አንድሪያ ፒርሎ በእግርኳስ ህይወቱ ያየው ምርጡ ወጣት ተጨዋች ጠቅሷል
By Eyob Dadi
የቀድሞው የኤሲሚላን እና የጁቬንቱስ አማካይ የነበረው አንድሪያ ፒርሎ በእግርኳስ ቆይታው ያየው ምርጡ ወጣት ተጨዋች ተናግሯል።
ፒርሎ የቡድን አጋሩ የነበረው ፓል ፓግባን ምርጡ ወጣት ተጨዋች ሲል ያወድሰዋል።
ፓግባ 2012 ላይ በማንቸስተር ዩናይትድ በቂ የመሰለፍ እድል በማጣቱ ወደ ጣሊያኑ ጁቬንቱስ ማምራቱ ይታወሳል።
ለ ጋዜታ ዴሎ ስፓርት የተናገረው ፒርሎ እንዲህ ብሏል
“ፓግባ እስካሁን ካየኋቸው ምርጡ ወጣት ተጨዋች ነው።ከመጀመሪያው የልምምድ ጊዜው ጀምሮ ትልቅ ተጨዋች እንደሚሆን ተረድተናል።እሱ ቀጭን ነው ነገርግን እግሮቹ የትም ቦታ እንዱሆን ይፈቅዱለታል።አሁን ግን ትልቅ እና ጠንካራ ሆኗል።ሲል አድናቆቱን ይገልጻል።
