በጅማና ሃሮማያ ዩኒቨርሲቲዎች ትላንት ምሽትና ዛሬ ማለዳ ላይ የተከሰቱ የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች – VOA

Protests at Haramayaa and Jimma Universities - 12 January 2016
በሃሮማያ ዩኒቨርስቲ ከትናንት በስትያ የተጀመረው ተቃውሞ ዛሬም ቀጥሎ የመንግሥት ሓይሎች ርምጃ እየወሰዱ መሆኑንና ተማሪዎች ወደ አካባባቢው ማኅበረሰብ እየሸሹ መሆኑን የኦሮሚኛ ክፍል ባልደረቦቻችን ያነጋገሯቻቸው ነዋሪዎች አመልክተዋል።

ፌዴራል ፖሊስ “ልጆቹን ለምን ትሸሽጋላችሁ” በማለት አርሶ አደሮች ላይ ተኩስ መክፈቱንና የተጎዱ ሰዎች መኖራቸውን ምንጮቹ ገልጠዋል። ለደህንኔቱ ሲል ስሙ እንዳይገለጽበት የጠየቀ የዓይን ምስክር ስለ ሃሮማያ ዩኒቨርሲቲው ሁናቴ ለባልደረባችን ነሞ ዳንዲ እንዲህ ሲል ገልጿል።

“ተማሪዎቹ በዩኒቨርስቲው አካባቢ ወዳሉት ቀበሌዎች ሸሽተው ያገኙት ሰው ጋር ተሸሸጉ” ፌደራል ፖሊስ ደግሞ የደበቃችሁትን ተማሪ አውጡ በማለት አርሶ አደሩን መደብደብ ያዘ። “ተማሪው ለነፍሱ ብሎ እኛ ጋር መጥቶ ተደበቀ። አንተ ጋር መጥቶ የተደበቀን ሰው እንዴት አሳልፈህ ትሰጣለህ እኛም ኦሮሞዎች እነሱም ኦሮሞዎች ብሎ እምቢ አለ አርሶ አደሩ።”

የዓይን ምስክሩ ሲቀጥል፡-“መከላከያም ተኩስ ከፈተ፣ ብዙዎች በጥይት ተመትተዋል። ሁለት አርሶ አደሮች ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል። አሁንም ተኩስ ይሰማል። አርሶ አደሩም ሜንጫውን ይዞ ከያለበት ለመረዳዳትና ለመመከት እየሞከረ ነው። መከላከያዎች መንገዱን በመዝጋት ላይ ስላሉ ሁኔታውን ለማወቅ ያስቸግራል የሞተም ሰው ሊኖር ይችላል” ብሉዋል።

በተመሳሳይ በሃረማያ ሁለተኛ እና መሰናዶ ትምህርት ቤት ተማሪዎችም ትናንት የተቃውሞ ሰልፍ በማድረጋቸው በዕለቱ የተያዙትን ጨምሮ ወደ 200 የሚሆኑ የዩኒቨርስቲና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች በሃሮማያ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው እየተንገላቱ ናቸው ሲል አክሎ አስረድቷል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በምስራቅ ወለጋ ኪራሙ ከተማ የታሰሩ ተማሪዎች እና “አቶ በቀለ ገርባ ይፈታ” ብለው የመሰናዶ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የተቃውሞ ሰልፍ እንዳደረጉና የአካባቢውም ማህበረሰብ ከተማሪዎቹ ጋር ተቀላቅሎ ተቃውሞ ማሰማቱን አንድ ስሙን መናገር ያልፈለገ ተማሪ ለባልደረባችን ቱጁቤ ኩሳ ገልጾላታል። “የአካባቢው ኣስተዳዳሪና የከተማዋ የኦህዴድ ተመራጭ ወይዘሮ አበባ በየነ መጥተው ለማረጋጋት ሞከሩ ። ተማሪዎቹ ግን የታሰሩት እስኪፈቱ አንማርም ብለው ተቃውሞኣቸውን ቀጥለዋል ብለዋል” ካሉ በሁዋላ፣

“በሁዋላ አጋዚ ከጊዳ አያና ከተማ መጣ ። ተማሪዎችን ለቅመው ወደእስር ቤት ወሰዱ። መምህር ገደፍ የሚባሉ አስተማሪ “ አንተ ነህ ይህን ያነሳሳኸው” ተብለው እስር ቤት ውስጥ እየተሰቃዩ ናቸው። ሴቶች ሳይቀሩ ነው እስር ቤት ተወስደው እየተደበደቡ ያሉት።” ሲሉ አመልክተዋል።

