Author: Afandii Muttaqii
ነቢዩ እና ዘመናዊነት
ጽንፈኝነት፣ ምዕራባዊያንና ሚዲያ
ቅዱስ ቁርኣን በአማርኛ ሲተረጎም
——
አፈንዲ ሙተቂ
ታሕሳስ 22/2007
ሀረር-ምሥራቅ ኢትዮጵያ
ሓጂ ሙሐመድ ሣኒ ሐቢብን ስናስታውሳቸው
——
ኢድሪስ ገላውዴዎስ- አንጋፋው “ጀብሃ”
ጸሐፊ፡ አፈንዲ ሙተቂ
—–
“ሻዕቢያ” የሚለው ስም ሲነሳ የዑስማን ሳልህ ሳቤ ስምም አብሮ ይነሳል፡፡ በእርግጥም “ሻዕቢያ” የሚለውን ስያሜ በስራ ላይ ከማዋል ጀምሮ ድርጅቱን በሁለት እግሩ እንዲቆም ያደረገው ሳልህ ሳቤ በመሆኑ እርሱን እንደ ሻዕቢያ መስራች መመልከቱ አግባብ ነው፡፡ የ“ጀብሃ” ስም ሲጠቀስ ደግሞ ብዙዎች የሚያስታውሱት ሓሚድ ኢድሪስ አዋቴን ነው፡፡ ሆኖም ስህተት ነው፡፡ ሃሚድ ኢድሪስ አዋቴ በታሪክ የሚታወሰው ጀብሃ የትጥቅ ትግል በጀመረበት ጊዜ የመጀመሪያውን ጥይት የተኮሰ ሰው በመሆኑ ነው፡፡ “ጀብሃት ታሕሪረል ኤርትሪያ” (በአጭሩ “ጀብሃ”) ወይንም በትግርኛ ስሙ “ተጋድሎ ሓርነት ኤርትራ” (ተ.ሓ.ኤ) የሚባለው የኤርትራ አንጋፋ የፖለቲካ ድርጅት የተመሰረተው ግን ሃሚድ አዋቴ ትግሉን በባርካ በረሃ ከመጀመሩ ከአንድ ዓመት አስቀድሞ ነው፡፡ የድርጅቱ መስራቾች በአብዛኛው በካይሮ የሚማሩ ተማሪዎች ሲሆኑ የቀድሞው የኤርትራ ፓርላማ አባላት የሆኑ ጥቂት ሰዎችና ነጋዴዎችም ተቀላቅለቸዋል፡፡ ከመስራቾቹ መካከል ሙሐመድ ሳሊህ ሁመድ፣ ሙሐመድ አደም ኢድሪስ፤ ሰዒድ ሁሴን፣ ጣሓ ሙሐመድ ኑር፣ ወዘተ…ይጠቀሳሉ፡፡ ይሁንና እነዚህን ሰዎች አሰባስቦ የድርጅቱን መሰረት በመጣል ከፍተኛ ሚና የተጫወተው ሰው ኢድሪስ ገላውዴዎስ ይባላል፡፡
ኢድሪስ ዑሥማን ገላውዴዎስ በ1934 በከረን ከተማ አቅራቢያ በነበረችው “በይት ጀክ” በተባለች አነስተኛ ከተማ ነው የተወለደው፡፡ ኢድሪስ የቤኒአምር (ትግረ) ብሄረሰብ ነው፡፡ አባቱ ሀብታም ነጋዴ የነበሩ ከመሆኑም በላይ በተጨማሪም በምዕራባዊው ኤርትራ ሰፊ እርሻ ነበራቸው፡፡ በመሆኑም ኢድሪስ መደበኛ ትምህርቱን የጀመረው በ1942 የአባቱ እርሻ በሚገኝባትና በኢትዮጵያና ኤርትራ ድንበር ላይ ባለችው የአሊጊደር ከተማ ነው፡፡ በ1947 የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን ካጠናቀቀ በኋላ ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ወደ ከሰላ (ሱዳን) ተላከ፡፡ የፖለቲካ ተሳትፎውንም የጀመረው በከሰላ ከተማ በነበረበት ወቅት ነው፡፡
