ቴሌ በጤና ላይ አደጋ ያደርሳል የተባለው የሞባይል ፍሪኩዌንሲ ሀሰተኛ መረጃ ነው አለ
ሰሞኑን ማንነታቸው ከማይታወቁ የሞባይል መስመሮች፣ ድረ ገጾች፣ ኤሜልና የሞባይል አጭር የጽሑፍ መልዕክቶች (SMS) አደገኛ የሞባይል ፍሪኩዌንሲ በጤና ላይ አደጋ ያደርሳል ተብሎ የሚናፈሰው ወሬ መሠረተ ቢስ መሆኑን፣ የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሽን አስታወቀ፡፡ ኮርፖሬሽኑ ዛሬ ለሪፖርተር በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፣ በዓለም ኅብረተሰብ ዘንድ ሆን ተብሎ ሽብር ለመፍጠር የታሰበ በመሆኑ፣ ተጠቃሚው ኅብረተሰብ ምንም ዓይነት ስጋት እንዳይሰማው አሳስቧል፡፡