የጋምቤላ ክልል ገዢ ፓርቲ አመራር ምርጫ ቅሬታ አስነሳ

(በታምሩ ጽጌ)

የጋምቤላ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ አንድነት ፓርቲ (ጋሕዴአፓ) ነሐሴ 26 እና 27 ቀን 2002 ዓ.ም. ባደረገው ስብሰባ ላለፉት ሁለት የምርጫ ዘመናት ይመሩ የነበሩት ኃላፊዎች በድጋሚ መመረጣቸው፣ አግባብነት የሌለውና የዴሞክራሲ መንገድን የተከተለ አለመሆኑን አንዳንድ የፓርቲው አባላት ለሪፖርተር ገለጹ፡፡