እንደሚታወቀው በዚያ ዘመን ኤርትራ በእንግሊዞች አስተዳደር ስር ነበረች፡፡ በዘመኑ ኤርትራ ነጻ መውጣት አለባት የሚሉና ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር ትቀላቀል የሚሉ ሁለት ጎራዎች ነበሩ፡፡ የመጀመሪያውን ጎራ የሚያንቀሳቅሰው “ራቢጣ አል-ኢስላሚያ” የሚባል ፓርቲ ሲሆን ሁለተኛውን ጎራ የሚመራው ደግሞ “ማሕበር ሀገር ፍቕሪ” የሚባለው ቡድን ነው፡፡ የኢድሪስ አባት የራቢጣ አባል የነበሩ እንደመሆናቸው “ኤርትራ ነጻ ትሁን” በማለት ከሼኽ ሱልጣን ኢብራሂም ጋር ብዙ ተንቀሳቅሰዋል፡፡ ኢድሪስም በአባቱ ላይ ባየው የትግል መንፈስ በጣም ተማረከ፡፡ መሆኑም “የራቢጣ” የወጣቶች ክንፍ አባል ሆነ፡፡
ኢድሪስ በ1951 ትምህርቱን በከፍተኛ በማዕረግ በማጠናቀቁ ከካይሮ ዩኒቨርሲቲ የስኮላርሺፕ እድል አገኘ፡፡ ወደ ዩኒቨርሲቲው ገብቶም የህግ ትምህርት ማጥናት ጀመረ፡፡ ከዓመት በኋላም የኤርትራ ተማሪዎች ማህበር ሲመሰረት የማህበሩ ሊቀመንበር ሆኖ ተመረጠ፡፡ ኢድሪስ በዚህ ማህበር ኤርትራዊያ ስደተኞችን ለማሰባሰብ በሰፊው ተጠቅሞበታል፡፡
ኢድሪስና ጓዶቹ በስደት ላይ ሆነው የሀገር ቤቱን ሁኔታ በቅርበት ይከታተሉት ነበር፡፡ በተለይም የተባበሩት መንግሥታት ለኤርትራ የሰጠው የፌዴሬሽን መብት እየተሸረሸረ ነው በማለት ተቃውሞአቸውን ያሰሙ ነበር፡፡ በ1957 የኤርትራ ሰንደቅ ዓላማ ታገደ፡፡ ከዓመት በኋላም ትግርኛና ዐረብኛ የስራ ቋንቋ መሆናቸው አብቅቶ በአማርኛ ሲተኩ ደግሞ “ሐረካ” (Eritrean Liberation Movement) የተባለው ድርጅት በሚስጢር ተመሰረተ፡፡ ”
የሐረካ ዓላማ ፌዴሬሽኑ በተቀመጠለት ደንብ መሰረት እንዲሰራ መጠየቅና ለዚህም እስከ መጨረሻው መታገል ነበረ፡፡ በተጨማሪም የትጥቅ ትግልን እንደ አማራጭ አልወሰደም፡፡ ይህ ድርጅት በካይሮ የነበሩትን ተማሪዎች በአባልነት ለማሳተፍ ሲሞክር ግን ተቃውሞ ገጠመው፡፡ እነ ኢድሪስ ገላውዴዎስ የሐረካ ዓላማና የትግል ስልት አዋጪ መስሎ ስላልታያቸው ድርጅቱን እንደ ከንቱ ማህበር ነበር ያዩት፡፡
