“ማስተር ፕላኑን ህዝቡ እንደማይቀበለው ተረጋግጧል” – ኦህዴድ – “ማስተር ፕላኑ መሰረዝ ያለበት በፓርቲ ውሳኔ አይደለም” – ተቃዋሚዎች
“ማስተር ፕላኑን ህዝቡ እንደማይቀበለው ተረጋግጧል” – ኦህዴድ – “ማስተር ፕላኑ መሰረዝ ያለበት በፓርቲ ውሳኔ አይደለም” – ተቃዋሚዎች
Addis Admass :- ማስተር ፕላኑ ተግባራዊ እንዳይሆን የተሰረዘው ህዝቡ እንደማይቀበለው በውይይት በመረጋገጡ መሆኑን የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ ፅ/ቤት የገለፀ ሲሆን ተቃዋሚዎች በበኩላቸው፤ ማስተር ፕላኑ መሰረዝ ያለበት በም/ቤት እንጂ በፓርቲ ውሳኔ አይደለም ብለዋል፡፡
የኦሮሚያ ክልልን የሚያስተዳድረው የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ ሰሞኑን ለ3 ቀናት በአዳማ ከተማ ባደረገው ስብሰባ፣ ላለፉት ሁለት ዓመታት ሲያወዛግብ የከረመው የአዲስ አበባና ፊንፊኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ማስተር ፕላን ሙሉ ለሙሉ እንዲቀር ውሳኔ አስተላልፏል። የፓርቲውን ውሳኔ በተመለከተ የተጠየቁት የድርጅቱ ማዕከላዊ ኮሚቴ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ዳባ ደበሌ፤ በክልሉ የተለያዩ ቦታዎች ከአርሶ አደሩ፣ ከወጣቱና በየደረጃው ከሚገኝ የህብረተሰብ ክፍል ጋር በተደረገ ውይይት ማስተር ፕላኑን ህዝቡ እንደማይቀበለው አረጋግጠናል ብለዋል፡፡
ኦህዴድም የህዝቡን ፍላጎት መሰረት አድርጎ ማስተር ፕላኑ ሙሉ በሙሉ እንዲሰረዝ መወሰኑን የገለፁት አቶ ዳባ፤ ህዝቡ በውይይቱ ወቅት የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ማንሳቱንም ጠቅሰዋል፡፡
ተቃዋሚ ፓርቲዎች በበኩላቸው፤ ማስተር ፕላኑ ቀርቷል የሚለው ምላሽ የተሰጠው አሳማኝ ባልሆነ መልኩ ነው ሲሉ ተችተዋል፡፡
በኦሮምያ ክልል ማስተር ፕላኑን መነሻ በማድረግ የተነሳውን ተቃውሞና ግጭት ተከትሎ ተቀዳሚ ም/ፕሬዚዳንቱ አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ ከ500 በላይ አመራርና አባሎቹ እንደታሰሩበት የገለፀው የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ)፤ “ማስተር ፕላኑን መሰረዝ ያለበት ፓርቲ ሳይሆን ምክር ቤቱ ነው” ብሏል፡፡
“ለህዝቡ ጥያቄ የተሰጠው ምላሽ በቂ አይደለም” ያሉት የኦፌኮ ሊቀመንበር ዶ/ር መረራ ጉዲና፤ ጥያቄው የአዲስ አበባ መስፋፋት ብቻ ሳይሆን የሚፈናቀለው ገበሬ የካሳና ዋስትና ጉዳይን በዋናነት የያዘ በመሆኑ ማስተር ፕላኑ ተሰርዟል ብቻ ብሎ ማለፍ በቂ መልስ አይሆንም ብለዋል፡፡
“ሁለት ወር ሙሉ ብዙ ሰብአዊ ቀውስ ሲፈጠር ኦህዴድ የት ቆይቶ ነው ሰሞኑን በአስቸኳይ ስብሰባ ይሄን ውሳኔ ያስተላለፈው?” ሲሉ የጠየቁት ዶ/ር መረራ፤ በግጭቱና ተቃውሞው ሳቢያ የሞቱና የታሰሩ ሰዎች ጉዳይ በዝምታ መታለፉንም ነቅፈዋል።
“የኛ ክርክር አዲስ አበባ ባዶ መሬት ላይ አትስፋፋ የሚል አይደለም” ያሉት ሊቀመንበሩ፤ ዋናው ጥያቄ ገበሬው ከመሬቱ መፈናቀል የለበትም የሚል ሲሆን የግድ ከሆነም ቀሪ እድሜውን ሊያኖረው የሚችል ካሳ ተከፍሎት ሊነሳ ይገባል የሚል ነው” ብለዋል፡፡ የኦሮሞ ህዝብ ኦህዴድን እየሰማው አይደለም ያሉት ዶ/ር መረራ፤ ድርጅቱ ህዝቡን ይቅርታ ጠይቆ ስልጣን መልቀቅ አለበት ብለዋል፡፡
የመድረክ ሊቀመንበር ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ በበኩላቸው፤ “እኛ እስከምናውቀው ማስተር ፕላኑ በምክር ቤት አዋጅ የፀደቀ በመሆኑ መሻር ያለበትም በአዋጅ ብቻ ነው” ብለዋል፡፡ መንግስት፤ አዋጁ ገና በረቂቅ ደረጃ ያለና ለህዝብ ውይይት በሰፊው ያልቀረበ መሆኑን በመጥቀስ እንደፀደቀ ተደርጎ የሚነገረው ትክክል አለመሆኑን በተደጋጋሚ መግለፁ ይታወሳል፡፡ ፕ/ር በየነ ግን አይቀበሉትም። “እኛ እስከምናውቀው ፀድቋል ተብሎ ነው ቢሮ ተደራጅቶለት ተግባራዊ እንቅስቃሴ ውስጥ የተገባው” ይላሉ፡፡
“የዲሞክራሲ፣ የሰብአዊ መብትና የህግ የበላይነትን እየጠየቀ ላለ ህዝብ ማስተር ፕላኑ እንዲቆም ተወስኗል ማለት ብቻ በቂ መልስ አይደለም ያሉት የኢዴፓ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ወንደሰን ተሾመ በበኩላቸው፤ ኦህዴድ ፈታኝ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡
የህዝቡ ጥያቄ እየሰፋ ሄዶ ከማስተር ፕላኑ በላይ ፖለቲካዊ ይዘት ከተላበሰ በኋላ ኦህዴድ መግለጫ መስጠቱ ብዙ ለውጥ ያመጣል ብዬ አላምንም ያሉት አቶ ወንደሰን፤ ማስተር ፕላኑ ተሰርዟል የሚለው ውሳኔ ለህዝቡ በቂ ምላሽ አይደለም ብለዋል፡፡
የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ዳባ ደበሌ በበኩላቸው፤ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት ድርጅቱም ሆነ መንግስትም ያስቀመጣቸውን አቅጣጫዎች የአፈፃፀም ችግሮችን በመቅረፍ ተግባራዊ ያደርጋሉ ብለዋል፡፡
የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት በበኩሉ፤ የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ ማስተር ፕላኑ እንዲቆም መወሰኑ እየተገነባ ያለው ዲሞክራሲያዊ ስርአት በህዝብ ሉአላዊ የስልጣን ባለቤትነት ላይ የተመሰረተ መሆኑን አረጋግጧል ብሏል – ትናንት ለዝግጅት ክፍላችን በላከው መግለጫ፡፡
“የህዝቦች ውሳኔ የተከበረበት ህገ መንግስታዊ ስርአት በጠንካራ መሰረት ላይ እየተገነባ ነው” ያለው መግለጫው፤ የክለሉ መንግስትና ህዝብ የመልካም አስተዳደር ችግሮችንም ሆነ የልማት ጉዳዮችን በውይይትና ምክክር ለመፍታት መዘጋጀታቸውን አመልክቷል፡፡
የህዝብን ጥያቄ በመጥለፍ ሁከትና ብጥብጥ ሲፈጥሩ የቆዩ አካላት ከዚህ ውሳኔ ሊማሩ ይገባል ያለው ጽ/ቤቱ፤ እኒህ ወገኖች ወደ ህዝብ መድረኮች በመምጣት የሰለጠነ የሃሳብ ክርክር እንዲያደርጉ መክሯል፡፡፡
This regime still degrading people. They think they are smart, peoples know you that you all gathered in the regime are so stupid. But you don’t know the people. your knowledge is established by laying, robbing, killing hating….so, what ever the regime says, no one believed. We know the racist and narrow minded. May God bless our people & land.
