የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን ተከትሎ በኦሮሚያ የተነሳው ተቃውሞ እንደቀጠለ ነው ። RDH
የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን ተከትሎ በኦሮሚያ የተነሳው ተቃውሞ እንደቀጠለ ነው ።
#RDH ጥር 4/2008
በምዕራብ ሃረርጌ መሰላ ወረዳ አባድር ከተማ ከሳምንት በፊት በተደረገ የተቃውሞ ሰልፍ ከተሳተፈ በኃላ በመንግስት ሃይሎች ተይዞ ከተወሰደ በኃላ የት እንደወሰዱት ያልታወቀ የነበረው በሪ ሰኢድ አሊ የተባለ በዛሬው እለት ተገሎ ጫካ ውስጥ ተጥሎ መገኘቱ ታወቀ


የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን በመቃወም የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ መንግስት የወሰደውንና እየወሰደ ያለውን ህገወጥ ተግባር በመቃወም እየተደረገ ያለው ተቃውሞ በተለያዩ አካባቢዎች ቀጥሏል።

በምዕራብ ሃረርጌ ሃረማያ ዩኒቨርሲቲ እየተደረ ያለው ተቃውሞ አሁንም እንደቀጠለ ሲሆን የመንግስት ሃይሎችም በተማሪዎች ላይ የተለመደውን ህገ ወጥ እርምጃ በመውሰዳቸው ተማሪዎች ወደ አካባቢው ገበሬ ማህበረሰብ ሸሽተው በመሄድ መከለላቸው ታውቋል።
ይህ የመንግስት ሃይሎች ህገ ወጥ እርምጃ ለሶስት ተከታታይ ቀናት የተካሄደ መሆኑም ተዘግቧል ።
በምእራብ ሀረርጌ እስኳሁን 263 ተማሪዎች የታሰሩ ሲሆን ብዛት ያላቸውም ቆስለው : በሃረማያ ሆስፒታልና በሃረማያ ህይወት ፋና ሆስፒታል በህክምና ላይ እንደሚገኙ ታውቋል ።
በትላንትናው እለትም በሃረማያ አካባቢ የሚገኙ ሙዴ እና ቱጄ ገቢሳ የሚባሉ ገበሬ ማህበር ገበሬዎችም ከመንግስት ሃይሎች ጋር የተጋጩ ሲሆን የመንግስት ሃይሎች በወሰዱት እርምጃም አንድ ጫላ ሙሀመድ የሚባል ገበሬ መገደለሉንና በዛሬው እለትም የቀብር ስነስርአቱ መፈፀሙ ታውቋል ።
በአምቦ ከተማም አብደታ ኦላና የሚባል በመንግስት ሃይሎች የተገደለ ሰው : የቀብር ስነስርአቱ ሲፈፀም ረብሻ መፈጠሩ የታወቀ ሲሆን ህዝቡ የቀብር ስነስርአቱን በአግባቡ እንዳይፈፅም አስለቃሽ ጭስ የመንግስት ኀይሎች መተኮሳቸውንና በሰው ላይ ጉዳት ማድረሳቸው የታወቀ ሲሆን የተጎዱ ብዛት ያላቸው ሰዎችም አምቦ ሆስፒታል እየታከሙ መሆናቸውንና ከተጎዱት መካከልም አንዲት ህፃን ልጅ ከነ እናቷ እንደሚገኙበት ታውቋል ።
የአምቦ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችም ዶርሙ ተዘግቶባቸው መደብደባቸው ተሰምቷል ። በትላንትናው እለትም በሻሻመኔ የፕሪፓራቶሪ ተማሪዎች ተቃውሞ አካሄደዋል በዛሬው እለትም ግቢው ውስጥ ተሰባስበው ተቃውሟቸውን እያሳዩ መሆኑ ተዘግቧል ።
ባለፈው ሳምንት አዳባ ላይ ተጎድቶ ሻሸመኔ ሆስፒታል ተኝቶ የነበረው አወል በዛሬው እለት ህይወቱ ማለፋ ታውቋል ።
በትላንተ እለት ምስራቅ ወለጋ ሪሞ ወረዳ የአንደኛና የሁለተኛ ደረጃ የፕሪፖራቶሪ ተማሪዎች : የታሰሩ ተማሪዎችና ሌሎችም ይፈቱ በሚል ድምፃቸውን ማሰማታቸው ታውቋል ።
በዛሬው እለትም በሀረር ተቃሞው የቀጠለ ሲሆን በሆሮ ጉድሩ ዞን አባዪ ጮማን ወረዳ ፊንጫ ከተማ ተማሪዎች በከፍተኛ ሁኔታ ተቃውሟቸውን አካሄደዋል
በድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ተቃውሞው ተፋፍሞ የቀጠለ ሲሆን ሶስት መቶ የሚደርሱተማሪዎች ታስረው እንደሚገኙና አንድ ተማሪም ቱዊንስ ሲ የሚባል ህንፃ ውስጥ መገደሉን የፀጥተ ሃይሎች ቦታውን ከበውት ሰለሚገኙ የሟቹን ማንነት ለመለየት አለመቻሉ ታውቋል ።
የአምቦ አዋሮ ካምፓስ ተማሪዎችም ተቃውሞ እያሰሙ መሆናቸውንና ምግብም ሆነ መጠጥ እንዳይገባላቸው መከልከሉን ተዘግቧል ።
በተያያዘ ዜናም በትላንትናው የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ ባደረገው ስብስባ የአዲስ አበባ ማሰተር ፕላን እንዲቆም ወስነናል ማለታቸውን ኢቢሲ የተባለው የመንግስት የቴሌቪዥን ጣቢያ የዘገበ ሲሆን አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች የትኛውን ማስተር ፕላን ነው ኦህዴዶች እንዲቆም የወሰኑት? አቶ አባዱላ በኢቢሲ ቀርበው ከ2006 ጀምሮ ቆሟል ያሉትን ነው ወይንስ ሌላም ህዝብ ያላወቀው ማስተር ፕላን አለ ሲሉ በመገረም ጠይቀዋል ። #RDH
Lemelkam astedader bicha kehone Ketlubet
5
2
1. Begf yetaseru hulu baschequay
yalandach qdme hunieta yfetu.
Lederesebachew engltna sqaym
kasa ykefelachew.
2. Begf letegedelut
bietesebachewn lidegf miyaschl
kfteña kasa kej lay ykefelachew.
3. Begf akalachew legodele
lidegfachew yemiyaschl kefteña
kasa ykefel.
4. Yetedebedebu, yeteleyaye sqay
yederesebachewm tegebiw
kasa yekefelachew.
5. Yechfchefa tzaz yastelalefu,
yechfchefa tzazun yefeTemu
baschequay beglT ye wonjeleña
chlot lefrd yqrebu.
Dlachn yqeTlal
ቀይ ሽብርን ዳግም ትውልዱን አሳዩት።
ማሥተር ፕላኑ አልተሠረዘም ይቆይ (pending) አርጉት ተባብለዋል ወሮ አሥቴር የኦህዴድ እንሥት አህያዋ እንዳፀደቀችው።
ለወገናችን መድረሥ አቅቶናል የታል ሀገር አድኑ ወያኔን ለማሥወገድ እየተከፈለ ያለው መሥዋእትነት የኦሮሞውና የጎንደር ህዝብ ብቻ ነው እንዴ ሀገር እንዳትሸጥ ከአባቶቹ አደራን የተቀበለው ወይሥ እንደ ትግራይ ወያኔ እና ሻብያ የሀገር ባንዳ ሄንን የታል…..
ኦህዴድ ሆይ ትጥቅህን ፈተህ ልጆችህን አድን አፈሙዙን አዙረው ቁላው ወያኔን።
የብሄር ፖለቲካ ጉድ አፍልቷል በአንደኛ ደረጃና ሁለተኛ ተማሪዎችን ሆን ተብሎ እርሥ በርሡ ማን የማን ጎሣ እንደሆነ እንዲተያይ ያረገ በባህል በብሄር ሥም የሥነ ትምህርት አላማው ጎሣ መር አድርጓል ።
እንዲሁም በዩኒቨርሥቲ ምደባው ብሄር ተኮር አደረጃጀትን በተከተለ ከየብሄሩ በማጣረዝ ቡድም እንዲመሠረት እና የተማሪ የብሄር ካድሬዎች እና መምህራንን በማሠማራት ትውልዱን ለ10 አመት በበለጠ ከፍተኛ ችግር ውሥጥ ገብተናል ይህም ትውልዱ እንደሀገር ሣይሆን እንደብሄር አሥቦ በክልሉ ብቻ መኖር መሥራት እንደሚችል በሚያረጋግጡ አደረጃጀት ተተብትቦ ይህን የመሠለ ሥንቃር ውሥጥ ሀገራችን ገብታለች አሁንም ቢሆን ይህ ትግል የኦሮሞው ብቻ ችግር ሣይሆን የሁሉም ክልሎች ችግር ነው። በጋራ በልማት ሥም እየተዘረፈና እየተሸጠ ያለውን መሬት ባለቤቶቹ እኛ ሥለሆን በየክልሉ ያለውን የዝርፊያ እሥትራቴጂ ልናሥቆም ሁሉም ኢትዬጵያዊ ሊረባረብ ይገባል የሀገራችንን መሬት አልሚዎቹም ባለቤቶቹም እኛው ነን ማንም ከጫካ መጥቶ እኔ ነኝ የማውቅልህ ተነሥ ልጅህን እኔ አረብ አገር ልላክልህ በሚል የባርነት ድለላ ውየላና ውየናው ገብቶህ ግንባርህን ለጥይት ደምህን ለሀገርህ እየከፈለ ያለው አርሶ አደር ያበላን እጁ በሬውን የገረፈበት እጁ ይፋረደናልና ሁላችንም የወገን እንባን እናብሥ።
ሞት ለወያኔ ወያኔም ይወገዳል!!!
This article is a pure propaganda. I am there in Ethiopia and all the story I see here is patently false. The pics are copied somewhere else in Africa. Do not pour gasoline into fire! It is totally shameful and instigating racial instability in Ethiopia. I guess no body will benefit from its aftermath.
But there is fire burning out there!
And you will soon experience first hand when the fire catches your own home.
Get ready
This is true story everybody.
weyane must be disarmed
@Bedaanee,
I think you may be correct somehow. Yesterday, I saw RT News exposing BBC and CNN regarding a small besieged town in Syria. These main stream medias copied hungry children and elderly photos from different part of the world and a year or so ahead pics which was posted on the internet to blame the siege by Syrian government army. After RT’s report, BBC as well as CNN retracted the photos while maintaining their stories. To my surprise, UN Secretary General is also parroting that same doctored story.
Therefore, whether it comes from TPLF or Oppositions, it is quite normal to misrepresent the information so as to gain political scores. We as a people has a responsibility to double check and confirm through various sources whether that particular information is correct.