በ1960 ነው፡፡ ኤርትራዊያን በፌዴሬሽኑ አሰራር ሙሉ በሙሉ ተስፋ ቆርጠዋል፡፡ በርካቶቹም በአጼ ኃይለ ሥላሤ መንግሥት የተሾሙት ቢትወደድ አስፋሓ ወልደሚካኤል ለባርነት ሊዳርገን ነው እያሉ መነጋገር ጀምረዋል፡፡ ከዓመት በፊት የኤርትራ ሰራተኞችና ተማሪዎች ሰላማዊ ሰልፍ ባደረጉበት ወቅት የጸጥታ ሃይሎች በወሰዱት እርምጃ ሳቢያ በሀገር ቤት ተቃውሞ ማድረጉም ብዙ እንደማያራምድ አምነዋል፡፡ በዚህም የተነሳ በርካቶች የመንግሥትና የፓርላማ ስልጣናቸውን በመተው ወደ ውጪ መሰደድ ጀመሩ፡፡ እነዚህ ስደተኞች ካይሮ ከሚገኙት ተማሪዎች ጋር ከተቀላቀሉ በኋላ ስለ ድርጅት ምሥረታ መነጋገር ጀመሩ፡፡ ውይይቱም ፍሬያማ ሆኖ በመውጣቱ በጁላይ ወር 1960 ከነጻነት በስተቀር የፌዴሬሽንን ፎርሙላ የማይቀበል አዲስ ድርጅት ተመሰረተ፡፡ ይህም ድርጅት “ጀብሃት ታሕሪረል ኤሪቲሪያ” ወይንም “ተጋድሎ ሓርነት ኤርትራ” (ተ.ሓ.ኤ) ተብሎ ተሰየመ፡፡
“ጀብሃ” ሲመሰረት የድርጅቱ ሊቀመንበር ሆኖ የተመረጠው የቀድሞ የፓርላማ አባል የነበረው ኢድሪስ ሙሐመድ አደም ነው፡፡ የድርጅቱ ዋና ጸሐፊ ደግሞ ኢድሪስ ገላውዴዎስ ነው፡፡ የድርጅቱ ላዕላይ ምክር ቤት (Supreme Council) አባላት ኢድሪስ ሙሐመድ አደም፤ ኢድሪስ ገላውዴዎስ፣ ሙሐመድ ሳሊሕ አሕመድ፣ ዑሥማን ኢድሪስ ኪያር፣ ሙሐመድ ሰዒድ ኪያር፣ ሲሆኑ ከአንድ ዓመት በኋላም ዑሥማን ሳልህ ሳቤ ተቀላቅሎአቸዋል፡፡
“ጀብሃ” ከተቋቋመ በኋላ በምዕራብ ኤርትራ በረሃ በተበታተነ ሁኔታ ከሚታገሉት እነ ሃሚድ ኢድሪስ አዋቴን መከሳሰሉ ፋኖዎች ጋር ተገናኘ፡፡ ለአዋቴም የግንባሩን ወታደራዊ ክፍል እንዲመሩ ውክልና ሰጣቸው፡፡ በመስከረም 1/1961 በሃሚድ አዋቴ አዝማችነት በጀብሃ ስም የትጥቅ ትግሉ ተጀመረ፡፡ ሃሚድ ኢድሪስ አዋቴ ከአንድ ዓመት በኋላ ሲገደሉ ደግሞ የወታደራዊውን ክንፍ የመምራቱ ስልጣን ለኢድሪስ ገላውዴዎስ ተሰጠ፡፡ በዚህም የኢድሪስ ገላውዴዎስ መቀመጫ ከካይሮ ከተማ ወደ ሱዳኗ ከሰላ ከተማ ተቀየረ፡፡
ኢድሪስ ገላውዴዎስ ከሰላ ከደረሰ በኋላ በሱዳን ውስጥ የሚገኙ ኤርትራዊያን ስደተኞችን እያሰባሰበ ወታደራዊ ስልጠና እንዲያገኙ አድርጓል፡፡ በኋላ ላይ ደግሞ ለድርጅቱ ድጋፍ ለማግኘት ወደ ልዩ ልዩ ሀገራት ተጉዟል፡፡ በዚህም ውጤት አግኝቶበታል፡፡ ለምሳሌ በ1967 ወደ ቻይና ተጉዞ እነ ማኦ ዜዱንግን በማሳመን ለጀብሃ የመሳሪያና የስልጠና ድጋፍ አስገኝቷል (በዚያን ጊዜ ወደ ቻይና ሄደው ስልጠና ካገኙት መካከል አንዱ የአሁኑ የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ናቸው)፡፡ ወደ ኩባ በመሄድም የጀብሃ ተዋጊዎች የፓራ-ኮማንዶ ስልጠና እና የመሳሪያ ድጋፍ እንዲያገኙ አድርጓል፡፡ ከሶሪያና ከኢራቅም ብዙ እርዳታ አስገኝቷል፡፡ የእስያ-አፍሪቃ የወዳጅነት ኮንፈረንስ በተካሄደበት ጊዜም ድርጅቱን በመወከል ተሳትፏል፡፡
ከዚህ ቀደም በጻፍኳቸው ጽሑፎች እንደገለጽኩት “ጀብሃ” የሚባለው ድርጅት በኤርትራዊያን ክርስቲያኖች ላይ ውገና ያካሄድ ነበር፡፡ የዚህም መነሻ “ለኃይለ ሥላሤ መንግሥት አሳልፈው የሸጡን ክርስቲያኖቹ ናቸው” የሚለው የተሳሳተ ፍረጃው ነው፡፡ እርግጥ የኃይለ ሥላሤ መንግሥት ኤርትራዊያን ሙስሊሞች ወደ ስልጣነ-መንግሥቱ እንዳይቀርቡ አድርጓል፡፡ በመንግሥት ስልጣንም ሆነ በፓርላማው ውስጥ የተሰገሰጉት በአብዛኛው ደገኛ ክርስቲያኖች ነበሩ፡፡ ይሁንና የእነዚህ ጥቂት ሰዎች ምግባር ሁሉንም የኤርትራ ህዝበ ክርስቲያን አይወክልም፡፡ ስለዚህ ጀብሃ ኤርትራዊያን ክርስቲያኖችን በጥርጣሬ ማየቱና በድርጅቱ ውስጥ የነበሩትንም እያሳደደ መምታቱ ትክክል አልነበረም፡፡ ድርጅቱንም ለውድቀት ያበቃውም ይህ የውገና አቋሙ ነው፡፡
ይህ ወገንተኛ አቋም የሁሉም የጀብሃ አባላት አቋም አልነበረም፡፡ በመሆኑም በ1969 በወታደራዊ ግንባር የተሰለፉት አባላት ፓርቲው ራሱን እንዲፈትሽና እንዲያሻሽል የሚቀሰቅሰውን የአዶብሃ ኮንፈረንስ ጠሩ፡፡ በኮንፈረንሱ ማጠቃለያም ድርጅቱ ራሱን እስካላሻሻለ ድረስ ካይሮ የሚገኘው ላዕላይ ምክር ቤት የሚያወጣቸውን መመሪያዎች እንደማይቀበሉ አስታወቁ፡፡ የካይሮው ምክር ቤት ኮንፈረንሱን በህገ-ወጥነት ፈረጀው፡፡ ሆኖም በከሰላ የሚገኘው ኢድሪስ ገላውዴዎስ የተነሱትን ጥያቄዎች እንደሚቀበል አስታወቀ፡፡ በዚህም የተነሳ ኢድሪስ ገላውዴዎስ ከአመራሩ ጋር ተጋጨ፡፡ በድርጅቱ ውስጥ የነበረውንም ከፍተኛ ስልጣን አጣ፡፡ ይሁንና የወታደራዊ ኮሚቴ ሊቀመንበርነቱን አልተወውም፡፡
ኢድሪስ ገላውዴዎስ የጀብሃን ወታደራዊ ክንፍ በሚመራበት ወቅት ነበር በዑሥማን ሳልህ ሳቤ እና በኢሳያስ አፍወርቂ የሚመሩት ቡድኖች ከድርጅቱ ተንገጥለው የወጡት፡፡ የጀብሃ አመራር እነዚህን ቡድኖች በወታደራዊ ጥቃት የማጥፋት ውሳኔ አሳለፈ፡፡ ኢድሪስ ገላውዴዎስ ግን ውሳኔው ኤርትራዊያንን የበለጠ ይከፋፍላል በማለት ተቃወመው፡፡ ወታደራዊ ዘመቻዎችንም እንደማያስፈጽም ለድርጅቱ መሪዎች ቁርጡን ነገራቸው፡፡ በዚህም የተነሳ የድርጅቱ መሪዎች ኢድሪስን ከወታደራዊ መሪነቱ አስነሱትና በውጪ ጉዳይ ላይ ሾሙት፡፡