እንዲቆም ተደርጓል እና አዋጁ ተሰርዟል ማለት በጣም ሠፊ ልዩነት አላቸው አንሸዋወድ።
Weyane, I appeal t you to abandon the treacherous Master plan and listen to our Oromo brothers, By killing Ethiopians you are sowing the seed of hatred towards Tigrayans and we do not want that. Learn what as led to Tigrayan rebellion and do not undermine the will of the great Oromo public.
Eskrbito alekebgn be bomb tsaf yemigerm new ye zendro lijoch be bomb metsaf jemrewal hitsan lij enatu jerba lay tazlo cigara yachesal yemibalew ewnet new
ህዝብ አይሸውድም…………ነቅተናል እንግዲ
እነዚህ አህዮች ዕውነትም ከአህያ ጋር በርሃ እያሉ እንደ አህያ እያሰቡ ነው። you fkn ideots ሕዝቡ አልተቀበለውም ? ? አባይ ፅሃይ የተናገረውን ሕዝብ የሚረሳ ይመስልስችኋል እንዴ ? ? you asshole opdos why are you being used for woyanes against your people ? ? ሕዝቡን መቸ ነው ያማከራችሁት።ሰይጣን ዻቢሎስ እያላችሁ የሰደባችሁት ሕዝብ ይቅርታ አይገባውም ? ? ? ለገደላችኋቸው ወጣቶችና እናቶች እንዲሁም አባቶችስ ተጠያቂ የለም ? ? ? አባይ ጽሃይ ለምን አይናገርም ? ? ? Why is opdo doing the dirty job of tplf? ? ? you stinky assholes ! ! !
selam bus is changed to ethio bus. whom do you cheat ethiopian people or the opdo. fuck you eat your shit you woyanes.
ዶ/ር መራራ ጉዲና ህወሃትን በቻካ ስደግፍ ነበር ብለዋል 25 አመት ሙሉ ደግሞ ህወሃት ከትግሪ አልፎ የተቀሩትን ኢትዮፒያኖች እንዲት ሊቆጣጠር እንደቻለ ያውቃሉ የኦሮሞ ክልል ተብሎ በወያኒ የተሰየመው እንደ አጋጣሚ ሆኖ የአዲስ አበባ ጎረቢት በመሆኑ እንጂ ኦሮሞ ክልል እንደ አምሃራው ከትግሪ ክፍለ ሃገር ጎን ቢሆን ኖሮ የመጀመሪያው የዘር ማጥፋትና ወረራ ተካሂዶ ትግሪ ክፍለ ሃገሩን ወደ ክልል ያረገበት ሲስተም ኦሮሞም ሊሆን ይችል ነበር ይህ ዘር እያጠፉ መውረር ከትግሪ እየሰበሰቡና እያደራጁ ወደሊላ ቦታ ማስፈር በነጋዲ ስም በ ኢንቨስተር ስም መላ አምሃራን አዳርሶ ጋቢላ ተጨፍጭፎ አፋር ተጨፍጭፎ አዲስ አበባ በዘር ማጽዳት ደሃ ሃብታም መሪቱን ቢቱን በወያኒ ትግሪ እየተቀማ ባለ ቭላ ቢቶች ባለ ፎቆች ነጋዲዎች እንዲሆኑ ያደረጋቸው አይናችሁ እያየ አጥገባችሁ መተው ደሃ ኦሮሞ ሊጨፈጨፍ የቻለበት ምክንያት እንደናተ ያሉ የዘር ፖለቲከኞች ከስህተታችሁ ተምራችሁ የለም የ ኢትዮፒያ ህዝብ ኢትዮፒያን በጋራ ሞቶ አገር አቁማል እንደየ ታሪኩ ሰፍራል ለምዙ ሺ ዘመናት ባህሉም ሆነ ቃንቃው ዘሩ ተደበላልቆ ኖራል ሳይሆን አይ እኒ ለኢትዮፒያ ህዝብ ሳይሆን ለ ዘሪ ኦሮሞህዝብ ብቻ ነው የምታገለው ለከሊዘር እየተባለ ወያኒ ያው ክልል ሰጠሁህ በተረፈ ይህን ክልል ለመስጠት ሞቺ ስለሆነ የመጣሁት የትግሪ ዘር የማይገዛው የማይተቀምባት