተቆጠሩ ሲሆን፣ የጆን ቴሪ የመጨረሻ ደቂቃ ጎል አጨቃጫቂ ነበረች።

ሮቤርቶ ማርቲኔዝ ቴሪ ያስቆጠረው ጎል ከተጨመረው ሰዓት ማለፉ ብቻ ሳይሆን ከጨዋታ ውጭ የነበረ በመሆኑ የዕለቱ ውሳኔን “ሰይጣናዊ” ሲሉ ይገልጹታል።

“ለደጋፊዎች ጥሩ ጨዋታ ነበር ነገርግን የዳኝነቱ ደረጃ ሰይጣናዊ ነበር። በእውነት ልብ የሚነካ ነበር። ማንም እንደዛ አይነት ውሳኔ አይገባውም። ውሳኔው ጥሩ አልነበረም። የትኛውም የቸልሲ ተጨዎች ግቡ ከጨዋታ ውጭ እንደነበር መናገር ይችላል። የተጨመረው ሰዓትም ማለፉንም እንደዚሁ ም። ስህተቱ ጥቁር እና ነጭ ነበር።” ሲሉ ተናግረዋል።