ኢድሪስ ገላውዴዎስ ድርጅቱን በውጪ ጉዳይ ሃላፊነት በሚመራበት ወቅት ድርጅቱ በጣም እየተዳከመ ነበር፡፡ ቢሆንም ኢድሪስ በውጪው ዓለም የድርጅቱን ስም የሚያስጠሩ ስራዎችን ሰርቷል፡፡ ለምሳሌ እ.ኤ.አ. በ1978 ታላቋ ሶቭየት ህብረት ጀብሃ ከደርግ መንግሥት ጋር እንዲወያይ በፈጠረችው መድረክ ላይ ድርጅቱን ወክሎ ተገኝቷል፡፡
ከጥቂት ዓመታት በኋላ ጀብሃ ፍርስርሱ ወጣ፡፡ በኤርትራ ምድር የቀረው ትርፍራፊ ጦሩ በሻዕቢያ ተደመሰሰ፡፡ ድርጅቱም በስም ያለ በተግባር ግን የሌለ ሆኖ ቀረ፡፡ ይህንን የተመለከተው ኢድሪስ ገላውዴዎስ በድርጅቱ መሪዎች ላይ ከፍተኛ ሂስ ጽፎ አቀረበ፡፡ ድርጅቱ ሁሉንም ኤርትራዊያን በእኩል ሁኔታ አለማየቱና ዲሞክራሲያዊ አሰራር የሌለው መሆኑ ለሞት እንዳበቃው አሰመረበት፡፡ በመሆኑም ከጀብሃ አመራር ራሱን አገለለ፡፡
በ1991 ሻዕቢያ ኤርትራን ሙሉ በሙሉ ሲቆጣጠር ኢድሪስ ገላውዴዎስ ለአዲሱ መንግሥት እውቅና እንደሚሰጥ አስታወቀ፡፡ እነ ኢሳያስ አፈወርቂም ወደ ሀገር መጥቶ በስራ እንዲረዳቸው ጥሪ አቀረቡለት፡፡ ኢድሪስም ግብዣውን ተቀብሎ ወደ ሀገር ውስጥ ገባ፡፡ ከ1991-1993 በነበሩት ዓመታትም ከዶ/ር በረከት ሃብተ ሥላሴ ጋር የሪፈረንደም ኮሚሽን ሃላፊ ሆኖ ሰራ፡፡ በተከታዮቹ ዓመታት ደግሞ የህገ-መንግሥት አርቃቂ ኮሚሽን አባል ሆኖ በመስራት ላይ እያለ እ.ኤ.አ በ1998 አረፈ፡፡ የቀብር ስርዓቱም በብሄራዊ ደረጃ ተፈጸመለት፡፡
የጀብሃ አባላት ለኢድሪስ ገላውዴዎስ ሁለት ዓይነት እይታዎች ነው ያላቸው፡፡ ኢድሪስ ድርጅቱን ለመመስረትና የወታደራዊ ክንፉን መሰረት ለመጣል ያደረገውን አስተዋጽኦ በበጎ ዐይኑ ይመለከቱታል፡፡ ከዚያ በኋላ ግን አድርባይ ሆኖ ድርጅቱን ከድቷል በማለት ይኮንኑታል፡፡ የሻዕቢያ አባላትና ደጋፊዎች ግን ኢድሪስ ገላውዴዎስን በበረሃ ውስጥ የተገኘ ተክል አድርገው ነው የሚያዩት፡፡ “ጀብሃ ከውጥኑ ጀምሮ በርሱ ቢመራ ኖሮ ኤርትራዊያን እርስ በራሳቸው አይጋደሉም ነበር” በማለትም ያምናሉ፡፡ ሐቁ የትኛው እንደሆነ ታሪክ ነው የሚፈርደው፡፡ ከብዙ በጥቂቱ ግን ኢድሪስ ገላውዴዎስ ማለት ከላይ የተገለጸው ሰው ነው፡፡
—–
ምንጮች
አለቃ ገብረሃና ማን ናቸው?
