በኦሮሚያ ክልል ተቃውሞው አንደቀጠለ ነው።
በኦሮሚያ ክልል ተቃውሞው አንደቀጠለ ነው። #Ethiopia #Oromoprotests #MinilikSalsawi
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) ዛሬም በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ወረዳዎች ተማሪዎች አና ነዋሪው በኦሮሞ ሕዝብ ላይ የሚደረገውን ግድያ አና እስር በመቃወም ድምጻቸውን ሲያሰሙ ውለዋል። በዚህም መሰረት በሸዋ ጅባት አውራጃ ሻናን ከተማ በሃረርጌ በደኖ አንዲሁም በተለያዩ ኣከባቢዎች ሕዝቡ ሰልፍ ከመውጣት ጀምሮ በተለያየ መልኩ ተቃውሞውን ሲያሰማ በሻናን ከተማ የወያኔ ወታደሮች ወደ ተማሪውና ሕዝቡ በመተኮስ በርካቶችን ሲያቆስሉ በበደኖ አንዲሁ የጸጥታ ተቃውሞ ባደረጉ ተማሪዎች ላይ ኣስከፊ ድብደባ በመፈጸም ኣስራሰባት ተማሪዎችን ሲያስሩ ከወታደሮቹ ለመሸሽ የሞከሩ ተማሪዎችን ሸሽጓል የተባለ ኣንድ ነጋዴን ክፉኛ በመደብደብ ኣስረውታል።
ይህ በእንዲህ አንዳለ በወለጋ ማና ሲቡ ወርዳ ተማሪዎች ተቃውሞ የቀጠሉ ሲሆን በድሬዳዋና ኣምቦ ዩንቨርስቲም ውጥረት ሲያጠላ የሳይበር ጠላፊዎች የጅማን ዩንቨርስቲ ድረገጽን በመጥለፍ በኦሮሞ ክልል የሚካሄደውን ግድያ የሚቃውሙና የታሰሩ ይፈቱ እንዲሁምተቃውሞውን የሚደግፉ መልእክቶች ኣስተላልፈዋል። #ምንሊክሳልሳዊ