ኢትዮፒያ እና ለትግሪ ዘር የማይገዛ ይጥፋ እንዳለ እያዩት ነው ዛሪ አይደለም ስለዚህ ይህ ደግሞ ዛሪ ማንም በዘር ቆምኩ የሚል ሁሉ ንጽሃን ዚጎችን ሊያድን አልቻለም ስለዚህ ዲሞክራሲ ማለት አገርን በዘር በክልል መከፋፈል እና መለያየት አይደለም አገር ቆማል ህዝቡ እንደየታሪኩ ሰፍራል የሚያስፈልገው ዲሚክራሲ ሰረአት ነው ዲሞክራሲ ስረአት ማለት በዘር ከፋፍላችሁ አንተ የዚ ዘር ስለሆንክ ይሂ ክልል ያንተ አይደለም ማለት በራሱ አገርን መቀማት ነው ስለዚህ ፈረጆች ዲሞክራሲ ስረአት የገነቡት አገር አፍርሰው አይደለም የአገር ታሪክ በቆሻሻ ለውሰው አይደለም ከዘመኑጋ የሚሂድ ስረአት ለውጠዋል እነሱም የኛ አገር አባቶች አገር እንደ አገር ሲያቆሙና ያሳለፉትን ስረአት ነው የተከተሉት ስለዚህ የወያኒ ገዳይ ስረአት አስተሳሰብ በዘር ከልሎ የኒዘር ብቻ ከኒዘር ውጭ የሚል በምንም ተአምር የኢትዮፒያን ህዝቦች እንደ አገርም ሆነ እንደ ዘራቸው አያቆምም ኢትዮፒያ ደግሞ የ 3 እና የ4 ብሂር አገር አይደለችም ስለዚህ ታሪካን ተቀብላችሁ እየተጨፈጨፈ ያለው ህዝብ በጋራ እንዲቆም መስራት እና ያገሩ ተጠቃሚ እንዲሆን ማድረግ አሁንም ምሳሊ መስጠት ያለባችሁና ከወያኒ ለመላቀቅ በተቃዋሚነት ቆምን የምትሉ መጀመሪያ በዘር ሳይሆን በ ኢትዮፒያዊነታችሁ ኢትዮፒያን አድን መግባት አለባችሁ አለበለዚያ በያዛችሁት መንገድ እስከወዲያኛው የዘር አስተሳሰብ ሁሉንም ወደ ቁልቃል እንጂ ወደ ዲሞክራሲነት እና የአገር ባለቢትነት አያደርግም
1. Ethiopiawiyann eyegedele
neber Tgrai woyanie slTan yeyaze.
2. Yeselamawi tgl party abaloch, yeselamawi teqawmo selfeñoch,
beselamawi yeteqawmo Tyaqie aqrabiwech ena keqrb hunew yeteqawmo hasab aramajoch grmbiT (paradox) neger huno ye woyanien edmie arazmewal.
Mkniyatum enezihn mesewat lihonu yetezegaju Telotochun woyanie saydekm beqelalu beglT deretachewn le Tyt agalTew agnto aserachew, gedelachew, aswegedachew. Des eyalew yfejachewna dlun be fiesta, beshumet ena beshlmat yakebral. Edmiewn arazeme.
Endiwedm woyanien tegawemn teblo edmiewn marazem gafña (paradox) yehone neger new!
3. Yh ziediew 25 amet slTan lay aqoytotal. Be selamawi teqawmo memot yewoyanien edmie arazami new.
4. Madreg yalebn tgrain woyanien be yalubet wedaj meslen, Tru agaTami snageñ beziedie mechefchef new. AyTn endemegdelu aynet new.
5. Be Teqlala be ethiopia yalenew
BE YEBOtAWNA BE YEGIZIEW ke 1 eske 2 woyanien demesesn malet eko qenesnachew new. Yalqaluna neTa weTan malet eko new.
Zm blen kemnaleq enesun enmta.