ሰለዋት ከልዩ ልዩ አካባቢዎች
የቆምጬ አምባው- ቃለ-ምልልስ (ክፍል አንድ)
ዶ/ር ተወልደን በጨረፍታ
አል-ኸዋሪዝሚን በጨረፍታ
እስላማዊ ኪነ-ህንጻ እና “ሲናን”ን በጨረፍታ
ሁለት ትራጄዲ ተረቶች
ቆምጬ አምባው
በህይወት እያሉ ተረት ለመሆን የበቁትና በጎጃም ክፍለ ሀገር የደብረ ወርቅ ወረዳ አስተዳዳሪ የነበሩት አቶ “ቆምጫ አምባው” በዚህ ፎቶግራፍ የምትመለከቷቸው ሰውዬ ናቸው፡፡ አቶ ቆምጬ በአሁኑ ወቅት በትውልድ ከተማቸው በጥብቅና ሙያ ላይ ተሰማርተዋል፡፡ (ፎቶ፡ ዘ-ኢትዮጵያ ጋዜጣ)

ጂሚ እና ዲስኮ ዳንሰር
ሁለቱ የጎንደር ነገሥታት
በሀይል ብንለው በጣም ያውከናል፡፡
አምር ኢብን ኣስ እና “ፉስጣጥ” (ክፍል ሁለት)
አምር ኢብን ኣስ እና “ፉስጣጥ” (ክፍል አንድ)
![]() |
| Mosque of Amr in Old Cairo in 19th Century |
አምር ግብጽን በሚያስተዳድርበት ጊዜ በክርስትያኖቹ ላይ ይደርስ የነበረውን ጭቆና ሙሉ በሙሉ አስወግዷል፡፡ በህዝቡ ላይ በየምክንያቱ ይጣሉ የነበሩትን ልዩ ልዩ የታክስ ዓይነቶች በማስቀረት ሁሉም ዜጎች ዓመታዊውን “ዑሽር” (አስራት) እና “ዘካት” ብቻ እንዲከፍሉ አድርጓል፡፡ በመንግሥቱ ቢሮክራሲ ውስጥም ክርስትያኖቹን አሳትፏል፡፡ የቤተ-ክርስቲያኖች ይዞታ የሆኑ መሬቶችና ንብረቶች እንዲከበሩም አድርጓል፡፡
የህንድ ፊልም ትዝታ
ኢራን፣ “ሩሚ” እና “መስነቪ”
የማይረሱ የፕሬስ ውጤቶች-2
የኢትዮጵያ አብያተ ክርስቲያናትን በጨረፍታ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናት ሲጠቀሱ በቅድሚያ የሚታወሱት በላስታ አውራጃ፣ በ“ሮሃ” (ላሊበላ) ከተማ አጠገብ ከአንድ-ወጥ ድንጋይ ተፈልፍለው የተሰሩት አስራ አንድ ቤተ ክርስቲያናት ናቸው፡፡ የአስራ አንዱ ቤተ ክርስቲያናት ስም እንደሚከተለው ነው፡፡ትግራይ ትናፍቃለች!
