” እስካሁን ካሰለጠኑኝ አሰልጣኞች ሁሉ ሰውነት ቢሻው የኔ ምርጥ አሰልጣኝ ነው” – ጌታነህ ከበደ

የብሔራዊ ቡድኑ የፊት መስመር ተሰላፊ ነው ፡፡ የአይረሴው የደቡብ አፍሪካው የአፍሪካ ዋንጫ ቡድን አባል፡፡ በ2014 አለም ዋንጫ ማጣሪያ ላይ ለብሄራዊ ቡድኑ ቁልፍ ነበር በስሙ ሶስት ጎሎች አስቆጥሮ ዋልያውን የአፍሪካ ምርጥ አስር ውስጥ ሲካተት ትልቅ የሆነ ድርሻን ተወጥቷል ፡፡ የዋልያው ድንቅ የፊት መስመር ተጫዋች ጌታነህ ከበደ ከኢትዮ አዲስ ስፖርት አዘጋጅ ህሊና አዳነ ጋር በፕሮፌሽናልነተ እግር ኳስ ተጫዋችነት ካለበት ደቡብ አፍሪካ አጠር ያለ አዝናኝ ቆይታን በእግር ኳስ ህይወቱ ዙሪያ እና በሌሎች አዝናኝ ጉዳዮች ላይ ቆይታ አድርጓል፡፡
image

ኢትዮ አዲስ ስፖርት ፡- ጌታንህ ጥያቄችን አክብረክ የኢትዮአዲስ ስፖርት እንግዳ በመሆንክ እናመሰግናለን
ጌታነህ ከበደ ፡- እኔም አመሰግናለው ፡

ኢትዮ አዲስ ስፖርት ፡- ከቅጽል ስምክ እንጀምር ሰበሮም የሚለውን ስም ማን ሊያወጣልክ ቻለ በምን ምክንያት
ጌታነህ ከበደ ፡- የደደቢት ክለብ መስራች እና ፕሬዝደንት የነበሩት ኮረኔል አወል ናቸው ቅጽል ስሙን ያወጡልኝ በውጪ ጨዋታ ላይ ሆነን ማነው ቅጽል ስሙ ተብለው ሲጠየቁ ሰበሮም ብዮዋለው አሉ፡፡ ሰበሮም ማለት የሚወዱት ጓዳቸው የነበረ ግለሰብ ነው፡፡

ኢትዮ አዲስ ስፖርት ፡- ወደ ደቡብ አፍሪካ ቆይታክ ስንመጣ አሁን ባለንበት በጥር የዝውውር መስኮት ዩንቨርስቲ ኦፍ ፕሪቶሪያን እንደምትለቅ በስፋት በሀገር ውስጥ እየተነገረ ይገኛል በዚህ ጉዳይ ላይ ምን ትላለክ
ጌታነህ ከበደ ፡- በፍጹም የሚወራው ውሸት ነው እኔ በእዚህ ደስተኛ ነኝ ቦታዮን ለማስከበር ጠንክሬ እየሰራው እገኛለው ክለቡን አልለቅም ፡፡
image

ኢትዮ አዲስ ስፖርት ፡- ጌታነህ ከበደ ኳስ ተጫዋች ባይሆን ምን ይሆን ነበር ?
ጌታነህ ከበደ ፡- ኳስ ተጫዋች ባልሆን ኖሮ አባቴ የልብስ ስፌት ባለሙያ ስለነበር የሱን ሙያ ተከትዮ ልብስ ፈፊ እሆን ነበር፡፡

ኢትዮ አዲስ ስፖርት ፡- አብሬው ብጫወት የምትለው ኢትዮጵያዊ እግር ኳሰኛ
ጌታነህ ከበደ ፡- የአዋሳው ከነማው ታፈሰ ሰለሞን በጣም የማደንቀው እና ሁሌም አብሬው ብጫወት የምለው ጎበዝ እግር ኳሰኛ ነው፡፡

