በአዲሱ ፖሊሲ የቱሪስት ፍሰቱን ከ20 በመቶ በላይ ለማሳደግ ታቀደ
(በሔኖክ ያሬድ)
ኢትዮጵያ በዓለም አቀፉ የቱሪዝም ገበያ ፉክክር ውስጥ ብቁ ተወዳዳሪ ለመሆን በሚያስችላት የቱሪዝም ፖሊሲዋ አማካይነት አሁን ያለውን የ13.5 በመቶ አማካይ የቱሪስት ፍሰትን ከ20 በመቶ በላይ ለማሳደግ መታቀዱን፣ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ በሥራ ላይ ያለው የባህል ፖሊሲንም እንደሚያሻሽለውም ገለጸ፡፡