“ኦሮማይ” እና በዓሉ ግርማ
መጽሐፉ የብዙዎቹን አትኩሮት የሳበው ታሪኩ እውነት ነው ስለተባለ እና በመጽሐፉ ሳቢያም የደራሲው ህይወት ለአደጋ በመጋለጡ ይመስለኛል፡፡ ከመጽሐፉ ዐቢይ ገጸ-ባህሪያት አንዱ የሆኑት ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ “የደም እምባ” በተሰኘው መጽሐፋቸው ተመሳሳይ እይታ አንጸባርቀዋል፤ እንደ ሻለቃ ዳዊት አባባል ኦሮማይ ባይታገድ ኖሮ ተወዳጅነቱ ይሄን ያህል አይገዝፍም ነበር፡፡ ሆኖም እኔ በዚህ አባባል አልስማማም፡፡ ደራሲው ባይሞት እና ታሪኩ እውነተኛ ባይሆን እንኳ “ኦሮማይ” ተደናቂ የመሆንን እድል አያጣም ነበር ብዬ አምናለሁ፡፡ ለዚህም በርካታ አብነቶችን መጥቀስ ይቻላል፡፡ የኮማንደር “አያልነሽ” ወጎች
————-
The writer, Afendi Muteki, is a researcher of the Ethnography and History of the peoples of East Ethiopia. He is an author of “Harar Gey”, an Ethnography book about the historical city of Harar. You can read some of his articles on his facebook page.
Facebook https://www.facebook.com/afendimutekiharar
ኢትዮጵያዊው “ጌታቸው ካሳ” እና ሱዳናዊው “ሳላሕ ኢብን ባዲያ”
ለመጀመሪያ ጊዜ ያየሁት የዓለም ዋንጫ
ፀሐፊ፡ አፈንዲ ሙተቂ
“ቺርስ”- ለኢትዮጵያና ኤርትራ ህዝቦች ወዳጅነት
የኢሠፓ ምስረታ በዓል እና ሀገር አቀፉ ረሃብ (መስከረም 2/ 1977)
ዕለቱ መስከረም 2/1977 ነበር፡፡ በዚያች ዕለት ደርግ ከአጼ ኃይለሥላሤ መንግሥት ስልጣን የተረከበበት 10ኛው የአብዮት በዓል ይከበር ነበር፡፡ ያ በዓል ከቀደሙት በዓላት ለየት የሚልበት አንድ ነገር ታይቶበታል፡፡ ይህም የስመገናናው የኢትዮጵያ ሠራተኞች ፓርቲ (ኢሠፓ) ምስረታ በይፋ መታወጅ ነው፡፡ ይህንን ድርብ ደስታ ለማድመቅ ተብሎ የተዘጋጀው ክብረ በዓል በሀገራችን ታሪክ በድጋሚ አልታየም፡፡ ለዚህ በዓል ማክበሪያ በትንሹ አንድ መቶ ሚሊዮን ብር ወጪ ሆኗል (ያ ገንዘብ በአሁኑ ስሌት ሁለት ቢሊዮን ብር ሊሆን ይችላል)፡፡
ጥቂት ቆይታ- ከአል-በላቢል ጋር
ሃየሎም አርኣያን በጨረፍታ
![]() |
| Hayelom Ar’aya |
ኮ/ል መንግሥቱ ኃይለማሪያም እና የሀይሌ ፊዳ ሞት
አንጋፋው ሻዕቢያ
“አሕመድ ያ ሐቢቢ”