ኢትዮ አዲስ ስፖርት ፡- እስካሁን ካሰለጠኑክ አሰልጣኞች ላንተ ምርጡ አሰልጣኝ የቱ ነው፡፡
ጌታነህ ከበደ ፡- እስካሁን ካሰለጠኑኝ አሰልጣኞች ሁሉ ሰውነት ቢሻው የኔ ምርጥ አሰልጣኝ ነው

ኢትዮ አዲስ ስፖርት ፡- ከውጭ በክለብ ደረጃ የማን ደጋፊ ነክ
ጌታነህ ከበደ ፡- የሊቨርፑል ደጋፊ ነኝ

ኢትዮ አዲስ ስፖርት ፡- ከውጭ በህይወት ዘመንህ ብትጫወትበት ደስ የሚልክ ስቴዲየም እና ክለብ የቱ ነው፡፡
ጌታነህ ከበደ ፡- አንፊልድ ሮድ ላይ ለሊቨርፑል

ኢትዮ አዲስ ስፖርት ፡- ከውጭ የምትወደው እና የምታደንቀው እግረኳሰኛ ማነው
ጌታነህ ከበደ ፡- ከቀደሙት እግር ኳሰኞች ሮናልዶ ሊዊስ ናዛሪዮ ዲሊማ ለኔ የምንጊዜም ምርጡ ነው፡፡ በአሁኑ ጊዜ ደግሞ የሊቨርፑሉን ኮቲንሆን አደንቃለው፡፡

ኢትዮ አዲስ ስፖርት ፡- በአሁኑ ወቅት በትውልድ ሀገርክ ዲላ የተለያዩ በርካታ የስፖርት እንቅስቃሴዎችን እያገዝክ እንደሆነ ይነገራል ፡ ምን አይነት ድጋፍ ነው የምታደርገው
image

ጌታነህ ከበደ ፡- ዲላ ላይ ያለውን የስፖርት እንቅስቃሴ በቻልኩት አቅም እደግፋለው፡፡ ለጊዘው ዋናውን የዲላ ከነማ እና የታዳጊውን ቡድን በትጥቅ እና በኳስ እየደገፍኩ እገኛለው፡፡

ኢትዮ አዲስ ስፖርት ፡- በ2018 የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ላይ ግብ ካስቆጠርክ በዋላ አሳይተከው የነበረው የደስታ አገላለጽ ከሌላው ጊዜ የተለየ ነበር፡፡ እንዴት እንዲህ ሊሆን ቻለ
ጌታነህ ከበደ ፡- አዎ በእለቱ ኮንጎ ላይ ጎሉን ካስቆጠርኩ በዋላ የተለየ የደስታ አገላለጽ ነው ያሳየውት ፡ እንዲህ አይነቱ ጭፍራን ለማሳየቴ ምክንያቴም ከብሄራዊ ቡድኑ በተቀነስኩበት ወቅት ህዝቡ ለምን አልተመረጠም በሚል ከጎኔ ስለነበሩ እነሱን ለማመስገን ነው፡፡

ኢትዮ አዲስ ስፖርት ፡- በ2005 በደደቢት ቡድኑን በአንበልነት እየመራክ የሊጉን ዋንጫ አንስተካል በወቅቱ ይህንን ዋንጫ ማንሳትክ የፈጠረብክ የተለየ ስሜት አለ
ጌታነህ ከበደ ፡- 2005 ለኔ በጣም ምርጥ አመት ነበረ ፡፡ ከምንም በላይ የሊጉን ዋንጫ ማንሳት ያስደስታል፡፡ በወቅቱ ከክለቤ ስኬት በተጨማሪ በግሌ የሊጉ ኮከብ ግብ አግቢ እና ኮከብ ተጫዋች ተብዮ መመረጤ የተለየ ስሜት ሰጥቶኛል፡፡

ኢትዮ አዲስ ስፖርት ፡- ደቡብ ፖሊስን ለቀክ ደደቢትን ስትቀላቀል 110.000 ብር የፊርማ ክፍያ እንደተከፈለክ ይነገራል ፡፡ በወቅቱም ባልተለመደ መልኩ ለደቡብ ፖሊስ የተለየ ነገር አድርገክ እንደወጣክ በሰፊው ይነገራል ምንድን ነበር በወቅቱ ደቡብ ፓሊስን ስትለቅ ያደርግከው
ጌታነህ ከበደ ፡- በጊዜው ብዙም የተለየ ነገር አላደርግኩም ለደቡብ ፖሊስ እግር ኳስ ክለብ ሙሉ የስፖርት ትጥቅ ነበር ገዝቼ ያበረከትኩት ፡፡

