“ማውሪዚዮ ሳሪ ዘረኛ ነው፣አንተ ጅል ነጭናጫ ብሎ ሰድቦኛል” – ሮቤርቶ ማንቺኒ

ጥር 11፣2008 ዓ. ም
ትናንትና ምሽት በጣሊያን ዋንጫ ኢንተርሚላን ናፓሊን ባሸነፈበት ጨዋታ ላይ ሁለቱ አሰልጣኞች
ሮቤርቶ ማንቺኒ እና ማውሪዚዮ ሳሪ ሲጨቃጨቁ ታይተዋል።
ከጨዋታው በኋላ ሪቤርቶ ማንቺኒ ከ ራይ ቲቪ ጋር ከማውሪዚዮ ሳሪ ጋር በአሰልጣኞች መቆሚያ(touchline) ላይ ስለተለዋወጡት ቃላት ስሜታዊ ሆነው ተናግረዋል።
በአሰልጣኞች መቆሚያ ላይ ስለተነጋገራችሁት?ይህን ጥያቄ እሱን(ማውሪዝዮ ሳሪ) መጠየቅ አለባችሁ፣እሱ ዘረኛ ነው ብለው ይጀምራሉ ሮቤርቶ ማንቺኒ
“እንደ እሱ አይነት ሰዎች እግርኳስ ውስጥ መገኘት የለባቸውም።እሱ የዘረኝነት ቃላት ተጠቅሞ ሰድቦኛል።እኔ የቆምኩት ስለ ተጨማሪው 5 ደቂቃ ለመጠየቅ ነበር ነገርግን ማውሪዚዮ ሳሪ ወደ እኔ መጥቶ አንተ ቆሻሻ፣ጅል ነጭናጫ ብሎ ጮሆ ሰድቦኛል።እሱ እንደሚያስበው አይነት ሰው ከሆንኩኝ ኩራት ይሰማኛል።እርሱ 60 አመቱ ነው እንደ እሱ አይነት ሰዎች በእግርኳሱ መኖር የለባቸውም።እንደዛ ሲናገር አራተኛው ዳኛው ቢሰማውም ምንም ያለው ነገርግን የለም።ወደ መልበሻ ቤት ይቅርታ ሊጠይቀኝም መጥቶ ነበር
ነገርግን በራሱ በጣም ሊያፍር ይገባዋል።”
ሲሉ ነው ሮቤርቶ ማንቺኒ የተናገሩት
ምንጭ :- ዘ ጋርድያን
Filed under: የጣሊያን ሴሪ አ
![]()