ተስፋዬ ደበሳይ- አንጋፋው ኢህአፓ
ብርሀነ መስቀል ረዳን በጨረፍታ
![]() |
| Berhane Mesqel Redda |
ዋለልኝ መኮንን-አፈና ያልገታው የአመጽ ድምጽ
![]() |
| Walelign Mekoneen |
ሼርሎክ ሆምዝ
በአማርኛ የተተረጎሙ ታላላቅ መጻሕፍት
ከጊቤ ባሻገር ያለችው ጂማ (ክፍል ሁለት)
በፍቅር በናፍቆትልቤን የምትወዘውዘው ።
አቦል ጀባብላኝ ቡናዋን ብቀምሰው፣
እግሬ ወደጅማ ሱስ አመላለሰው ።
እንግባ አይመሽምወይ ፣
ከጊቤ ባሻገር ያለችው ጂማ
![]() |
| The palace of Abba Jifar, Jimma, |
በልጅ እያሱ አሟሟት ዙሪያ
የትግል ስም (Nom De Guerre)
“አል-ካብሊ”፤ “ሸዛ ዛሂር” እና “ዓሊ ቢራ”
“ጥጋብ አይቻልም”
ሁለት የሀረር ተረቶች
መሐመድ ወርዲ- ዘመን የማይሽረው አርቲስት
ኸሊኒ ፊሹጁኒ ዩምኪን ገልቢ ይክሳዚይክ
የኤርትራ ህልም!
ግመል-ጊመል-ገመል-ጀመል (ክፍል ሁለት)
“ልጆቼ ሆይ! በዚህ ምድር ላይ ስኖር የተገነዘብኩት ትልቁ ነገር የዕውቀት አስፈላጊነት ነው። ያለ ዕውቀት የሚሄድ ሰው በጭለማ እንደሚጓዝ በቅሎ ይደናበራል። ንግግሩም ሆነ ስራው አያምርለትም። ስለዚህ አዋቂና ታዋቂ እንድትሆኑልኝ እሻለሁ። ነገር ግን መምህራችሁን በጥንቃቄ መምረጥ አለባችሁ። ለዚህም ይረዳችሁ ዘንድ እነኝህን 17 ግመሎች ትቼላችኋለሁ። ታዲያ ግመሎቹን የምትከፋፈሉት በሚከተለው ቀመር መሰረት ይሁን።
• የመጀመሪያው ልጄ የግመሎቹን 1/2ኛ ይውሰድ።
• ሁለተኛው ልጄ 1/3ኛ ያህሉን ይውሰድ።
• ሶስተኛው ልጄ 1/9ኛ ያህሉን ይውሰድ።
አባታቸው ይህንን ተናዝዞ አረፈ። ልጆቹም አባታቸውን ከቀበሩ በኋላ ግመሎቻቸውን እየነዱ የተነገራቸውን ዓይነት መምህር መፈለግ ጀመሩ። በየከተማው ወዳሉ አዋቂዎች እየቀረቡ ከአባታቸው በተሰጣቸው ስሌት መሰረት ግመሎቻቸውን እንዲያካፍሉአቸው ጠየቁ። ነገር ግን አንድም ሰው ስሌቱን መፍታት አልቻለም። ሌሎች በርካታ አዋቂዎችንም አማከሩ። ይሁንና ሒሳቡን አውቃለሁ የሚል ሰው ጠፋ።
“አስራ ሰባቱን ግመሎች በአባታችሁ ቀመር መሰረት ባከፋፍላችሁ ውጤቱ በክፍልፋይ (fraction) የሚገለጽ ይሆናል። እንደዚያ ከሆነ ግመሎቹን መቆራረጥ ሊኖርብኝ ነው ማለት ነው። ስለዚህ እንዲያ እንዳይሆን የራሴን አንድ ግመል ልጨምርበትና የግመሎቹ ብዛት 18 ይሁን። ይህ ከሆነ ዘንዳ የአባታችሁ ቀመር የሚቀጥለውን ውጤት ያስገኛል።
***** ***** *****
አፈንዲ ሙተቂ

















