አንዳንድ ፣ አሸባሪ ፣ ልማት እና ወዘተ፣ የቃላት ትርጉም ( ሄኖክ የሺጥላ )

አንዳንድ ፣ አሸባሪ ፣ ልማት እና ወዘተ፣ የቃላት ትርጉም ( ሄኖክ የሺጥላ )

አንድ ወዳጄ <አንዳንድ> የሚለው ቃል ትርጉም ምን ማለት እንደሆነ ልታስረዳኝ ትችላለህ ወይ ብሎ የቃላት እውቀቴን ተፈታተነው ። በመጀመሪያ በፈረንጅኛው a small amount or number of people or things የሚለው ሊሆን ይችል ይሆን አልኩ ? ሲገባኝ ግን <አንዳንድ> በ ( contextual meaning ) አገባብ ትርጉሙ ላይ መሰረት ያደረገ የቃላት ትርጉም ከሆነ ደሞ ሊለይ እንደሚችል ስለማውቅ ፣ አንዳድን ማለት አንዳንድ ጊዜ ብዙ ማለት ሲሆን አንዳንድ ጊዜ ደሞ ጥቂት ማለት ነው አልኩት ሳስረዳውም የሚከተለውን ምሳሌ ጠቀስኩ ።

አንዳንድ የሚለውን ቃል የሰማኸው በ ኢትዮጵያ ቴሌቭዥን እና ራዲዮ ከሆነ ፣ አንዳንድ ማለት እጅግ በጣም ብዙ ፣ ሊቆጠር የማይችል ፣ ህልቆ-መሳፍርት ፣ የትየ-ለሌ ፣ ወይም ( negative infinitive ) ወይም እንጦሮጦስ ማለት ሊሆን ይችላል ። ይህንን አንዳንድ የሰማኸው ሌላ ሀገር ከሆነ ትርጉም ( insignificant ) ( ይህን-ታህል ) ወይም ጥቂት ወይም ከቁጥር የማይገባ ማለት ነው ። ስለዚህ የቃላት ትርጉም ከቃሉ ምንነት ተነስተን ብቻ ትርጉም የምንሰጠው ነገር እንዳልሆነ ልንረዳ ይገባል ።

ለምሳሌ አሸባሪ ( terrorist ) የሚለውን ቃል ኢትዮጵያ ውስጥ ከሆነ የሰማኸ ፣ ትርጉሙ ጋዜጠኛ ፣ ጠሐፊ ፣ የመንግስትን አሰራር ተጠያፊ ። ሀይማኖተኛ እና ህገ መንግስቱን አክብሮ የሚኖር ሕዝብ ፣ ህገ መንግስቱን ረግጦ በሚኖር መንግስት የሚወጣለት ስም ማለት ሲሆን በሌሎች ሀገሮች ግን አሸባሪ ማለት ከጥሬ ትርጉሙ ሌላ የአገባብ ትርጉም የለውም ።

ለምሳሌ ልማት የሚለውን ቃል ብንወስድ ። ይህ ቃል በኢትዮጵያ በከፍተኛ ሁኔታ ተነግሮለት ግን ያን ያህል አድማጭ ያላገኘ ቃል ነው ። ምክንያቱ ደሞ < ልማት > የሚለው ቃል በሀገራችን ኢትዮጵያ ሲተረጎም የሚከተለውን ቀለም ስለሚይዝ ነው
ልማት ማለት ፣ ህወሓት ሲሰርቅ ሌላው ቆሞ የሚያይበት የኑሮ መስመር ነው ።
ልማት ማለት ፣ ያንድ ጎሳ አባላት ሀገሪቷን ሲመዘበሩ ሌሎች ዝም ይሉ ዘንድ የተነገራቸው ማግባቢያ ቃል ነው ።
ስለዚህ አንድ ኢትዮጵያዊ ልማት ላይ ነን እንስራበት ካለህ ፣ በ 11 ፐርሰንት አድጌ ፣ ምንም የምበላው የሌለበት ሀገር ሕዝብ አባል ነኝ ማለቱ ነው ። ታስጨርሰኛለህ እኔ ፖለቲካ አልፈልግም ማለቱ ነው ። ልማት ላይ ነን ማለት አጭር ትርጉሙ ፣ ፍርሃት ላይ ነን ፣ ዝምታ ላይ ነን ማለት ነው ። ስለዚህ ወዳጄ ቃል እንደ አገባቡ ነው የሚፈታው ።

5 Comments on “አንዳንድ ፣ አሸባሪ ፣ ልማት እና ወዘተ፣ የቃላት ትርጉም ( ሄኖክ የሺጥላ )”

  1. ” Zarie yanen mengedeña wediet
    bageñehut”, alech astu.
    Zaries eñam wediet bageñenew
    yanen yashofkubetn
    ‘ yesdet mengst’ , new yalachuht
    weys ‘ shengo’ .
    Letebaberut mengstat yeTor hayl
    wede ethiopia edilk temaTno
    endiyaqerb bastawskut.
    Ethiopian miwogat tegenTayu ye
    tgrai woyanie be mela ye ethiopia
    hzb lay Tornet kefto, worari
    yetgrai agazi Tor azmto chfchefa
    be ethiopiawiyan lay eyakahiede,
    ye sew zer maTfat ena ye Tor
    wonjel eyefeTem mehonen gelTo
    be mamelkecha endiTeyq
    bengerkut.

  2. ምን ቀብሮ ብቻ ሬሣቸውንም ማቃጠል ነው።

    ነዳጅና መብራት እጦት ከተማዋ በከፍተኛ ውጥረት ውሥጥ ነች የአለም የነዳጅ ዋጋ 30በታች በርሜሉ እየተሸጠ ወያኔዎች የደጎምነውን እያሥመለሥን ነው መጠኑ ለህዝብ ይፋ ባልሆነበት ሸር እጥፍ እየከፈለ እየተዘረፈ ይገኛል ሱዳንን ለመጥቀም ተብሎ እየሸረበ ያለው የነዳጅ ግዥ አዋጭ አለመሆኑን ባለሞያዎች ይናገራሉ ይህም ሆን ተብሎ የትራንሥፖርት ዋጋውንና የነዳጅ ልዩነቱን ታሪፍ ለመቀራመት በተዘዋዋሪ ብሩን ለአባይ እንደሚያውሉት ይነገራል።

  3. እንደብዙዎች የምንሥማማበት 11 ቁጥር ወያኔዎች እናታቸው በምላጭ ቅንድብና ግንባራቸውን የሚተለትሉበት የጭካኔ መለያና ቁፅርም ነች

  4. I also want to be one of «ye limat» employee as long as the Woyanes are sitting in there because, I’m sick and tired of working hard for little pay out. Thank you Woyanes!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*