በኪራሙ ከተማ ተደረገ የተባለውን ሰልፍ በተመለከተ ለማጣራት የወረዳው አስተዳዳሪ ወደሆኑት አምሳለ ጃለታ ቢደወል ስልካቸውን አላነሱትም። በሃሮማያ ዩኒቨርስቲና አካባቢው የተደረገውን ተቃውሞ እና ተጎዱ የተባሉትን ሰዎች በሚመለከት ደግሞ ትናንት ያነጋገርናቸው የምዕራብ ሐረርጌ ፖሊስ ኮማንደር ኡስማን መሃመድ “የተባለው ሁሉ ሃሰት ነው፣ ሁሉ ሰላም ነው” የሚል ምላሽ መስጠታቸው ይታወሳል።

በኦሮምያ የተለያዩ አካባቢዎች ከተቀሰቀሰው የተቃውሞ እንቅስቃሴ ጋር ተያይዞ በጅማና የሃሮማያ ዩኒቨርሲቲዎች ትላንት ምሽትና ዛሬ ማለዳ ላይ መቀጠላቸው ሰዎች ገልጸዋል።

ድንገቶችን የተከታተሉት የኦሮምኛ ክፍል ባልደረቦቻችን ጃለኔ ገመዳና ነሞ ዳንዲ ያጠናቀሯቸው ዘገባዎች አሉ… ያዳምጡ → listen

5 Comments on “በጅማና ሃሮማያ ዩኒቨርሲቲዎች ትላንት ምሽትና ዛሬ ማለዳ ላይ የተከሰቱ የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች – VOA”

  1. በጅማ ዩኒቨርሲቲ የእጅ ቦምብ
    ተወረወረ | 33 ተማሪዎች
    ተጎድተዋል | 2 ተማሪዎች በሞት
    አፋፍ ላይ ናቸው

  2. በአንዋር መሥኪድ ወያኔ የጀመረችው ማፈንዳት ይህው አሁን በፒያሣ ባንኮ ዲ ሮማ አጥር ሥር መገኘቱ ቀጥሎም ዲላ ዩኒቨርሥቲ አራተኛ ትላንት ማምሻውን ጂማ ዩኒቨርሥቲ ላይ መፈንዳታቸው የብሄራዊው ደህንነት ክፍል እየሠራ ላለው የዘገባ ፊልም ግብአት አክሽን ፈፅመው እየተዘጋጁ ሢሆን ህዝባዊ አመፁን እየመራ ያለው የኦሮሞ ህዝብ አሸባሪ ሊባል ሊፈረጅ 11 ኛው ሠአት ላይ ነው።

    ቀይ ሽብር አይፋፋምብን!
    የታሠሩት እሥረኞች ይፈቱ!
    በልማት ሥም የመሬት ዝርፊያ ሽያጭ ለ99 አመት ይቁም!
    መሬት ላራሹ!
    የዘር ፖለቲካ ይቁም ህዝባዊ መንግሥት ይመሥረት!
    ሞት ለወያኔ ይገባል።

  3. ማስጠንቀቂያ ፥ ለሕወሓት

    ብሔሮችን ለማጋጨት የሚጠቀምበትን የዘር ፖለቲካ እሳት ላይ ኣማራ ኦሮሞ ትግሬ ምናምን የሚል ዘረኛ የቤንዚን ፕሮፓጋንዳ የምታርከፈክፉ ፕሮፓጋንዳችሁን ኣቁሙ ፤ የሕወሓት የደህንነት ቡድን ሕዝቦችን ለማገዳደልና ለማፋጀት መርዝ ስራዎቹን ይዞ በየክልሉ የዘመተ ስለሆነ አያንዳንዳችን ስለጋራ ኣንድነታችን በመስበክ አና ሕዝባዊ ግጭቶች እንዳይነሱ በመስራት የወያኔን አኩይ ተግባር እናክሽፍ።የሕወሓትን የፍጅት እቅድ ተገን ኣድርገው በጭፍን የዘረኝነት ወንጀል የሚፈጽሙ ካሉ ልንመክራቸው እናልናነቃቸው ይገባል።ሁሉም የኢትዮጵያ ሕዝብ ብሶት ኣለበት፥ይህን ከፋፋይ ስርዐት በኣድነት ሊያስወግድ ይገባል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*