ኢትዮ አዲስ ስፖርት ፡- የእግር ኳስ ህይወትክ ምርጡ ጊዜ የትኛው ነው
ጌታነህ ከበደ፡- ቅድም እንደነገርኩሽ 2005 ለኔ የተለየ ነው ከ 31 አመት በዋላ ለ2013 የደቡብ አፍሪካ የአፍሪካ ዋንጫ ያለፍንበት ክስተት ለኔ ምርጡ ጊዜዮ ነው፡፡ አመቱ ለኔ የተለየ አመት ነበር፡፡
image

አጭጭር የሆኑ መልሶችን የሚፈልጉ አዝናኝ ጥያቄዎች

ኢትዮ አዲስ ስፖርት ፡- ከእግር ኳስ ውጪ የምትወደው ስፖርት
ጌታነህ ከበደ ፡- ከእግር ኳስ ውጪ የምወደው ስፖርት የለም ፡ ለእግር ኳስ የተለየ ፍቅር ነው ያለኝ

ኢትዮ አዲስ ስፖርት ፡- በእግር ኳስ ሕይወት ውስጥ ያሉ የቅርብ ጓደኞችክ
ጌታነህ ከበደ ፡- አዳነ ግርማ ፡ጀማል ጣሰው እና ፍቸው ተፈሪ የቅርብ ጓደኞቼ ናቸው፡፡

ኢትዮ አዲስ ስፖርት ፡- በተቃራኒ ከገጠሙክ አሰቸጋሪ ተከላካዮች በግንባር ቀደምትነት የምትጠቅሰው
ጌታነህ ከበደ ፡- በወቅቱ እዚህ እያለው (ኢትዮጵያ) ሲዳማ ቡናን መግጠም አልውድም ነበር ምክንያቱም ያኔ ተከላካያቸው የነበረው ቢያድግልኝ ኤሊያስ እጅግ የሚያስቸግረኝ ምርጥ ተከላካይ ነው፡፡

ኢትዮ አዲስ ስፖርት ፡- በእግር ኳስ ዘመንህ ያስቆጠርካት ድንቅ ግብክ የትኛዋ ናት
ጌታነህ ከበደ ፡- አብሳ ፕሪሚየር ሺፕ ለቬድቬስት ስጫወት ፕላቲኒየም ስታርስ ላይ ያገባውት ግብ ምርጧ የምላት ናት

ኢትዮ አዲስ ስፖርት ፡- የእረፍት ጊዜክን በምን ታሳልፋለክ
ጌታነህ ከበደ ፡- በትርፍ ጊዜዮ ብዙ ጊዜ ፊልም በመመልከት አሳልፋለው

ኢትዮ አዲስ ስፖርት ፡- አይተክ የወደደክው ሀገርኛ ፊልም
ጌታነህ ከበደ ፡- ኢትዮጵያ እያለው ያየውት እቴጌ 2 የወደድኩት ፊልም ነው፡፡
image

ኢትዮ አዲስ ስፖርት ፡- ከሀገር ውስጥ እና ከባህር ማዶ ሙዚቀኞች ማንን ታደንቃለክ
ጌታነህ ከበደ ፡- አስቴር አወቀ እና ሄነሪክ ኤግላሲያስ የምወዳቸው ሙዚቀኞች ናቸው፡፡

ኢትዮ አዲስ ስፖርት ፡- በድጋሚ ጥያቄያችንን አክብረክ የድህረጻችን እንግዳ ስለሆንከ በጣም እናመሰግናለን መልካም የእግር ኳስ ዘመን ተመኝንልክ
ጌታነህ ከበደ ፡ እኔም በጣም አመሰግናለው

 

 

 

 

 

Filed under: የሀገር ውስጥ ስፖርት