ስለ ኦሮሞ ጉዳይ ካልገባችሁ ታሪክን ረጋ ብላችሁ አንብቡ:: ዝም ብላችሁ ከመጻፋችሁ በፊት በ21ኛው ክፍለ ዘመን ኦሮሞን እንደ ጭራቅ (የሌለ አውሬ) ከመሳላችሁ በፊት ቆም ብላችሁ አስቡ:: ኦሮሞ ማለት ኦነግ: ኦሮሞ ማለት ገላሳ ዲልቦ: ኦሮሞ ማለት ጁሃር መሃመድ: ኦሮሞ ማለት ኦፒዲኦ: ወዘተ … አድርጋቸሁ መውሰድ ትልቅ ስህተት ይመስለኛል::
አንጋፋው (ትልቁ) የኦሮሞ ልጅ በሆነው ቦረና ኑና ጠይቁ ቦረና = ሰው የሚል አባባል ታገኛላችሁ:: ኦሮሚያ ወይም ቦረና ውስጥ ለመኖር ሰው መሆን ብቻ በቂ መሆኑን ትረዳላችሁ:: ይህ የኦሮሞ (ቦረና) ምልከታ ነው::
ስለዚህ የኦሮሞን ጉዳይ ወሳኝ ከኦነግ: ከገላሳ ዲልቦ: ከጁሃር መሃመድ: ከኦፒዲኦ ጋር በማያያዝ አታሳንሱት:: ኦሮሞ በሃገሪቱ ውስጥ በቁመቴ ልክ መብቴና ጥቅሜ አልተጠበቀልኝም ብሎ ቢነሳ ይህ ሁሉ ውርጅብኝ ለምን ይወርድበታል:: ትግሉ ራሱን ከጭቆና ለማውጣት ስለሆነ ከተቻለ ማገዝ ካልሆነ ዝም ማለት ይገባል ባይ ነኝ:: በሃረሪቱ ያልተበደለ ስለሌለ ሁሉም በሚያዋጣው መንገድ መታገል እንጅ የኦሮሞን ትግል የግድ በዚህ ወይም በዚያ መንገድ ካልሆነ ብሎ ጥላሸት መቀባት የአዛዙን ስርዓት ማራዘም እንጅ ለማንም አይጠቅምም::
በሌላ በኩል ደግሞ የኦሮሞ ትግል ሌላውን ለመበደል ከሆነ የትም አይደርስም:: ትግሉ ህዝቡን ከዘረኛ አገዛዝ ነጻ ለማውጣት ከሆነ ደግሞ ሌሎችም በራሳቸው መንገድ በመታገል ነጻ ይውጡ:: ከዚያ በመቀጠል ሁላችንም እኩል መብታችን በተከበረባት ሃገር በአንድነት መኖር እንችላለን:: ስለዚህ ሁሉም በያለበት የራሱን የቤት ስራ ይስራ:: ኦሮሞው በራሱ ለብቻው ቢታገል እንደ ወንጀል ባይቆጠር መልካም ነው እላለሁኝ::
የኦሮሞ ጉዳይ በተነሳ ቁጥር ኦነግንና ጁሃር መሃመድን ማጥላላት የኦሮሞን ጉዳይ ከማሳነስ አልፎ የኦሮሞን ጉዳይ ወሳኞች ኦነግና ጁሃር መሃመድ የሆኑ ያስመስላል:: ህዝቡ ሎጂካል አይደለም የሚል ያስመስላለና ህዝብ ደግሞ የሚበጀውን ያውቃል:: ቦረና = ሰው የሚለውን ብሂል ኦነግና ጁሃር አይደለም ኦሮሞን ያስተማሩት:: በመጨረሻም የኦሮሞን ትግል ለመደገፍ ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው ባይ ነኝ::
ገመዳ ቦና – ከቦረና
ገመዳ እሺ እንዳልክ ይሁን በዚህ ደስ ካለ ለደስታ ብዙ ገንዘብ አትፈጂም ማለት ነዉ ወይ መታደል። ለመሆኑ ኦሮሞ ነህ ሻቢያ ቅልዱብን ተስፋዬ ገዳም ስሜን ቀይሪያለሁ ኤርትራ ተስፋ የለዉም ብሏል አንተም አንዱ ከሆንከ መንገዱን ምን ያድርግልህ ልበልህ ደግነቱ በትግራይ መሰለኝ የምትገባዉ እዛዉ ትጠያየቃላችሁ